Wednesday, August 26, 2015

ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው? – በያሬድ ታዬ መኮንን፤ ቶሮንቶ

ቶሮንቶ ከመጣሁ ሶስተኛ ሳምንቴን ያዝኩኝ፡፡ ቀኑን ሙሉ፤ ከሰሜን ደቡብ፤ ከምስራቅ ምእራብ ሳካልለው ውዬ፤ መጀመሪያ በጓደኛዬ ቤት፤ አሁን ደግሞ መንግስት በሰጠኝ፤ በቶሮንቶ፤ ኦንቴርዮ ጎዳና ላይ በሚገኘውና እኔና ሌላ አንድ ሰው በምንጋራው ክፍል ጣሪያ ስር ሆኜ፤ ወደጣሪያው አንጋጥጬ፤ የኢትዮጵያና የካናዳ ህይወቴን፤ እንዲሁም ነጻነቴን ማሰላሰል ይዣለሁ፡፡ ነጻነት እንዴት ይጥማል፡፡ ድህነት አንድ ነገር ነው፡፡ መራብም አንድ ነገር ነው፡፡ ሰው ግን ነጻነቱንና ክብሩን እንዴት ባገሩ ይነፈጋል፡፡ እነሆ በማያውቁን፤ በማላውቃቸው፤ በሰው አገር የተሰጠኝ


Ethiopia


 ክብርና እንክብካቤ እያጣጣምኩ ሳለሁ፤ የሩቅ ጓደኛዬ የነገረኝ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡  ይህ የሩቅ ጓደኛዬ አውነተኛ ታሪክ ነው ብሎ ያጫወተኝን፤ እኔም የተቀበልኩትን ገጠመኝ ላጫውታችሁ፡፡ እውነት መሆኑን እንዴት ተቀበልከው፤ ያላችሁኝ እንደሆነ ኢትዮጵያ ሃገሬ ውስጥ እንኳን ይሄ ይቅርና፤ ወያኔ “ተቃዋሚዎችም መርጠውኛል”  ብሎን ተቀብለነው የለም እንዴ? መቼ ነው ያለው፤ ለምትሉኝ ደግሞ አሁን ባሳለፍነው ምርጫ 2007፤ በአይኔ ያየሁት፤ ምናልባትም ብዙዎቻችሁ በሶሻል ሜዲያ ያነበባችሁ፤ እና ያሰገረማችሁ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳየው፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች፤ ከ1000 መራጮች መካከል ኢህአዴግ፤ 1000 ከ1000 ተብሎ በምርጫው ጣቢያ ሲለጠፍ፤ አስቡት እንግዲህ፤ ይህ 1000 መራጭ የተቃዋሚ ተመራጭ ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ መሆኑን፡፡ እንግዲህ ይህንንም አምነን “አሜን” ብለን ተቀብለን የለም ወይ? እንግዲህ የጓደኛዬንም የህይወት ገጠመኝ አምኜዋለሁ፡፡ የወያኔን ጉድ እስቲ ይሁን ብለን እንለፈውና ወደዋናው ታሪክ እንመለስ፡፡ በነገራችን ላይ ስም መጥቀስ ስላላስፈለገኝ፤ ጓደኛዬ እያልኩ በመተረኬ፤ ቅር አይበላችሁ፡፡ ያው እንደምታውቁት ጊዜው አስቸጋሪ ስለሆነ ስም ባይጠቀስ ይሻላል ብዬ ነው፡፡ ይህ ጓደኛዬ እና አንድ የስራ ባልደረባው ከስራ በኋላ መሸትሸት ሲል ለመዝናናት፤ 22 አካባቢ ወደሚገኙት የመዝናኛ ቤቶች ጎራ ይላሉ፡፡ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላኛው በመቀያየር ሲዝናኑ ይቆዩና፤ አትላስ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ታዋቂ የጭፈራ ቤት (በተለምዶ ክለብ) ይገባሉ፡፡ በክለቡ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን፤ ከእነዚህም መሀከል ከወደምስራቅ አካባቢ የመጡም (በግምት ቻይናውያን ይመስሉታል) ነበሩበት፡፡ ሙዚቃው ቀጠለ፤ ጨዋታውም ደራ፡፡ መቼስ በዳንስ ውዝዋዜ መሀል መነካካት አይጠፋም፤ የጓደኛዬ ጓደኛ ከአንዱ ቻይናዊ ጋር ይነካካል፡፡ ከዚያም ይቅርታ ጠይቆ ጨዋታውን ይቀጥላል፡፡ ቻይናዊው ጉዳዩን በቀላሉ አልተመለከተውም፡፡ “ሳታውቅ ሳይሆን እንደው ነገር ስትፈልገኝ ነው” በማለት እምቧ ከረዮውን አቀለጠው፡፡ ሰዎች ነገሩን ለማረጋጋት ቢሞክሩም፤ አጅሬ ቻይና ካልደበደብኩት ብሎ ሰፈሩን ቀውጢ አደረገው፡፡ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ መሆን በጀመረበት ሰዓት፤ የሀገሬው ፈላጭ ቆራጭ፣ ምንም ቢያደርግ ጠያቂ የሌለው፣ ማሰር፣ መደብደብ ካሻውም መግደል መብት የተሰጠው፤ መቼስ ታውቁታላችሁ ስለማን እያወራሁ እንዳለ፤ የወያኔ አካል የሆነው፡ ፈደራል ፖሊስ መጣ፡፡ ግርግሩም ቀዝቀዝ እያለ ሁሉም በመረጋጋት ስሜት ባሉበት ሁኔታ፤ ቻይናዊው ፌዴራሉን ሲመለከት የልብልብ ተሰምቶት ኖሮ፤ እጁን ሰንዝሮ የጓደኛዬን ጓደኛ በቡጢ ቢለውስ፡፡ ያኛውስ ከማን አንሶ በእጁ በሶ አልጨበጠ መልሶ ቢቦቅሰውስ፡፡ ታዲያ ይኽኔ ነበር ግራ የሚያጋባውና ማንነትን የሚፈታተነው ጉዳይ የተከሰተው፡፡ እንዲህ ነው የሆነው፡፡ ከፌዴራል ፖሊሶቹ መሀከል ሁለቱ ተንደርድረው መሃል በመግባት አንደኛው ቻይናዊውን ወደ ጎን ሲያደርገው፤ ሌላኛው የጓደኛዬን ጓደኛ በዚያ በያዘው የሚያቃጥል ቆመጥ (መቼስ የቀመሰ ያውቃታል) ሲዠልጠው ለተመለከተ ማንኛውም ሰው፤ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ ነበር፡፡ ቻይናዊውም ለካስ ይኼን አውቆ ኖሯል እንደዛ የልብልብ ተሰምቶት ቦክስ የሰነዘረው፡፡ ለጓደኛዬ ጉዳዩን ዝም ብሎ መመልከት አልሆንለት ቢለው፤ ጠጋ ብሎ በልመና መልክ ለማግባባት እየሞከረ፤ “ኽረ እባካችሁ ተውት እሱ ምንም አላጠፋም” በማለት ለማስረዳት ቢሞክር፤ አንተስ የት ይቀርልሃል ብለው ያላንዳች ማመንታት የዚያች ቆመጥ ተቋዳሽ በማድረግ፤ ሦስት አራት ጊዜ ካቀመሱት በኋላ፤ ቻይናዊውን በክብር ከይቅርታ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ በምልክት (ያው እንደምታውቁት ቋንቋ ችግር ነው) ይነግሩት እና ጓደኛዬን እና ጓደኛውን በያዙት ፒክ አፕ መኪና ጭነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ፡፡ ለመዝናናት የወጡት እኚህ ኢትዮጵያውያን፤ በገዛ ሀገራቸው ክብር ተነግፏቸው፤ ለውጭ ዜጋ ጎንበስ ቀና ባለማለታቸው የመዝናኛ ጊዜያቸውን በፖሊስ ጣቢያ አሳልፈው፤ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይለመዳቸው ከማስጠንቀቂያ ጋር በበነጋታው መለቀቃቸውን የነገረኝ፤ እጅግ በንዴት እና በቁጭት መንፈስ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች በተለያየ መንገድ ያጋጠመን ሰዎች እንኖር ይሆናል፡፡ ያላጋጠማችሁም ወደፊት ቢያጋጥማችሁ ግር አይበላችሁ፡፡ እንደው ነገርን ነገር አነሳውና ነው እንጅ፤ ከዚህም የባሰ ብዙ አይተናል ሰምተናል፡፡ ሁሌም ውስጤን የሚያንገበግበው ነገር ቢኖር፤ ቢያንስ ለሌሎች ዜጎች ሀገራችን ላይ የሚሰጣቸውን ክብር ያክል እንኳን ሰው በሀገሩ የማይሰጠው ከሆነ ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው? ማንስ አለሁልክ፤ አይዞህ ይለዋል? ሁሉም ነገር ከራስ ነው የሚጀምረው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ፍቅርም ቢሆን፣ አክብሮትም ቢሆን ለራስ ሰጥቶ ነው ወደሌላኛው የሚኬደው፡፡ እራሱን እና የራሱ የሆነውን የማያከብር፤ ሌላውን አከብራለሁ እጠብቃለሁ ቢል፤ ለእኔ እንደማስመሰል ነው የምቆጥረው፡፡ እዚህ ላይ የሌላ ሀገር ዜጎች አይከበሩ እያልኩኝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰው ከሀገሩ የበለጠ ጥበቃ እና ከለላ ሊያገኝ የሚችልበት የተሻለ ቦታ የት ነው ያለው? ያደጉት እና እኛን ጥለው የሄዱት ሀገራት ከሀገራቸው አልፈው በሰው ሀገር ስለሚገኙት እያንዳንዱ ዜጎቻቸው ክትትል በማድረግ፤ ያሉበትን ሁኔታ ሰላማዊነት ሲያረጋግጡ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ሀገራችን ውስጥ ግን ለሚከሰተው ማንኛውም ጉዳይ የዜጎቹን መብት ሊያስከበር የሚችል ስራ የመስራት ግዴታ የመንግስት አንዱ ሃላፊነት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሰው ሀገር አለኝ ብሎ በሀገሩ ሰርቶ እና ተለውጦ፣ የዘር፣ የጎሳ፣ እንዲሁም የቀለም ልዩነት ሳይገጥመው መኖር ካልቻለ፤ ከመሰደድ ውጭ ምን አማራጭ ይኖረዋል? አስቡት እስቲ በሀገሩ ክብር ተነፍጎት በሰው ሀገር ተከብሮ የሚኖረውን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል? እንደው ወያኔ የሀገር ትርጉም አልገባውም እንጂ ቢገባው ኖሮ ይሄንን ግጥም ያዜምልን ነበር፡- ሀገርን ሀገር ያሰኘው ሰው የተባለው ፍጡር  ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45792#sthash.HtfvoDRG.dpuf

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

==================================
* ህጻን የደፋረን የ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል ?
* ፍርዱ ቅጣት ነው? ወይስ ማበረታታት ?
* ህግ አውጭና አስፈጻሚ አካላት ወዴት ናችሁ?

