Monday, January 12, 2015

በጎንደር አርማጭሆ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊበርድ አልቻለም

10923573_1560615314186107_7573440129440943485_n


















ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ በጎንደር አርማጭሆ ውስጥ <<ሶረቃ>> የሚባለውን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማካለል በወሰዱት እርምጃ የተነሳው ግጭት እስካሁን ሊበርድ እንዳልቻለ በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል።
ወኪላችን እንዳለው ታጣቂዎቹ፤ አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት አስነስተው ቦታውን ለማካለል ያደረጉትን ጥረት የአካባቢው ህዝብ ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስና ውጊያ ጭምር በመግጠም ነበር ያከሸፈው።በወቅቱ የታጣቂዎቹን እርምጃ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ከሁለቱም በኩል ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
ውጥረቱ እስካሁን ያልበረደ ከመሆኑም ባሻገር የ አካባቢው ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር እየተጠራራ ንብረቱን ለማስጠበቅ በአንድ ተሰባስቦ መዘጋጀቱ፤ ሌላ ዙር የከፋ ግጭት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት አሳደሯል።

No comments:

Post a Comment