የሕዝባችን አንድነት እና የአገራችን ታሪካዊ መልካአ-ምድር ለመጠበቅ ታሪካዊ ሃላፊነት ለሚሰማችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፦
እንደሚታወቀው የጎንደር ክ/ሀገር፤ የጋራ መመኪያችን ለሆነችው ኢትዮጵያችን የአንድነት መሰረት የታሪክ እምብርት በመሆን ትታወቃለች። በመሆኑም፤ ለሁላችንም ኩራት እና መመኪያ የሆነችውን ኢትዮጵያ አገራችን ለማጥፋት መሰሪ አላማን ይዘው የተነሱ አገር አጥፊዎች ሁሉ የመጀመሪያ የጥፋት ክንዳቸውን የሚሰነዝሩት፤ ጦራቸውን የሚወረውሩት አላማቸው በቀላሉ ይሳካ ዘንድ በቅድሚያ በጎንደር ላይ ነው። እንደምሳሌ የውጭ ወራሪዎችን ብንጠቅሥ፤ በእጅ አዙር ቱርኮች ከግብፃዊያን ጋር በመተባበር የሀገር ውስጡን ግራኝ መሃመድን በመሳርያነት በመጠቀም ከ1519-1535 ዓ. ም፤ እንዲሁም ድርቡሾች በ1880-81 ዓ. ም. በቀጥታ፤ በማዝመት፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ወገኖቻችን ጨፍጭፈዋል፤ የታሪክ ቅርሶችን መዝብረው፤ ቀሪውን ለማሥረጃ እንዳይተርፍ ለቃቅመው አቃጥለዋል። —
No comments:
Post a Comment