Monday, June 15, 2015

የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44340#sthash.UdVHgBqd.dpuf

ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ዛሬ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። ከስፍራው የሚወጡት ዜናዎች እንደሚያረጋግጡት በአይከል ከተማ መሀል ገበያ ህዝብ ላይ ተኩስ የከፈቱት የህወሀት ወታደሮች በርካታ ሰዎችንም ማቁሰላቸው ተገልጿል። ከሶስቱ ሟቾች የሁለቱ ስም የታወቀ ሲሆን የአስር አለቃ ውቤ እና አቶ ብርሌ በህወሀት ወታደሮች ዛሬ ተገድለዋል። የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ሙስሊምም መገደላቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋልል:: እንደ ዘገባው ከሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ነው። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአይከል ከተማ ውጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል። በማንነት ጉዳይ የተነሳው የህዝብ ጥያቄ በመንግስት ምላሽ ተስጥቶታል ቢባልም አከባቢውን ወደትግራይ ክልል ለመጠቅለል በህወሀት መንግስት እየተደረገ ያለው ድብቅ ሴራ ህዝቡን እንዳስቆጣው ይነገራል። ባለፈው ቅዳሜ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በአብደራፊ የሚገኘውን የሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የእርሻ ይዞታ ሲያቃጥሉ የእኛ ድንበር የሚዋሰነው ከትግራይ ክልል እንጂ ከአማራ አይደለም ማለታቸው መዘገቡ የሚታወስ ነው። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44340#sthash.UdVHgBqd.dpuf

No comments:

Post a Comment