* ወላጆቿ ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!”ይላሉ  

የኢፊድሬ ህገ መንግሰት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል ። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል ! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል ። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም ። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር ዝርዝሩ ሰፋ ያለ ይሆናል ። ዳሩ ግን የህግ እውቀት ኖሮኝ ያንን ለመተንተን ባይዳዳኝም በህግ አስከባሪዎች ፍትህ እየጎደለ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል ዘልቆ ቢያመኝ እንደ ዜጋ በጎደለው ፍትህ ተቃውሞና በቅሬታየ ዙሪያ የዜጋ ድምጼን ማሰማት ግድ ብሎኛል …
ዛሬ ዛሬ የምንሰማው ሰው በሰው ላይ ቀርቶ በእንስሳ ላይ መፈጸም የሌለበትን ርክሰት የተጠናወተው ወንጀል ጀሯችን ሆኗል ። በተለይ በአቅመ ደካማ ህጻናት ታዳጊዎችና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እያደር መክፋቱ ጸሀይ የሞቀው እውነት ሆኗል። በዚህ ረገድ እየተኬደ ያለውን የከፋ ወንጀል ሳስበው ” ወደ የት እየሄድን ይሆን? ” እያልኩ ያስፈራኛል ! የአጉራ ዘለል አስገድዶ የመድፈር ወንጀለኞች መስፋፋት ፣ እያደር ውሎ አዳራችንና አብሮነታችን እንዳያጎድፈውም በአስፈሪ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ! ሴሰኛ ወንጀለኛ ሽምጥ ጋልቦ እዚህ ሲደርስ ወንጀሉን በጥብቅ ተከታትሎ የማያዳግም ቅጣት አርአያነት ያለው ውሳኔ ቢሰጥ ዛሬ እዚህ ባልተደረሰ ነበር ፣ ይህ አይፈጸምምና ፣ ይህ አልተደረገምና ዛሬ ውርደትን መከናነብ ግድ ብሎናል ። የተከናነብነው ውርደት ምክንያት የሆነን ወንጀልም ሊሰሙት ከሚችሉት በላይ ሰቅጣጭና የከበደ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ አይገድም !
ይህን ሁሉ የምለው በአንዲት የ4 ዓመት ከ6 ወር ብላቴና ተዳጊ ላይ የተፈጸመው ወንጀልና ተመጣጣኝ ያልሆነውን የፍርድ ውሳኔ ወደምቃዎምበት የማለዳ ወጌ የመረጃ ግብአት ለመዝለቅ ነው ! እንደኔ የፍትህ መዛባት ዘልቆ ያመማችሁ ተከተሉኝና ፍርዱን ስጡ … !
በያዝነው ሳምንት ማህበራዊ መገናኛ ድህረ ገጾችን ቀልብ የሳበው ጉዳይ መካከል የ4 ዓመት ከ6 ወሯ ታዳጊ መደፈርን ተከትሎ የተላለፈው ዜና የብዙዎቻችን ቀልብ ስቧል ። ለዚህ መሰሉ ዜና አዲስ ባይንሆንም ብላቴናዋ መደፈሯ ሳይሰማ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በመጨረሻ ው የፍርድ ውሳኔ ጋር ሰማን ፣ በውሳኔውም ደፋሪው የ4 ወር እስራት ቅጣት ፍርድ መሰጠቱን በአንድ ላይ ሲነገረን ማመን ከተቸገሩት መካከል አንዱ ነበርኩ። የጉዳዩን ጭብጥ ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ያገኘሁት መረጃ ይዠ የዜጋ ተቃውሞ ድምጼን በማለዳ ወጌ ላሰዳ ስውተረተር በድሬ ትዩብ ስሟን በመጥቀስ በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበ አንድ ዘገባ ለወጌ መረጃ ግብአትነት ተጠቅሜበታለሁ ። ትክክለኛ ስሟ ስለመሆኑ ግን ማረጋገጫ አላገኘሁም ። ስሟ ቢታወቅም መግለጹ አስፈላጊ ባለመሆኑ የድሬ ትዮብን ስም ተቀብየ እዘልቃለሁ ። ከዚሁ በተጨማሪ ሌላም ሌላ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጣራት ሞክሬ በእርግጥም ወንጀሉ ለመሰራቱና ፍርደ ገምድል ብይን የመሰጠቱ ሁነኛነት አረጋግጫለሁ !
የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚስረዱት ታዳጊዋን የ4 ዓመት ከ6 ወር ተዳጊዋን አሚራ ትባላለች ። ኑሮዋም አዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ እንደሆነ ተጠቁሟል። ደፈረ የተባለው አስነዋሪ ወንጀል ፈጻሚ የ25 ዓመት ጎረምሳ ነው። በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት የአሚራ ቤተሰቦቿ ቤት ጎን ተከራቶ ነበር አሉ ።
ከውሳኔው አስቀድሞ ተከሳሽ አሚራን ስለመድፈሩ ክስ ቀርቦበት ፣ ጉዳዩ በፖሊስ ቀርቦና ተጣርቶ ተከሳሽ ተይዞ በፊዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ችሎት የቀረበ ሲሆን በ30 ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቀ። ክሱን በዋስ ወጥቶ እንዲከላከል በፊዴራድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ያ ከሆነ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ተከሳሽ ለብይን ቀረበ ። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የቀረበለትም ምርመራ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ” ተከሳሽ ድንግልናዋን ባይገስም በእጆቹ የማህጸኗ ግድግዳ የመሰንጠቅና የመላላጥ ጉዳትና ማድረሱና በማህጸኗ የመቅላት ምልክት በመታየቱ !” በሚል ማስረጃ ፍርድ ቤተ ተከሳሽን ” ሞከርክ ” በሚል ወንጀለኛ ሲል የ4 ወር እስራትን አስተላልፎበታል ። ይህው ፍርድ ቤት ገና የትምህርት ገበታ ያልቀመጠችን ታዳጊ ብላቴና አመራን የደፈረበትን የጨካኝ ድርጊት ከደፈረ ሞከረ ቀይሮ በቀረበ ማስረጃ በፍትሀ ብሔር ህግ 6264 ሀ መሰረት ውሳኔ መሰጠቱ ተነግሮናል ። አስገራሚ ፣ አስደንጋጭና አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ !
ክሱን አቀለለ ወደተባለው ምክንያት ስንሄድ ደግሞ ይበልጡኑ እንታመማለን … ወንጀለኛው ” የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛና በቀጣዩ አመት ተመራቂ !” መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቦ በፍርድ ቤቶ ተቀባይነት ማግኘቱ አገኘ ብለውናል ። ለእኔ የክስ ማቅለያ የቀረበው ሀሳብ የተማረ የተመራመረው ” የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ” ነኝ ባይ ወንጀለኛ ነው ፣ ምንም የማታውቅን እምቦቃቅላ ታዳጊ ገላን በአሻው መንገድ አድርጎ ገፎታል ፣ ገፈፋውም የተፈጸመው በአንድ አዋቂ መሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊያከብድ እንጅ ሊያቀል ባልተገባ ነበር ባይ ነኝ ። ይህ ያቀረበው የክስ ማቅለያ ይልቁንም በሰነድ ተረጋግጦ ክሱን ማጠንከር ሲገባው ክሱን ማቅለያ ሆኖ መቅረቡና ከምን ወደ ምን እንደቀለለ ያልተገለጸው ማቅለያ ተቀባይነት ማግኘቱ በራሱ በምንም ሚዛን ፍትሃዊነት የለውም ! ይህን ለመናገር ሰብእናና የራስን ፍርድ መስጠት እንጅ ግዴታ ህግ ማጥናት አያስፈልገውም …
የህዝብን መብት ለማስጠበቅ የተሰየሙትን የፍትህ አካላት የሙያ ብቃት ጥያቄ ውስጥ የጣለው ይህ መሰሉ አሳዛኙ የፍትህ ውሳኔ ማህበረሰቡ በፍትህ እንዳይተማመን ከማድ ረግ ባሻገር በህግ ጥላ ስር መጠበቁን በጥርጣሬና እንዲ ያይ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም ። ከዚህም አልፎ ተርፎ በአሚራ ደፋሪ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሀገሬው ፍትህ አጥቶ የሚንገዋለል እንዲሆን አድርጎታል ወደሚል መደምደሚያ አድርሶኛል … የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞ ች ጉዳይ መስፋፋትና ገደብ ማጣት በተደጋጋሚ በመንግ ስት ላይ የሰላ ወቀሳ ይቀርባል ። በተለይም የህግ ጥበቃ ውንና ቅጣቱን ከማጠንከሩ በተጓዳኝ ተማኝነት እንጅ የሙያ ብቃት ሚዛን ሆኖ ቅጥር ስለማይፈጸም ተደጋጋሚ ችግሮች ተስተውለዋል ። የፍትህ አካላት ብዛት እንጅ ጥራት የጎደላቸው መሆኑ ከዚሁ ጋር ይጠቀሳል ። የተባለውን ወቀሳ እውነታነት እንዳለው ለመረዳት የአሚራን አይነት በደል ተሰርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከት ብቻ ማየት ከበቂ በላይ ይመስለኛል ።
በአሚራ ውሳኔ አሰጣጥ እንዳየነው ከምንም በላይ የፍትህ ስርአቱ በወንጀለኛውም ሆነ በጠበቆች የቀረበውን የተውተፈተፈ መከላከያና ቅጣት ማቅለያ መቀበላቸው ለፍትህ አካላት የደረሱበትን ደረጃ ያሳይ ከሆነ መልካም ነው ። የአሚራን ጉዳይ በግርድፉ ላየ ለተመለከተው ጥፋታቸውን በአዞ እንባ ለመሸፋፈን ከተጉ ወንጀለኞች ጎን ለገንዘብ ብለው ጥፋቱን ለማቅለል ሚሞግቱት ጠበቆች ሰብዕና ያማል ፣ የዳኞቹ ውሳኔ አሰጣጥና ውሳኔ ማቅለያ አቀባበል ደግሞ ይገርማል ፣ ይደንቃል … ! ይህ መሰል ከእውነታው ጋር የሚጋጭ የተፋለሰ ፍርድ በአደባባይ ሲሰጥ ህጉን ማስከበር ያለባቸው አቃቤ ህግ ተወካዮች የታሉ ? ፍትህ ወዴት ነህ ? ያስብላል …
በሰብዕና ላይ ወንጀል ሲሰራ በቸልተኝነት መመልከት ሊቆም ይገባል ። የሴቶችን መብት ለማስከበር ተብሎ የወጡት ሕጎች ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አካል የሆነ የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን በ2005 ዓም መቋቋሙን ከሰማን አመታት ተቆጥረዋል ። ኮሚሽኑ በሴቶችና በሕጻናት ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተገን እንደሚሆን ቢጠቀስም ለአሚና የጎደለ ፍትህ ድምጹን ሲያሰማ አለመታየቱ ግር ያለው እኔን ብቻ ከሆነ መልካም ነው ፣ ግን አይመስለኝም ። ” መብቷ ይከበር ፣ ፍትህ ጎድሎባታል፣ ፍትህ ታግኝ ” የምንላት ታዳጊዋ አሚራ ያለ ፈቃዷ አይደለም ገላዋ የጸጉር መጠምጠሚያ “ሂጃቧ ” ሊነካ አይገባም ፣ ከተነካ ህግ ተጥሷል ! አሚና ድንግልናዋ አልተገሰሰም ፣ ማህጸኗ ግን ተነካክቷል ብሎ ወንጀለኛን ከአስገድዶ መድፈር ወንጀል ማራቅ ፣ ማሸሸት ፍትህን ማረጋገጥ ሳይሆን ፍትህን ማርከስ አድርጌ ነው የምቆጥረው ። ወንጀለኛው ” አስገድዶ የደፈረ ” ለመባል አሚራ በጭካኔ ተደፍራ እንደተገደለችው እንደ ሀና ኦላንጎ መሆን አልነበረባትም ! አሚራም ሀና እንደሆነችው ባትሆንም በአሚራም ማህጸን ዙሪያ ክብረ ነክ የመድፈር ሙከራ አድርጓል ። የቀረበው ማስረጃ የሚየስረዳው አርቆ አሳቢው የተማረ ጎልማሳ ምንም በማታውቀው የ4 ዓመት ከ6 ወር ታዳጊ ህጻን ላይ ወንጀል አስገድዶ መድፈር ለመሆኑ ሌላ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለ ብየ አላምንም!
የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን ሴቶች ሥርዓተ-ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶባቸው እንዲህ ሲመለከት አብሮ ከተጎጅ ወገኖች ጎን መቆም ፣ የሕግ ጥበቃ ማቆም ፣ የህግ ጠበቃ የማቆም አቅም ከሌለው የህግ ጥሰቱን በአደባባይ ተቀውሞ ስታዳጊዋ ብላቴና ስለአሚራ ፍትህ ማግኘት ድምጹን ሊያሰማ ይገባል !
በፍርድ ገምድሉ ውሳኔ ያዘኑ ቤተሰቦች ወላጆቿ ፍትህ ጎድሎባቸው ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!” ማለታቸው ስሰማ የእነሱም ጩኸትና አቤቱታ የእኔም ለአሚራና ቤተሰቦቿ ፍትህ ርትዕ ይከበርላቸው የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል ! ከምንም በላይ የሴት ልጅ በረከት የታደልኩ አባት እንደመሆኔ የሴት ልጅን ወሰን የሌለው ፍቅር አውቀዋለሁና ከአሚራ ቤተሰቦች ጋር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ፣ በጎለው ፍትህ አምርሬም አዝኛለሁ … !
ፍትህ ለህጻን አሚራና ቤተሰቦቿ ስል እጠይቃለሁ !
ነቢዩ ሲራክ

