Monday, January 12, 2015

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው።

UDJየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው። የጠቅላላ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ በየሶስት አመቱ ሲሆን አስቸኳይ ወይንም ልዩ የጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚቻል የአንድነት ደንብ በግልጽ ያስቀምጣል፡ በአንድነት ደንብ መሰረት አስቸኳይ ወይም ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ መጥራት የሚቻለው ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት አንድ ሶስተኛው ሲጠይቁ ወይንም ምክር ቤቱ ሲወስን ብቻ ነው። የጠቅልላ ጉባኤ አባላት በፓርቲው የተመዘገቡ፣ የድርጅቱ አባልነት መታወቂያ ያላቸው ናቸው። የድርጅቱ የሥር አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣ የቀድሞ ሊቀመንበር ሆነ የአሁኑ ሊቀመንበር ጠቅላል ጉባኤ የመጥራት ስልጣን በደንቡ መሰረት የላቸውም።
በዚህ መሰረት ከጠቅላላ ጉባኤ ቀጥሎ የድርጅቱ የበላይ አካል የሆነው ብሄራዊ ምክር ቤቱ፣ ሐሙስ ታህሳስ 30 ቀን ባደረገው ስብሰባ ነበር እሁድ የሚደረገዉን ጠቅላላ ጉባኤዉ የጠራው። በምክር ቤቱ ስብሰባ፣ “ቅሬታ አለን” ባለው አሁን ባለው አመራር ላይ ችግር ያላቸውና ምርጫ ቦርድ በመሄድ ከምርጫ ቦርድ ጋር አብረው ሲሰሩ ከነበሩት መካከል፣ ሶስት የምክር ቤት አባላት ( 5 %) ፣ ሐሳባቸውን እና ታቋዉሟቸውን ለማሰማት እድል ተከፍቶላችው የነበረ ቢሆንም፣ ዝምታን መርጠዋል። በስብሰባው የተገኙ ሌሎች 39 (78%) የምክር ቤት አባላት ግን የጋራ አቋም በመያዝ፣ በምርጫ ቦርድ እየተደረገ ያለውን ኢ-ሕገመንስግታዊ እንቅስቃሴ በማውገዝ አንድነት በፊቱ የተደቀነበትን መሰናክል ያልፍ ዘንድ ጠቅላላ ጉባዔዉ በተሎ እንዲጠራ የወሰነው።
መኢአድ እና አንድነት የዉህደት ስምምነት በሚፈርሙበት ጊዜ ኢሕአዴግ ዱርዬዎች ልኮ ስብሰባዉን ለመረበሽ ሞክሮ እንደነበረ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር፣ ፖሊስ ለምን አስቀድማችሁ አልነገራችሁኝ ነበር እንዳለይ፣ ፖሊሲ አስፈላጊዉን ጥበቃ እንዲያደርግ ከወዲሁ የማሳወቅ ሥራም ተሰርቷል። ምርጫ ቦርድ ሕጉ እንደሚጥይቀው ታዛቢዎች እንዲልክም ደብዳቤ እንዲደርሰው ተደርጓል።

No comments:

Post a Comment