Monday, January 12, 2015

ከእናቷ ጋር አስፓልት እየተሻገረች መኪና የበላት የ19 ዓመቷ የነፋስ ላይ ሻማ የሜሪላንዷ ቤዛ አማረ

beza amare




















 ትናንት በዘ-ሐበሻ የዜና እወጃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ በሜሪላንድ ከአውቶቡስ ወርዳ ወደ ቤቷ ስታመራ በመኪና ተገጭታ መሞቷን ዘግበን የሟቿን እህታችን ፎቶ ባለመለጠፋችን በርከት ያሉ አንባቢዎቻችን ፎቶዋን እንድናቀርብ ጠይቀውን ነበር::

የ19ኝ ዓመቷ ቤዛ ፎቶ ግራፍን አቅርበናል:: ቤዛ አማረ የተባለችው የ 19 ዓመት ወጣት የተገጨችው ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ሲሆን፣ ከአውቶቡስ ወርዳ ከ እናቷ ጋር ወደ ቤት ለመሄድ መንገድ እየተሻገሩ ሳለ ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ሲሻገሩ የነበረው “ተሻገሩ” የሚለው የ እግረኞች ምልክት ሳይበራ ነበር። ገጪው የ 68 ዓመት ሰው ፣ ጥቂት ጉዳት ደርሶበት ታክሞ ከሃኪም ቤት ወጥቷል።
ለቤዛ የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ በሜሪላንድ እየተደረገ ሲሆን ሁላችሁም እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል:: ነብስ ይማር:http://www.youcaring.com/memorial-fundraiser/funeral-fund-for-beza-eshetu-/287980#.VK22-_bqbvk.facebook

No comments:

Post a Comment