ነሀሴ 5 ቀን 2007 ዓም

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45788#sthash.Lzyw7Bby.dpuf

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ

85e2b2dbb35ca49ffb94675c848f9135_Lኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በመጪው መስከረም ወር አራተኛ ሳምንት ላይ ደግሞ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱን ለመምራት የሚያስችለውን ፓርላማ ሥራ ያስጀምራል፡፡
ላለፉት 24 ዓመታት አገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው ኢሕአዴግ አሁን ቆም ብሎ በአንክሮ ራሱን መገምገም አለበት፡፡ ውስጡን አብጠርጥሮ መፈተሽ አለበት፡፡ የተሸከማቸውን ጉድፎች አራግፎ በሥርዓት አገር ማስተዳደር አለበት፡፡ በስኬቶቹ የሚመፃደቀው ኢሕአዴግ በጣም በርካታ ጉድለቶች ስላሉት መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ያጥራ! ራሱን ይመልከት!
ኢሕአዴግ በአሥረኛው ድርጅታዊ ጉባዔው የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም፣ ሁለተኛውን ዕቅድ አጠናክሮ ለመቀጠል ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት በኢሕአዴግ አመራር የተመዘገበውን ዕድገት ለማስቀጠል፣ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ቀጣዩ ትኩረት እንደሚሆንም እንዲሁ ትልቅ ግምት የተሰጠው አጀንዳ ነው፡፡ ይህ ለአገር ጠቃሚ በመሆኑ ድጋፍ ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ዕድገቱም ሆነ ትራንስፎርሜሽኑ ሰው ሰው ካልሸተተ፣ የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ካላከተተ፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ካልተመቸ፣ የሕዝቡን የነቃና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ ካላረጋገጠ፣ ሙስናን ከሥሩ መንግሎ ካልጣለ፣ ፀረ ዴሞክራሲ ተግባራትን ካላስወገደ፣ ሕገወጥ ተግባራትን ካላጠፋ፣ ወዘተ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡
አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ሲያምኑ፣ ሕግም ለሁሉም ዜጎች እኩል ጥበቃ ሲያደርግ፣ ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ ሲሆንና የፍትሕ ሥርዓቱ በነፃነት ሲንቀሳቀስ የሕግ የበላይነት መኖሩ ይረጋገጣል፡፡ ‹‹አንድን ንፁኅ ዜጋ ከማሰር ይልቅ አንድ ሺሕ ዜጎችን መፍታት የተሻለ ነው›› የማለው የሕግ ጽንሰ ሐሳብ በአንድ አገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ፣ ዜጎች በነፃነት በአገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ሰበብ እየተፈለገላቸው በሚከሰሱና በሚታሰሩ ዜጎች ምክንያት አገራችን ውስጥ በፍትሕ ላይ መተማመን ጠፍቷል፡፡ ኢሕአዴግ ይኼ ካላሳሰበው ሌላ ምን ያሳስበዋል? ሰዎች ያለጥፋታቸው ታስረው የቀረበባቸው ክስ የማያወላዳ በመሆኑ በነፃ ሲሰናበቱ አሁን መታየት ጀምሯል፡፡ የአንዳንዶችም ክስ ሲቋረጥም ተስተውሏል፡፡ ከመነሻው እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ተግባር ለምን ይፈጠራል? የፍትሕ ሥርዓቱስ ለምን ይሳጣል? ለሕግ የበላይነት ለምን ቅድሚያ አይሰጥም? ብዙ ማለት ይቻላል፡፡
ዜጎች በገዛ አገራቸው ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ዝም ይባላል፡፡ በአመለካከታቸው ምክንያት መደብደብ፣ መታሰር፣ መንገላታት፣ ከሥራ መባረር፣ የቤተሰብ መበተን፣ ወዘተ ሲደርስባቸውና ጩኸቱ ሲበረክት በተደጋጋሚ ተሰምቷል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው እንደተገደሉባቸው በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ በታዳጊ ዴሞክራሲ ውስጥ የሚያጋጥም ነው እየተባለ ዜጎች በገዛ አገራቸው ሲሰቃዩ እስከ መቼ ይቀጥላል? የመልካም አስተዳደር እጦት ምሬት ከዳር እስከ ዳር ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ሥራ መሥራት ያቃታቸው ሹማምንት የተመደቡበት ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ በመቅረታቸውና ለአገር ደንታ የሌላቸው ሹማምንት የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ሕዝብ ሲያስለቅሱ ዝምታው ምንድነው? ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ እነዚህን ችግሮች መፍታት ያቃተው ለምንድነው? ችግሮቹስ ለምን ይድበሰበሳሉ? በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡
የዴሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከርና በፍርኃት ቆፈን መያዝ፣ የሲቪል ማኅበረሰቡ ደብዛው መጥፋት፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ ደብዝዞ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት መንገሥ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ሕግ የማውጣትና አስፈጻሚውን የመቆጣጠር አቅም አለመጠንከር፣ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ መገናኛ ብዙኃን የገዥው ፓርቲ ብቻ አገልጋዮች መሆን፣ የግሉ ሚዲያ መፍረክረክ፣ ወዘተ ግልጽነትና ተጠያቂነትን እያጠፋ ነው፡፡ በየቦታው ትንንሽ አምባገነኖች እየተፈለፈሉ ነው፡፡ ለአገር አደጋ ነው፡፡
ሙሰኞች የአገር ሀብት እየዘረፉ ሲከብሩ ዞር ብሎ የሚያያቸው የለም፡፡ ጭራሽ በድርጅት አባልነት ከለላ፣ በሹማምንት ትውውቅና ኔትወርክ ዕውቅና የተሰጠው ሙስና ግለሰቦችን በቀናት ውስጥ ሚሊየነር ሲያደርግ ዝም ይባላል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ የለም እንዳይባል ያህል እዚህም እዚያም በአለፍ ገደም አንዳንድ የሚጠየቁ ግለሰቦች ቢኖሩም፣ ሙስና የሥርዓቱ መግለጫ እስኪመስል ከተራ ዜጋ እስከ ውጭ ኢንቨስተር ድረስ የምሬት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ በሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ በሕንፃ ግንባታና ዕድሳት ፈቃድ፣ በወጪና ገቢ ንግድ የጉምሩክ ኬላዎች፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በአነስተኛና በትልልቅ ግዢዎችና ጨረታ፣ በንግድ ፈቃድ ምዝገባና በብቃት ማረጋገጫ፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ምዝበራ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርፊያ፣ በኤሌክትሪክ፣ በውኃና በስልክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ በመንገድ ግንባታዎችና በመሳሰሉት አገሪቱንም ሕዝቡንም ራቁታቸውን የሚያስቀሩ የሙስና ተግባራት እየተፈጸሙ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ሆይ የት ይሆን ያለኸው? አባላትህና ደጋፊዎችህ ምን እያደረጉ ነው? የምዝበራው ተሳታፊ ወይስ የዳር ተመልካች? ይኼም በደንብ ይፈተሽ፡፡ ራስህን ተመልከት፡
አገሪቱ ከነበረችበት የድህነት አረንቋ ውስጥ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ መስዋዕትነት እየከፈለበት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ አሁንም በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመታ ነው፡፡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በየቀኑ ዋጋቸው እየጨመረ ኑሮን መቋቋም ተስኖታል፡፡ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅም በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ከሚቋቋመው በላይ ነው፡፡ በትራንስፖርት እጦት በፀሐይና በዝናብ ይንገላታል፡፡ ፈረቃ በይፋ ያልታወጀላቸው ኤሌክትሪክና ውኃ ለቀናት እየጠፉበት ይሰቃያል፡፡ ይህንን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ አገሩን የሚገነባ ሕዝብ እንዴት ነው ድጋፍ ማግኘት ያለበት? በስሙ በድጎማ የሚመጡትን ዘይትና ስንዴ በጥቅም የተሳሰሩ ሌቦችና ደላሎች አየር በአየር ይሸጡበታል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ እጅግ በጣም ኋላቀርና ተቆጣጣሪ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሕዝቡን በቁሙ እየገደለው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እስከ መቼ ጆሮ ዳባ ልበስ ይላል? አስቸኳይ መፍትሔ ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት፡፡
ዜጎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያቀርቡዋቸው አቤቱታዎችና ብሶቶች አይደመጡም፡፡ ቅሬታዎች በአግባቡ አይስተናገዱም፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ጥድፊያው ለማድበስበስ እንጂ መፍትሔ ለመፈለግ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ስኬቱን እያወደሱ የሚያሞካሹትን ጆሮውን ሰጥቶ የሚያዳምጠውን ያህል ለምን ተቃውሞዎችን፣ ምክሮችንና ቅሬታዎችን ለማዳመጥ አይተጋም? በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ከነአጋሮቹ ያገኘው መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን እንጂ፣ መቶ በመቶ የሕዝቡን ይሁንታ አይደለም፡፡ ካገኘው የሕዝብ ድጋፍ ጋር ባይወዳደርም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ይቃወሙታል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኢሕአዴግ በውስጡ ከሕግ በላይ የሆኑ ግለሰቦችን በመያዙ፣ አድርባዮችና ሌቦችን በማቀፉ፣ ፀረ ዴሞክራሲና አምባገነን በህሪያት ይንፀባረቁበታል በሚል ነው፡፡ ይኼም በተደጋጋሚ ተተችቶበታል፡፡ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ እየተገፉና ዕድገት እየተከለከሉ ወረበሎች አገር እየበደሉ ነው፡፡ ኢሕአዴግንም እያስተቹት ነው፡፡ ይኼም መፍትሔ ይፈልጋል፡፡
ኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ሲያካሂድ ወሳኝ የሆነ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጨክኖ መወሰን አለበት፡፡ ፀረ ዴሞክራቲክ ተግባራት ይወገዱ፡፡ የተዘጋጋው የፖለቲካ ምኅዳር ይከፈት፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት ይንቀሳቀሱ፡፡ ጦር አንስተው የሚፎክሩ ኃይሎች ሳይቀሩ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉ እንዲመለሱ ሁኔታዎች ይመቻቹ፡፡ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ የሚፈነጭባት አገር እንዳትሆን የሕግ የበላይነት በተግባር ይረጋገጥ፡፡ ሙሰኞችና ሌቦች ለሕግ ይቅረቡ፡፡ ብቃት የሌላቸው ይሰናበቱ፡፡ አቅም ያላቸው ለሹመት ይታጩ፡፡ ሕዝቡን ደስ የሚያሰኙ ተግባራት ይከናወኑ፡፡ አስመሳዮችና አድርባዮች ይወገዱ፡፡ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የነፃነትና የብልፅግና አገር ትሁን፡፡ ኢሕአዴግም ራሱን ይመልከት!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46125#sthash.ORsIe1j6.dpuf

