Wednesday, January 14, 2015

በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም አካባቢ እሳት ተነሳ

ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ
ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ

(ዘ-ሐበሻ) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደዘገበው በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ እሳት ተነሳ::
እንደ ዘገባው ከሆነ እሳቱ የተነሣው ከደኑ አካባቢ ሲሆን ወደ ገዳሙ ገና አልደረሰም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት መድረሱ ተሰምቷል ያለው ዲ/ን ዳንኤል አባቶች እሳቱን ቆርጦ ለመከላከል እየሞከሩ ነው ብሏል::
በደጋ እስጢፋኖስ የተነሳውን እሳት በሰው ኃይል ለመከላከል የማይቻል ከሆነ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክልሉ ገልጦላቸዋል ሲል ዲ/ን ዳን ኤል ዘገባውን ቋጭቷል::

No comments:

Post a Comment