Sport: ኢትዮጵያዊያኑ 3 አትሌቶች በቤጂንጉ የ5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ላይ ይሳተፋሉ

The men's 5000m heats at the IAAF World Championships, Beijing 2015 (Getty Images) © Copyrightበሙለታ ንገሻ በ15ኛው የቤጂንግ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በሶስት አትሌቶች ትወከላለች። ሌሊት 10 ስአት ከ35 ላይ በተደረገ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሀጎስ ገብረ ህይወትና ኢማና መርጋ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል። ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጎስ ገብረ ህይወት ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን፥ ኢማና መርጋ አምስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ነው ያለፈው። አትሌት ዮሚፍ ቀጄልጃ ውድድሩን 13:19.38. በሆነ ሰዓት የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ የነበረውን ሞህ ፋራህን ቀድሞ በመግባት የማጣሪያ ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩ ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን፥ 10 ስዓት ላይ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ፥ አትሌት ህይወት አያሌውና ሶፊያ አሰፋ ኢትዮጵያን ከዚህ ያልተለመደ የውጤት ማሽቆልቆል ይታደጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገ ሌሊት 10 ስአት ከ40 ላይ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ፣ አልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ጎይቶም ገብረ ስላሴ ይወዳደራሉ። በዚሁ ቀን ሌሊት 11 ከ35 በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ አማን ወጤ፣ ዳዊት ወልዴ እና መኮንን ገብረ መድህን ይሳተፋሉ። እሁድ ነሃሴ 24 2007 ዓ.ም 8 ስአት ከ30 ሌሊት በሴቶች ማራቶን ትርፌ ፀጋዬ፣ ማሬ ዲባባ እና ትእግስት ቱፋ የሚወዳደሩ ሲሆን፥ ቀን 8 ስአት ከ15 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር፤ 8 ስአት ከ45 ላይ ደግሞ የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ይከናወናሉ። ትናንት በተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ በ4 ደቂቃ 08:09 ሰከንድ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማስገኘቷ ይታወሳል። በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን 1 የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአለም 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ገንዘቤ ዲባባ፣ በወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ እንዲሁም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ገለቴ ቡርቃ ናቸው ሜዳልያዎቹን ያስገኙት። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች በወንዶች ውድድር ድል የራቃት ኢትዮጵያ፥ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከሜዳልያ ውጪ ሆናለች። ኢትዮጵያ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ያልሆነችበት 15ኛው የቤጂንግ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአንፃሩ ለኬንያውያን ስኬታማ ነው ማለት ይቻላል። ኬንያ እስካሁን 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ ሜዳልያዎችን በማግኘት ከአለም ሀገራት በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ብሪታንያ በ3 ወርቅ በ2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ጃማይካ በ2 ወርቅ እና በ1 ነሃስ በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46193#sthash.fSZPgGXF.dpuf

የ “ሀ” ን ዘር የ “ከ” ዘር እያጠፋው ነው:: – ይገርማል ታሪኩ

በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ አልፎ ተርፎም ቀጥተኛ ግድያ አማሮች እያለቁ ቁጥራቸውም እየተመናመነ በመሄድ ላይ መሆኑን ሁሉም ያውቃል:: የአማራ ዘር ብቻ ሳይሆን የአማራ ባህል: ቅርስና ትውፊት ናቸው ተብለው በሚታመኑት የረጅም ጊዜ የታሪክና የእምነት አሻራወቻችን ላይም የማጽዳት እርምጃ በተለያየ መንገድ እየተወሰደ ነው:: ዛሬ አማራንና ኦርቶዶክስ ሀይማኖትን ለያይተው ማየት የተሳናቸው ግብዞች ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማራው የፈጠረውና የአማራ መሸሸጊያ እንደሆነ አድርገው በመስበክ: ቤተክርስቲያናቱን 


Amharic2

በማቃጠል: መጽሀፍቱንና የአምልኮ መገልገያ መሳሪያወችን ባህር እያሻገሩ በመሸጥ: ቤተክርስቲያን በነጻነት መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳትሰጥ ካድሬወችን በመሰግሰግ የወያኔ ጉዳይ ፈጻሚ በማድረግ: ጊዜ የማይሽረው በደል እየፈጸሙ ነው:: እንደሚታወቀው የአማራ ክልል የሚተዳደረው በዋናነት አማራ ሳይሆኑ አማራ ናቸው ተብለው በተቀመጡ የሌላ ብሄርና የሌላ ሀገር ሰወች ነው:: ከታች የተኮለኮለው አማራ ነኝ ባይ የአህያ ባል ሆኖ የመጣውን እየተቀበለ አድርግ የተባለውን እያደረገ የሚኖር ስለክልሉም ሆነ ስለ ህዝቡ የማይጨነቅ ለከርሱ ብቻ የቆመ ተራ ስብስብ ነው:: ቀደምት አማሮች በአራቱም ማእዘን በመዝመት አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍስሰው በየትኛውም የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ያልታየ ገድል በመፈጸም በምስራቅ ከጣሊያኖችና ከፈረንሳዮች በደቡብና በምዕራብ ከእንግሊዞች ጋር ድንበር ተካለው ኢትዮጵያን ለእኛ አስረክበዋል:: ያ ባይሆን ኖሮ ዛሬ ላይ በምስራቅ ያለው ኢትዮጵያዊ ከፊሉ ከጅቡቲ ቀሪው ደግሞ ከሶማሊያ ጋር: በደቡብ ያለው ኢትዮጵያዊ ከኬንያ ጋር: የሰሜኑ ከኤርትራ የምእራቡ ደግሞ ከሱዳን ጋር የመሆንና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በታሪክ ብቻ የምትታወስ ሆና በቀረች ነበር:: የአፍሪካም ሆነ የኤዥያ ሀገሮች እንደሀገር የቆሙት በቅኝ ግዛት ጊዜ በነበራቸው አብሮነት መሰረት በመሆኑ በተለያዩ አገሮች በቅኝ ግዛትነት ተይዘው የቆዩት አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ተበታትነው በተለያዩ ሀገሮች የመኖር እጣ ደርሶባቸዋል:: እኛ ግን አያት ቅድመአያቶቻችን ባደረጉት የመረረ ተጋድሎ ረጅም ታሪክ ያላት ጥንታዊቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥቁር ዘር የነጻነት ፋና የልጆቿ መመኪያ በመሆን ከዘመን ዘመን ተሻግራ ለእኛ ተላለፈች:: ዛሬ ባለጊዜ ወያኔወች እንደፈለጋቸው የሚያደርጓት: ብዙሀኑም ፍዳ የሚያይባት: “ኢትዮጵያ” የምትባል ሁላችንንም ሰብስባ የያዘችዋ ሀገር ነጻነቷን አስጠብቃ ለእኛ እንድትደርስ የተከፈለው ደምና አጥንት ከ-እስከ የሚባል አይደለም:: ታዲያ እነዚያ ጠላት አይደፍረንም ብለው በቀዳሚነት ደምና አጥንት የከፈሉት ኢትዮጵያውያን ልጆች ዛሬ ላይ ራሳቸውን እንኳ ማስከበር አቅቷቸው በመጥፎ መንፈስ በተሞሉ የወያኔ ተኩላወች ፊታውራሪነት ለፈርጀ ብዙ ጥቃት ተጋልጠው ያለ አለሁ ባይ በየአካባቢው እየወደቁ ነው:: ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ተጣመው የተፈጠሩና ነፍስ ያላወቁ ከራሱ ከአማራው አብራክ የተገኙ ጥቂት ጉዶች ለወያኔ አድረው የጠላት መሳሪያ በመሆን እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ከአዋራጆቹ ጋር ተስማምተው እያዋረዱት: ከአሳዳጆቹ ጋር እያሳደዱት: ከገዳዮቹ ጋር ተባብረው እየገደሉት በወገናቸው ላይ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ ሳይጎረብጣቸው በድርጊታቸው ተኩራርተውና ረክተው መቀጠላቸው ነው:: በአማራው ላይ የሚደርሰውን ሁለንተናዊ ግፍ የሚቃወሙትን ፈጥነው በማጥፋት “ጎሽ” ለመባል የሚተጉት እኒህ ትንሽየ እንኳ እንጥፍጣፊ ህሊና የሌላቸው እፍኝ የማይሞሉ የእንግዴ ልጆች ያማራውን ክልል ለማስከበርና የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት ሲገባቸው መሬቱን በውጪ ለሱዳን: በውስጥ ደግሞ ለተለያዩ ክልሎች እያስቦጠቦጡ ከጊዜ ወደጊዜ መኖሪያውን እያጠበቡ ተስፋውን እያጨለሙበት ነው:: በየዳር ድንበሩ በውትድርና ዘምቶ በዚያው ሀገሬ ብሎ ከአካባቢው ህዝብ ጋር ተጋብቶና ተዋልዶ ለረጅም ጊዜ በኖረው ህዝብ ላይ የወያኔ የጥላቻ በትር ሲያርፍበት ለምን ብሎ እንደመከራከርና መብቱን እንደማስከበር “ከክልሉ የወጣ አማራ ጉዳይ አይመለከተንም” በማለት ወገኖቻችን በየሄዱበት ወድቀው እንዲቀሩ ድጋፋቸውን አበረከቱ:: እኒህ ከወያኔ ጉያ ተወሽቀው በሚያገኙት ዳረጎትና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ዘግናኝ ግፍ ተደስተው ሰላም አግኝተው የሚኖሩ የብአዴን ሰዎች የሚቆጭ ህሊና የሌላቸው ለሆዳቸው ብቻ የተፈጠሩ ትናንሽ ሰወች ለመሆናቸው ተግባራቸው ይመሰክራል:: በመሆኑም አማራው በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ እንደዜጋ መብቱ ተከብሮ ለመኖር ያልቻለ: በስውርና በግልጽ ደባ ቁጥሩ የተመናመነ: በቤተሰብ እቅድ ስም በርሱ ላይ ብቻ ያተኮረ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበት ሆኗል:: የዚያ ታሪክ ሰሪ ህዝብ ልጆች ራሳቸውን መከላከል ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ወድቀው ያም ያም እንደፈለገው የሚያደርጋቸው እርካሾች ሆነው ሲታዩ እንዴት ያማል:: ወደርዕሴ ስመለስ.:- በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአሁኑ ትውልድ የሀን ዘር በከ ዘር በመተካት የሀን ፊደል ከፊደል ገበታ ለመሰረዝ በጉዞ ላይ ነው:: ፊደሎችን ካለወህል መጠቀም እንዴት ያስቀይማል! በተለይ ይህን የሚያደርጉት የስነጥበብ ሰዎች ሲሆኑ ደግሞ ከማስቀየም አልፎ ህመሙ ይጠዘጥዛል:: ጥሩ የታሪክ አወቃቀርና ፍሰት ያለው ድራማ/ፊልም ላይ ፊደላት ያለቦታቸው ሲገቡ ለሰሚ ይቀፋሉ: ታሪኩንም ያደበዝዛሉ:: አንድ ወይም አንዲት የአርት ሰው መሰረታዊውን የቃላት አወቃቀር በመቀየር እንዴት ነክ: እኔ እምልክ: የት ነክ: ወዘተ እያለ/እያለች ሲናገር/ስትናገር ለሰማ ጆሮን “ኩ-ር

 የአሁን ምን አደረግሁ                                             ምን አደረኩ ማን ነህ                                                     ማን ነክ የት ነህ                                                     የት ነክ እኔ       የምልህ                                              እኔ የምልክ ታምራለህ                                                  ታምራለክ ተውበሀል                                       ተውበካል          አምሮብሃል                               አምሮብካል …….   

                                                    ——— በአንድ ወቅት ት/ቤት እያለሁ አንድ መምህር የተናገሩት ምን ጊዜም አይረሳኝም:: አንድ ተማሪ should የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል “ሹልድ” እያለ ሲያነብ ሰምተው በጣም ተቆጡና “ስማ! አንተ ሹድ ተብለህ ተምረህ ሹልድ እያልህ መጣህ የአንተ ልጆች ደግሞ ሹልዳ እያሉ ይመጣሉ” ተከታዩ ትውልድስ የቱን የአማረኛ ፊደል ይገድፍ ይሆን! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46198#sthash.AcpwdVeu.dpuf

Tuesday, August 25, 2015

Sport: ገንዘቤ ዲባባ ያሸነፈችው በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ ፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46176#sthash.E51VwfPV.dpuf


BEIJING, CHINA - AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women's 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)
BEIJING, CHINA – AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women’s 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                (ኢብራሂም ሻፊ)
ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ድልን ተጎናፅፋ የኢትዮጵያ ህዝብ ኩራት ትሁን እንጂ ቤይጂንግ ከመምጣቷ በፊት የተቀናጀ የስም ማጥፋት ሲካሄድባት እና የተለያዩ ውሃ የማይቋጥሩ ክሶች ሲቀርቡባት የከረመች አትሌት ናት፡፡ የዚህ የተቀናጀ የስም ማጥፋት እና ክስ አቀናባሪ ደግሞ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ (በዋናነት ዱቤ ጅሎ) ነበር፡፡ የቱታ እና ስኒከር ጫማ እርጥባን የሚጥልላቸው አንዳንድ “ጋዜጠኞች” ደግሞ የስም ማጥፋቱ እና የክስ ማርቀቁ ተባባሪዎቹ ነበሩ፡፡
ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆናለች ተብላ ተከሳለች፡፡ አዎን በእርግጥም ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ሮጣለች፡፡ ሞናኮ ላይ የዓለም 1500 ሜትር ሪከርድ ያሻሻለችው አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ሳይፈቅድላት ነው፡፡ እዚህ ላይ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ “አትሩጡ” ቢልም ለምን አትሩጡ እንዳለ አጥጋቢ ምክንያት አልነበረውም፡፡ የቱታ እና ስኒከር እርጥባን ተቀባዮችን “ጋዜጠኞች” ምክንያትን ሰምተን የፌዴሬሽኑ ምክንያት ነው ካልን “ፋቲግ” (ድካም) እንደ ሰበብ ቀርቦ ነበር፡፡ እግዜር ያሳያችሁ ሞናኮ ላይ የዳይመንድ ሊግ ውድድሩ የተደረገው ጁላይ 17/2015 ነበር፡፡ ድካም እንደ ሰበብ የቀረበው ኦገስት 22/2015 ለሚደረግ ውድድር ነው፡፡ አንድ ውድድር ከወር በላይ ቀርቶት ገንዘቤን “አትወዳዳሪ……ትደክሚያለሽ” ማለት ምን ዓይነት ሙያዊ ውሳኔ ነው? አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ይሄን ሰበብ አድርጎ በዓለም ቻምፒዮንሺፑ 1500 ሜትር እንደማትሮጥ አሳውቆ ነበር፡፡ ገንዘቤ የግድ እንደምትሮጥ ስታሳውቅም ያደራጃቸውን ጋዜጠኞች ተጠቅሞ “ፋቲግ…..ፋቲግ……..” እያለ ውርድ ከራሴ የሚመስል አይነት ማስታወቂያም ሲሰራ ሰንብቷል፡፡ በጣም የሚገርመው አሁን የዓለም ቻምፒየንሺፑን ድሎች እየተቆጣጠሩ የሚገኙት ከሞናኮ በኋላ በለንደን ጁላይ 24/25 (ሁለት ቀናት) አሸናፊ የነበሩ አትሌቶች ናቸው፡፡ ሞ ፋራህ፣ ዩሴን ቦልት እና ዳቪድ ሩዲሺያ ለዚህ እንደማስረጃ መነሳት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ከገንዘቤ በኋላ ዳይመንድ ሊግ ለሮጡ የውጪ ሀገር ሯጮች “ፋቲግ” ሲሉ አትሰሙም፡፡ የእነርሱ እኮ ርቀቱ አጭር ነው የሚል ሰበብ እንዳይቀርብ ደግሞ ሞ ፋራህ ለንደን ዳይመንድ ሊግ የሮጠው 3000 ሜትር ነው፡፡ ይኽን ርቀት 7፡34.66 ፉት ብሎት ኦገስት 22/2015 የዓለም 10000 ሜትር ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ የ5000 ሜትር ውድድሩን በድል ለመወጣትም ቀናት እየተጠባበቀ ነው፡፡ “ፋቲግ” የሚለው ቃል ሞ ላይ አይሰራም ገንዘቤ ላይ ግን ይደሰኮራል፡፡
ገንዘቤ ከጓደኞቿ (ኢትዮጵያዊያን ሌሎች አትሌቶች) ጋር አልተለማመደችም ተብላ ተከሳለች፡፡ እኔ ደግሞ ይኽች ዕፁብ አትሌት ለምን ብቁ ባልሆነ አሰልጣኝ ትሰለጥናለች? ለምን ከብቃቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ተቀባይነቱን በሚያስቀድም አሰልጣኝ ትሰራለች? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ገንዘቤ በሞስኮው የዓለም ቻምፒዮንሺፕስ 1500 ሜትርን ተወዳድራ ስምንተኛ ከወጣች ወዲህ የወሰነችው ምርጡ ውሳኔ ከታታሪው አሰልጣኝ ጃማ አደን ጋር መስሯቷ እና የልምምዷን አጠቃላይ መልክ መቀየሯ ነው፡፡ ጃማ አደን ሱዳናዊውን አቡበክር ካኪን (800 ሜትር) የዓለም ሻምፒዮን እንዲሁም ፤ አልጄሪያዊውን ቶውፊቅ ማክሉፊን (1500 ሜትር) የኦሊምፒክ አሸናፊ ማድረግ የቻሉ ድንቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮን ከገንዘቤ በተጨማሪ ሙሳብ ባላ (800 ሜትር) እና አያልነህ ሱሌይማንን (1500 ሜትር) የመሳሰሉ ምርጥ አትሌቶችን የሚመሩ ምርጥ አሰልጣኝ ናቸው፡፡
ገንዘቤ በእርሳቸው መሰልጠን ከጀመረች በኋላ ከቤት ውስጥ ውድድሮች አሸናፊነት ወደ ሁሉም መስክ አሸናፊነት ቀይረዋታል፡፡ የ2015 አንዳንድ ድሎቿን ብንመለከት ይሄን ይመሰክራሉ፡፡ ዩጂን፣ ኦስሎ እና ፓሪስ ላይ የተደረጉ ተከታታይ የ5000 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ልዕልቷ ሳትቸገር አሸንፋቸዋለች፡፡ ሞናኮ ላይ እርሷ የአንድ ዓመት ህፃን ሳለች (ከ22 ዓመታት በፊት የተመዘገበ) በቻይናዊቷ ኩ ዩንዢያ የተያዘውን 1500 ሜትር ሪከርድ ሰብራለች፡፡ ከ2014 ጀምራ 1500፣ 3000 እና 5000 ላይ የተፎካከሯትን በሙሉ ረታለች፡፡ ታዲያ ይህን ድል እንድታስመዘግብ የረዳት አሰልጣኝን ጥላ ስራውን ከፖለቲካ ፓርቲ በተሰጠው መታወቂያ ወደሚያፀድቅ አሰልጣኝ ለምን ትጓዛለች?

ገንዘቤ የዛሬውን እና መጪዎቹን ድልሽን ለእልፍ ዓመታት ስንዘክረው እንከርማለን፡፡ ዛሬ ኬንያውያን እና ሆላንዳዊያንን ጭምር አላሸነፍሽም፡፡ በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ፣ ፍርደ ገምድልነት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ውሳኔን፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ አሸንፈሻል፡፡ በድጋሚ እንኳን ደስ ያለሽ ገንዘቤ……….!!!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46176#sthash.E51VwfPV.dpufBEIJING, CHINA - AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women's 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)

የሕወሓት ሊቀመንበርነት ሽኩቻ እየተደረገበት ይገኛል




Arkebe Equbay - Ethiopia


አምዶም ገብረስላሴ እንደዘገበው የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል። እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው። “ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል። ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል። ኣባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ ኣዳራሽ እንዳይ ገባ ኣድርገዋል። እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል። ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ ኣውጡ። በስብሰባው ኣንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። ኣለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ ኣስገኝቶለታል። ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል። የመቐለ ከሓወልቲ እስከ ኣክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ ኣሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46166#sthash.HKTdT89f.dpuf

በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

ከኤልያስ ገብሩ ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በዛሬው ዕለት ማረሚያ ቤቱ ላይ ክስ መቅረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ፍርድ ቤቱ፣ በክሱ ከተራ ቁጥር 2-5 እና 7ኛ ተከሳሽ ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመፍቻ ትዕዛዙን በ15/12/2007 ዓ.ም ለማረሚያ ቤቱ ቢደርስም ተከሳሾቹ እስከአሁን ድረስ ከእስር ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡ በመሆኑም ‹‹ፍርድ ቤቱ ይህንን ባደረጉ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ተከሳሾቹን እንዲለቅ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ›› ሲሉ ለ2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው እና ለ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ገ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ትዕዛዙን ለሰጠው ችሎት ክሳቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በነጻ ካሰናበታቸው ተከሳሾች መካከል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት በመድፈር ወንጀል ሁለት ጊዜ ያህል መቀጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ሕግ በአምስቱም ተከሳሾች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከእስር እንዳይፈቱ ዕግድ አቅርቦ ነበር፡፡ እንዲሁም የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46171#sthash.SoMvs0NO.dpuf

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46155#sthash.h1dmJLqQ.dpuf

እየተላኩት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የሞቱት ልጆቻችን ና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓ


ethiopia-millitary-in-somalia-300x200


ማይነግረን በመሰረቱ ልጆቻችን ወደ ሶማልያ አገር ሂደው እንዲያልቁ የሚደረገውስ ለምን ዓላማ ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ግልፅ በሆነ መንገድ መነገር አለበት በማለት ጥያቂያቸውን እያቀረቡ መሆናቸው ተገለጸ። ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ባለስልጣን አልሸባብን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ከሃያላን መንግስታት የሚያገኙትን ዶላር ለመሰብሰብ ካልሆነ ከአገሩ ውጭ እየሄደ ህይወቱን እያጣ ላለው ወጣትና ቤተሰቦቹ ግን ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌላቸው የሟቾች ቤተሰብና አንዳንዱ የአገራችን ምሁራኖች አስተያየታቸው እየሰጡ መሆናቸው አስታውቋል። በተመሳሳይ አንድ በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ተምቤን ዓብይ ዓዲ ውስጥ የሚኖሩ ወላጅ ልጃቸው በሶማልያ ሃገር ሄዶ መሞቱ ለምን አላማ ሲባል ነው ብለው መጠየቃቸው ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46155#sthash.7XYqNFci.dpuf

የጋሞን ሕዝብ በሚያንቋሽሸው መጽሐፍ የተነሳ የደቡብ ክልል አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46173#sthash.jhkmr369.dpuf




debub ethiopia 

አስፈጻሚዎች ሆነዋል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46173#sthash.jhkmr369.dpuf


ኢሳት ዜና :-በታደለ ቱፋ የተጻፈውን የጋሞን ህዝብ ማንነት የሚያንቋሽሸውን መጽሃፍ ፣ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩትየደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የገንዘብ ደጋፍ በማድረግ አስጽፈውታል በሚል ምክንያት ፣ በአርባምንጭና በተለያዩ የጋሞ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰለፎች መደረጋቸውን ተከትሎ፣ በከፍተኛ አመራሩ እና በታች አመራሩ መካከል ያለው አለመግባባት ይፋ ሆኗል።


debub ethiopia


 ለኢሳት የደረሰው የድምጽ ማስረጃ ከመጽሃፉ ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ኢሳት በአመራሩ መካካል ልዩነት መፈጠሩን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ የሚያረጋገጥ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ፣ የጋሞ ጎፋ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የደኢህዴን ባለስልጣናት እጃቸው አለበት በሚል የሚያናፍሱት ወሬ ትክክል አይደለም በማለት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጥፋታቸውን እንዲቀበሉ ጫና አድርገዋል። የወረዳ አመራሮች በተለይም የጨንጫ እና የአርባምንጭ የወረዳ አመራሮች ሂሳቸውን ወይም ጥፋታቸውን ለመቀበል ዝግጁ ካልሆኑ፣ የጥገኞች አስተሳሰብ አራማጆች ተብለው እንደሚፈረጁ በፕሬዚዳንቱ ተነግራቸዋል። የወረዳ አመራሮች ከመጽሃፉ ጋር በተያያዘ ” ህዝቡ ከአመራሩ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል” ቢሉም፣ የክልል መሪዎች ” ሊቀበሉት ፈቃደኞች አልሆኑም። ፕሬዚዳንቱ መጽሃፉን ደኢህዴን እንደላስጻፈውና እንዲያውም ሁሉም የድርጅቱ መሪዎች ደራሲውን ማውገዛቸውን ገልጸዋል። ምንም እንኳ ደራሲው ታስሮ በዋስ የተፈታ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡ ተመልሶ እንዲታሰርና ፍርድ ቤት የዋስትና መብቱን ጠብቆ የሚፈታው ቢሆን እንኳ፣ እርሳቸው እንደማይፈቱት በመናገር፣ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ከህግ በላይ ወይም ከፍርድ ቤት በላይ መሆናቸውን አስመስከረዋል፡፡ ይህ አንድ መጽሃፍ እርስ በርስ እንድንጠራጠርና እንዳንተማመን ካደረገን፣ እስከዛሬ አብረን የተጓዝነው ጉዞ የውሸት ነበር ያሉት መሪው፣ መጽሀፉ የድርጅቱን መዋቅር እንዲፈትሹ እና የደኢህዴንን የድርጅት ጥንካሬና በአመራሩ መካካል ያለውን መተማመንና መደጋገፍ እንደገና እንዲመረምሩ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ዶ/ር ካሱ ኢላላ ከአመራር ቦታ ላይ ሲነሱ ዶ/ር ሽፈራው ደግሞ ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት ተነሱ:: የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ደኢህዴን/ ጉባኤ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ በሕዝበ ሙስሊሙ ጠላት ናቸው የሚባሉትን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት አሰናብቶ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አድርጓቸዋል። ዶ/ር ካሱ ኢላላን በመተካካት ስም ሸኝቶአል፡፡ ጉባዔው 65 አባላት በማዕከላዊ ኮምቴ አባልነት የመረጠ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ዘጠኝ ያህሉ ማለትም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ ደሴ ዳልኬ ፣ ተስፋዬ በልጂጌ ፣ ሲራጅ ፈጌሳ ፣ ሬድዋን ሁሴን ፣ መኩሪያ ሀይሌ ፣ መለሰ አለሙ ፣ ተክለወልድ አጥናፉ እና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የድ


በሰቆጣ ከተማ ከፍተኛ የውሃ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለጹ

rain-water-harvesting1
ኢሳት ዜና :-በተያዘው ክረምት በአብዛኛው ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝእጥረት ተከትሎ የሰቆጣ ከተማና የአካባቢው ወንዞች በመድረቃቸው የውኃ እጥረቱ መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ነዋሪዎች ፣ በዝናቡ እጥረት የተነሳ የጉድጓድ ውሃ መጠን በማነሱ የሚጠጣ ውኃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
“በከተማዋ በአጠቃላይ የውኃ ችግር ተከስቷል፡፡በከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ ልማት ጽህፈት ቤት ምን እየሰራ እንደሆን አናውቅም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ የውሃ መስመሩ በየሳምንቱ ተበላሽቷል እንደሚባሉ ይናገራሉ፡፡ በየቤቱ የሚገኘው የቧንቧ መስመር አገልግሎት በመቋረጡ የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በመነሳት ወረፋ በመያዝ የገደል ውሃ ለመቅዳት መገደዳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በሌሊት ወጥተው እስከ ቀኑ አራት ሰዓት ድረስ አርፍደው ውሃ እንደሚያገኙ በምሬት ገልጸዋል፡፡
በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የውኃ ችግር እንዳለ የሚገልጹት ሌላው የከተማ ነዋሪ ከዝናቡ መጥፋት ጋር ተያይዞ የሚታይ ችግር መሆኑን ይናገራሉ፡፡በከተማው ውስጥ ለውስጥ የሚያቋርጡና በዙሪያው ያሉ ወንዞች መድረቅ ህብረተሰቡ ከወንዝ ቀድቶ መጠቀም እንዳይችል አድርጓል፡፡ዝናብ አንድ አንድ ጊዜ ሲዘንብ እንዲህ ያለ መጨናነቅ እንደማይከሰት የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢ አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ ከቆርቆሮ ላይ በመሰብሰብ የየዕለት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንደሚሞክሩ ይናገራሉ። ዝናብ በወር አንዴ ብቻ መዝነቡንና ከዚህ ውጭ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚቆይ ካፊያ ብቻ መሆኑ የውኃውን ችግር እንዳባባሰው ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ አስተድደር ከአሁን በፊት ውኃ በቦቲ በማቅረብ የህዝቡን ጊዜያዊ ችግር ለመቅረፍ ቢሞክርም፣ አሁን አገልግሎቱ በመቋረጡ የከተማው ህዝብ በችግር ላይ ነው፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚናገሩት በነሃሴ ወር ከአሁን በፊት እንደዚህ ዓይነት የውኃ ችግር ተከስቶ እንደማያውቅ ተናግረው፤አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ የደረቀውን መሬት ከማራስ አልፎ ወደ ከርሰ ምድር የሚዘልቅ ውኃ ባለመኖሩ ከመስከረም ወር በኋላ ከፍተኛ የውኃ ችግር ሊከሰት ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው አክለዋል።
የገዢው መንግስት አመራሮች ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠታቸው ህብረተሰቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መጋለጡን የሚገልጹት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ የጉድጓድ ውኃ ለመቅዳት በወረፋ ሰበብ ህዝቡ እርስ በርሱ ሲጣላ እና ቀኑን ሙሉ አንድ ጀሪካን ውኃ ለመቅዳት ተሰልፎ ስራ ሲፈታ በዝምታ ከማየት ሌላ የፈየዱልን የመፍትሄ ነገር የለም በማለት ይናገራሉ፡፡
ከአሁን በፊት ለሃያ አመታት ያገለግላል ተብሎ በከፍተኛ ወጪ የተሰራው የቧንቧ ውኃ ፣ ሶስት ዓመት ብቻ አገልግሎ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46152#sthash.pKhcACYR.dpuf

Thursday, August 20, 2015

በዋሽንግተን ዲሲ ብቻ 100 ሺህ ዶላር (ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ) ለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጣ

በዋሽንግተን ዲሲ ብቻ 100 ሺህ ዶላር (ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ) ለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጣ (ዘ-ሐበሻ) ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በስካይፒ ይዞ አቡነ ፊሊጶስ; ሙሉነህ እዩኤል እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት ለአርበኞች ግንቦት 7 በተካሄደ የገንዘብ ማሰባሰብ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ግራፍ በጨረታ $70 ሺህ ዶላር ተሸጠ:: በአጠቃላይ ገቢም ከ$100 ሺህ ዶላር በላይ ተዋጥቷል:: ይህም በኢትዮጵያ ምንዛሪ ሲሰላ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል:: ለአርበኞች ግንቦት 7 ማጠናከሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ በዳላስ እና በሲያትልም የተደረጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ይኸው ማሰባሰብ ይቀጥላል:: በዲሲ በተደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ ሕዝቡ ወርቁን ሁሉ እያወለቀ ሲሰጥ ነበር ተብሏል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45932#sthash.pQfcWz1q.dpuf


DC A

በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተደብቀው ሲሄዱ የተያዙ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ

ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው
በኬንያ መሩ ካውንቲ በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ አመሻሽ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ችለዋል፡፡

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45994#sthash.zey5Ff9d.dpuf

ethiopia
ኢትዮጵያዊያኑ የሚገኙበት የካንጌታ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ምርመራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ መናገራቸው ተወስቷል፡፡
በሚያዘያ ወር ከሁለት የተለያዩ ቤቶች ከኢስሊና ኪማኢኮ 40 ኢትዮጵያዊያን በፖሊሶች በተደረገ አሰሳ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡
እስረኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማምራት ወደ ኬንያ መግባታቸውን ከመናገር ውጪ ምንም አይነት የጉዞ ዶክመንት አለመያዛቸው ተስተውሏል፡፡
ስደተኞቹ በሁለት ቡድን ተከፋፍለው ወደ ሁለት ቤቶች እንዲያመሩ ከመደረጋቸው አስቀድሞ ወደ ኬንያ በአንድነት መግባባቸውን የተናገሩት ፖሊስ ኦፊሰሩ በርናርድ ኒያክዋካ ‹‹ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ተደርገው ነበር፡፡በዚህ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወኪሎቻቸውን በማፈላለግ ላይ እንገኛለን››ብለዋል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45994#sthash.zey5Ff9d.dpuf

በኢትዮጵያ ቆይታዬ ያነሳኋቸው ፎቶዎች – (ይናገራል ፎቶ)

የዘ-ሐበሻ አንባቢ የሆኑት ግለሰብ ኢትዮጵያ ሄጄ መመለሴ ነው ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የተመለከትኳቸው አሳዛኝ ሁኔታዎችን በፎቶ ግራፍ አንስቼያቸዋለሁ በማለት ፎቶዎቹን ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አድርሱልን ብለዋል:: በዚህም መሰረት ፎቶዎቹን “ይናገራል ፎቶ” በሚል አቅርበነዋል: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45979#sthash.gRG3PM0k.dpuf



ethiopia 1

በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46023#sthash.dQh0MHWD.dpuf

በዐማሮች ላይ የተፈፀመ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ዘገባ ቅፅ ፫፣ ቁጥር ፩ ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ለመስማትም ሆነ ለማውራት ይዘገንናል!! በምን ቋንቋ እንግለጸው! ሰውን ሰው በላው! ጉምዞች ዐማሮችን አርደው በሏቸው!
 ሀ) መግቢያ
 ሞረሽ-ወገኔ ይህ አስደንጋጭ ዜና እንደደረሰው የድርጊቱን ዘግናኝነት እና ፍፁም ኢሰብዓዊነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ ከዚያም አልፎ ያለአግባብ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን ላለመወንጀል፣ ስለሁኔታው ከሥር መሠረቱ መረጃዎችን ለማጣራት ሙከራ አድርጓል። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እና ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦች ሁሉ እንድትገነዘቡልን የምንፈልገው፣ በእንዲህ ዓይነት እጅግ የሚሠቀጥጥ ድርጊት ላይ ዘገባ ለማዘጋጀት ምን ያህል ከባድ የኅሊና ፈተና እንደሚደቅን ንፁሕ ኅሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ይስተዋል አልባልም።

Benishangul

አንዳንድ ጊዜ «ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ ያስቸግራል» ይባላል። ዕውነት ነው፣ እንደዚህ ያለ ለመስማትም ሆነ ለመናገርም የሚቀፍ እና የሚከብድን ድርጊት፣ ድርጊቱን ባየው ሰው፣ በተረዳው እና በገባው መልክ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ወገን ለመግለጽ ይቸገራል። የቋንቋ ሊቃውንቱም «ቋንቋ አንዳንድ ጊዜ ኃሣብን በትክክል አይገልጽም» የሚሉት እንደዚህ ያሉ ድርጊቶችን በአዕምሯቸው በተቀረጸው መንገድ በቃላት አሳክቶ ለመግለጽ ሲፈልጉ ተስማሚ ቃል ስለሚያጡ ነው። በዚህ በምንኖርበት በ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ያውም የክርስትና ኃይማኖትን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተቀብሎ በኖረ እንደ ኢትዮጵያ ባለ የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት በሆነ ሕዝብ መሃል፣ «ሰውን ሰው በላው፣» «ጉምዝ የተባለው ጎሣ አባሎች የዐማራውን ነገድ አባሎች በጠላትነት ስሜት ተነሳስተው ከወያኔ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት አርደው በሏቸው» የሚለውን ክፉ ዜና ላልሰሙና ላላወቁ ሰዎች ማስረዳት እጅግ ይከብዳል፣ ይቀፋል፣ በምን ቃላትም ለመግለጽ እንደሚቻል ያስቸግራል። ድርጊቱ ግን በአሳዛኝ መልኩ ተፈጽሟል። በዕውነትም አንበሣ፣ ጅብ ወይም ሌሎች ሥጋ-በል አራዊት በመሰሎቻቸው ላይ የማይፈጽሙትን ድርጊት፣ ሰው ፣ሰውን አርዶ በሚጥሚጣ አጣጥሞ ሲበላው ላየ ሰው፣ ለሌላ ወገኑ ለመግለጽ ቃላት ያጥረዋል። የአገላለጽ መንገዱም ይጠፋዋል፤ ይከብደዋል። «ሰው ሰውን በላው» ማለት ተራ አባባል ይሆናል፤ የተለመደ ተራ አጠቃቀም ይሆናል። በምን ቃል ቢገለጽ ነው ድርጊቱ «ትንግርት፣ ጉድ፣ እግዚኦ የፈጣሪ ያለህ» የሚያሰኘው! ይህ ነው እንግዲህ «አንዳንድ ጊዜ ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ አያስችልም» የሚባለው። የሰው ልጅ ከጅብ እና ከአንበሣ፤ በአጠቃላይ ሥጋ- በል ከሆኑ እንስሶች የከፋ አውሬ መሆኑ እንዴት ይገለጻል? - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46023#sthash.dQh0MHWD.dpuf

የፕሬዝደንት ኦባማ “ታሪካዊ ጉብኝት” አምባገነን አወዳሽ ወይንስ ዲሞክራሲ አጎልማሽ? – አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46043#sthash.8BkbIp1U.dpuf

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

                  ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

የዚህ ሃተታ ዓላማ የፕሬዝደንት ኦባማን ጉብኝት አግባብና ሚዛናዊ ባለው መንገድ ተንትኖ አሉታዊና አወንታዊ ገጽታወቹን ለአማርኛ ተናጋሪዎች ለማቅረብ፤ የወደፊቱ የኢትዮጱያ ህልውና አስተማማኝ ሆኖ፤ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት መከበር አለባቸውና የዲሞክራሳዊ አገዛዝ ምስረታ ሂደቶች ሕዝብን ማእከል ማድረግ አለባቸው የሚለው ብሂል ያገባናል የሚሉ ክፍሎች፤ ፈቃደኛነት ካላቸው፤ በጋራና በተናጠል ሊሰሯቸው የሚችሉትን የተወሰኑ መንደርደሪያ ሃሳቦች ለማቅረብ ነው። ባለፈው ሳምንት በድህረ ገጾች ላይ የተሰራጨው ተመሳሳይ ትችት ሆነ ተብሎ ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች፤ በተለይ ለአሜሪካ ሕዝብ ቀርቧል፤ ብዙ ጠቃሚና የተለመደው “ለምን ይኼ ተባለ፤ ለምን ይኼ አልተባለም” የሚሉ ትችቶች ተሰራጭተዋል። ሁለቱንም አስተናግዳለሁ። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46043#sthash.c9Q1Sj9r.dpuf

ሃብታሙ አያሌው; ዳንኤል ሺበሺ; አብርሃ ደስታ; የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46052#sthash.rjjiWQMe.dpuf

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ ወደ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡
በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎ
አቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡

Habtamu abrhayeshiwas daniel


በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46052#sthash.rjjiWQMe.dpuf

በአማራ ክልል አንዳንድ ዞኖች አርበኞች ግንቦት 7ንና ትህዴንን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ድብደባ እየደረሰባቸው ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46007#sthash.7AkV45Qu.dpuf



Arebegnoch Ginbot 7


በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ከፍተኛ ድብደባ እየደርሰባቸው መሆኑ ታወቀ። የደህሚት ድምጽ ደረሰኝ ባለው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ዜጎችን ከፌድራል የደህንነት መስሪያ ቤት የተላኩ ደህንነቶች ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶችን እየደገፋችሁ ወጣቶችንም ወደ አርበኞች ግንቦት 7ና ትህዴን እየላካችሁ ነው በሚል የሃሰት ውንጀላ እየደበደቡና እያስፈራሩ መሆኑን የገለፀው መረጃው እንደዋና መነሻነትም የኢሳትን ቴሌቪዥንና የተቃዋሚዎችን ሬዲዮ ስታዳምጡ ተገንታችኋል የሚል መሆኑን አስረድቷል። በክልሉ የአምባገነኑ መንግስት ተላላኪነት የሃሰት ውንጀላ ከደርሰባቸው መካከል በአዊ ዞን አንከሻ ጓጉሳና ጃዊ ወረዳዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ሰከላና ወምበርማ ወረዳዎች በሰሜን ወሎ ዞን መቄትና ዋድላ ወረዳዎች የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን እያሰቃዩ ናቸው: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46007#sthash.7AkV45Qu.dpuf

Saturday, August 15, 2015

የወለደችውን የ1 ወር ህጻን ልጅ ገደለች የተባለች ኢትዮጵያዊት በዱባይ ተያዘች



girum

ግሩም ተ/ሀይማኖት የተባበሩት አረብ ኤምሬት.. ሻርጃ ውስጥ የወለደችውን የአንድ ወር ህጻን ገድላ በኮርኒስና ኮንክሪት ውስጥ የደበቀችው ኢትዮጵያዊት መያዟን ካሊጅ ታይምስ ዘገበ። ጨካኝ…ባላት ኢትዮጵያዊት ላይ Mother kills love child and stuffs body in box በሚል ርዕስ ካልጅ ታይምስ ዘግባውን አቅርቧል። የኤማሬት ቤተሰቦች ጋር የምትሰራው ገዳይ..የገዳይ ፍቅረኛና ሌላ ሴትም በሻርጃ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ማክሰኞ ነው። (ሌሊት በመሆኑ የጻፍኩት ከትላንትና ወዲያ ማክሰኞ ብል ይቀላል) ፖሊስ በስጠው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ዝም ብሎ ሳይሆን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው በዲ ኤን ኤ ምርመራ ትክክለኛ እናት መሆኗን አረጋግጦ ነው። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45834#sthash.aPbMdOCY.dpuf

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በወረዳው አመራር ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች ሞቱ * አመራሩና ባለቤታቸው ቆስለዋል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45841#sthash.PGATYadL.dpuf


news

የደህሚት ድምጽ እንዘገበው በደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ወደ ወረዳው አመራሩ በተወረወረው ቦምብ ምክንያት 2 ልጆች መገደላቸው ተገለፀ። በአማራ ክልል፤ ደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በወረዳው አመራር በአቶ መሓመድ ረሽድ ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች መሞታቸውና ራሱና ባለቤቱም ጭምር ክፉኛ በመቁሰላቸው ምክንያት ደሴ ሆስፒታል እያተካሙ መሆናቸውና እስካሁን ድረስም ድርጊቱ የፈፀመው አካል እንዳልተያዘ ለማወቅ ተችሏል። በአሁኑ ግዜ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የስርዓቱ ባለስልጣናት በህዝቡ ላይ በሚያደርሱት ከፍተኛ ችግር ምክንያት ህዝቡ በአስተዳድሪዎቹ ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ይታወቃል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45841#sthash.PGATYadL.dpuf

አለምነህ ዋሴ ለምን ከራድዮ ፋና ከዜና መጽሔት መሪነት እንደተነሳ ይናገራል (የሚደመጥ) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45843#sthash.Hasl7VDg.dpuf

አለምነህ ዋሴ ለምን ከራድዮ ፋና ከዜና መጽሔት መሪነት እንደተነሳ ይናገራል (የሚደመጥ) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45843#sthash.tGhWg740.dpuf

የአፋር መስተዳደር አዲስ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሾመ

afar
አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:
በኢህኣደግ ሰርዓት እረጂም ዓመታት በክልል መሪነት በማገልገል ሪከርድ የሰበረው ብቼኛ ኣገልጋይ ኣቶ እስማዒል ዓሊ ሲሮ ባለፈው ምረጫ ለፈደራል ፐርላማ መወዳደራቸውን ተከትሎ ዛሬ ኣዲስ መሪ ተሾሟል።
ዛሬ የተሾሙት ኣቶ ኣዋል ዓርባ ዑንዴ ከምርጫው ቀደም ብሎ ከግብሪና እና ገጠር ልማት ቢሮ ወደ ምክትል ረዕሰ መስተዳደር በማምጣት የተሾሙ ሲሆን ኣሁን ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ የክልሉ ጊዜያዊ ፕረዝዳንት ሆኖው ይቆያሉ ተብሏል።
በኣሁኑ ወቅት በኣጣቃላይ በኢህዴግ መሪዎች ዉስጥ ያለውን ኣለመግባባትን ተከትሎ የኣፋር ክልል ካድረዎች ዉስጥም ክፍተኛ የሆነ ኣለመግባባት ኢየታየ ነው።
በነግራችን ላይ የኣፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኣብደፓ) በነገው ዕለት ጣቅላላ ጉባኤ ያድርጋል ትብሎ ይጠበቃል።
በዚህ በነገው ሰብሰባ የክልሉ ምክትል ፕርዝድንት፣ የክልሉ ምክሪቤት ኣፌጉባኤ እና የፓርቲ ኃላፊ ይምረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወትርዉም ብሆን የኣፋር ክልል መሪ የሚመረጠው በህወሃት ጣልቃ ገብነት ሲሆን ኣሁን በጊዜዊነት የተሾሙት ኣዋል ዓርባ በክልል መሪነት ይቀጥሉ ኣይቀጥሉ ኣይታወቂም።
ኢህአዴግ ህወሀት ባለፉት ሁለት ኣስርት ዓመታት የብሔር ብሔርሰቦችን መብት ኣክብሬያለሁ በሚል ሽፋን በኣፋር ህዝብ ላይ ያደርሰው በደሎች ኢንኳን ጉልቻ መቀያየርን ቀርቶ እራሱ ኢህአደግ ብቀየሪም ታሪክ ይቅር የማይለው የመግደል፣የማፋናቀል፣የማሰር እና በሃብታቸው እንዳይጠቀሙ በማድረግ የፈጸመው በድሎች በኣፋር ክልል የህወሀት ተቃዋሚዎች እንዲበረከቱ ምክንያት ሆነዋል።
በኣሁኑ ወቅት በኣፋር ክልል ወጣቶች ብዙ የትደራረበ ጥላጫ ለኢህአደግ መንግንስት እንዳላቸው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየግለጹ ሲሆን ለምሳሌ ያህል መንግስት በክልሉ ህዝብን በማፋናቀል እየሰራ ያለው ልማት ተብዮው በኣፋር ኣርብቶ ኣደሮች ህይዎት ላይ ያስከተለው ችግር ቀላል ኣይደለም።
እይዉነት ለመናገር የኣፋር ህዝብ ካሁን በፊት ባልፉት ሰርዓቶች በዚህ ሁኔታ ኣልራበም።
በተለይ በምስራቅ የክልሉ ኣክባቢ በኣዋሽ ወንዝ ዳር ይኖሩ የነበሩ ኣርብቶ ኣደሮች ተፈናቅለው መሬታቸው በሙሉ ለመንግስት የስኳር እርሻ ተከለዋል።
የዚህ ዉጤት እነሆ ዛሬ በህዝብ ላይ ክፊተኛ ረሃብ አስከትሎ የኣለም ኣቀፍ ሚዲያዎች መንጋገሪያ ሆኖ ይገኛል።
በኣፋር ክልል እየሞቱ ያሉት ከብቶች ብቻ ኣይደለም፣ ሰዎቹም እየሞቱ ነው።
ኢስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት በዱብቴ ወረዳ ፣ ዳትባሃሪ ኣከባቢ በራሃብ ና በጥም እንዲሁም የቆሸሸ ዉሃ ጠጥተው
የስምንት ህጻናት ህይዎት ኣልፈዋል።
በሚሌ፣ በኦንዳ ፎኦ አከባቢም ከብቶቻቸው ያለቁባቸው ነወሪዎች እራሳቸው ያጠፉ እንዳሉ ሰሚቼያለሁ።
ሌላው ድግሞ በሰሜን የክልሉ ኣከባቢ ከዳሎል ኢስከ ማጋሌ ወረዳ ያለው የትግራይ መሬት ነው በማለት ነዋሪዎችን በማጋጨት ብዙ ኣፋሮች በወያኔ ሚልሻዎች ተገድልዋል።
በባራህሌ ወረዳ የሚገኘው ኣሞሌ ጨው ለኣንድት የትግራይ ሃብታም ካልሰጠሁ በማለት የባራህሌ ወረዳ ኣፋሮችና ወያኔ ከተፋጠጡ ወራት ተቆጥረዋል።
በዳሉል ወረዳ ኣብዛኛው መሬት በዋያኔ ተጠቃሚነት ለውጭ ኣገር ድሪጅቶች የተሰጠ ሲሆን የቀረው መሬትም በቅርብ ለፖጣሽ ኣምራቶች ተሰጥቶ ህዝብ ገና ካሁን በኋላ ልፈናቀል መሆኑን የኣፋር ክልል የወያኔ ኣገልጋይ ተሰናባቹ እስማዕል አሊ ሲሮ ባለፈው ሳምንት በኢቢሲ በሰጡት መግለጫ የገለጹ ሲሆን ኣሁን በኣዲሱ በዳሉል ወረዳ ለፖጣሽ የተሰጠው መሬት ስፋቱ ከሶስት መቶ ሲልሳ ኣምስት በላይ ስከዌር ኪሎ ሚትር መሆኑን በካምፓኒው ዲህረ ገጽ ኣምቢበውለሁ።
ሌላውና ቀዳሚው የኣፋር ክልል የጨው ሃብት ባለበት የሆነችው ኣፍደራ ሲትሆን በኣፍደራ የጨው መሬት የለለው የወያኔ ባለስልጣን፣የወያኔ ጀነራል የለም።
ኢንዲሁም ባለፈው ሳምንት በኣስመራ ታስረዋል የተባለው የኤረትራ የጻጥታ ሀላፊ ( ሚነስተር ) በኣፍደራ የጨው መሬት ኣላቸው፣ የቀድሞው የትግራይ ክልል መሪ ኣቶ ፀጋይ በርሄን ጨምሮ ኢያንዳንዳቸው የህወሀት መሪዎች በኣፍደራ የጨው መሬት ኣላቸው።
ሌላው ዶቢ ዓስቦ ( የዶቢ ጨው ሲሆን ዶቢ የሚባለው በኣፋር ክልል ኢትዮጲያ ከጀቡቲ በሚያዋስን ቦታ ላይ የሚገኝ የጨው መሬት ነው።
ይህ መሬት ሙሉ በሙሉ የኣንድ ባለሃብት ሆኖ ይሚገኝ ሲሆን እርሱ ማሀመድ ሁመድ ይባላል።
በኣፋሮች ዶቢ ዓስማሀማድ በሚል ቅጽል ሲሙ ሲታወቅ በህወሀት የተለመደው ልማታዊ ባለሃብት የሚል ማዓረግ ተስጦታል።
ለነገሩ ልማታዊ ባለሃብት ማለት የወያኔ ደጋፊ የሆነ ባለሃብት ማለት ኣይደል ?
ትርጉሙ በተዘዋዋሪም ብሆን ይህ ብሆን ነው እንጂ ልማታዊማ ብሆን ሲንት ህዝብ በራሃብ ኢና በዉሃ ጥም እየሞተ እያየ እንዳላየ የሚያልፍ ሃብታም ልማታዊ ባለሃብት ሲባል ምን ትለውለህ ?
የብሔር ብሔረሰቦች መብት ኣስክብረናል በሚል ሽፋን የብሔር ብሔርስቦችን ባህሎች፣ሃይሞኖቶች፣ሃብቶችና ክርሶች እያጠፋና እዘረፈ ያለው ህወሀት በኣፋር ክልል ያለው እውነታ ግን ዜሮ ዜሮ ነው።
ለምሳሌ፦ በየኣጋጣሚው ባህላዊ ጨፈራ በተለቭዥን ከማሳየት የዘለለ የተከበረ መብት የለም ።
ኣራት ነጥብ

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45865#sthash.mI7RfWa2.dpuf

ከረዢም አመታት በፊት የተጀመረው የባህርዳር ሞጣ ብቸና መንገድ አሁንም ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ





Motta 2012 week1 044


-ከአመታት በፊት ተጀምሮ በማዝገም ላይ ያለው የባህርዳር ሞጣ ደጀን መንገድ አሁንም በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በትራንስፖት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የስምሪት ተተኪ የስራ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ባለሙያ እንደተናገሩት መንገዱ በተደጋጋሚ በመበላሸቱ እና ለረዢም ጊዜ ባለመሰራቱ ህብረተሰቡ መቸገሩን ገልጸው፤ለመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቶች ስራውን እንዲያጠናቅቁ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም ስራውን ለማጠናቀቅ አልቻሉም። ባለሙያው በተጨማሪ እንደተናገሩት የስራውን መጠናቀቅ ተከታትሎ ለማስፈጸም ሃላፊነቱን የወሰደው የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የህዝቡን ተደጋጋሚ ቅሬታ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ከአዲስ አበባ በቡሬ ባህርዳር አሁን የሚያገለግለው የአስፓልት መንገድ 565 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከአዲስ አበባ በሞጣ ባህርዳር ግን አንድ መቶ ኪሎ ሜትር የሚቀንስ በመሆኑ ነጋዴዎች የሸቀጥ ጭነታቸውን በሞጣ በኩል በመጫን በትራንስፖርት መቀነስ ምክንያት የሚኖረውን የኑሮ ውድነት በመጠኑ ለማገዝ የሚያስችል የንግድ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የሚችሉበትን ዕድል እንዳላገኙ ነጋዴዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ ከደጀን ብቸና በሚወስደው መንገድ ብቸና ከተማ አካባቢ የሚገኘው የሰዋ ወንዝ ድልድይ ባለፈው የክረምቱ ወራት ወቅት መሰበሩ በርካታ ችግሮችን እንዲያሳልፉ መገደዳቸውን የሚናገሩት የብቸና ከተማ ነዋሪዎች፣ የዚህ መስመር የአስፓልት መንገድ ለምን በተያዘለት ጊዜ እንደማይጠናቀቅ ሁሌም እንደሚገረሙ ተናግረዋል፡፡ ከደጀን ፈለገ ብርሃን ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ሳትኮን በሚባል ሃገር በቀል የመንገድ ስራ ተቋራጭ እየተከናወነ ቢገኝም የጥራቱ ጉዳይ አሳሳቢ ከመሆኑና በአካባቢው የተሰሩት ድልድዮች ከማነሳቸው የተነሳ በስራቸው ጎርፍ ማሳለፍ አቅቷቸው በላያቸው ላይ እየፈሰሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ከሁለት አመት በፊት ባደረጉት ገለጻ ከደጀን ፈለገ ብርሃን ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት በቶሎ እንደሚጠናቀቅ አስታውሰው፥ ከዘማ ወንዝ እስከ ባህርዳር ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክትም በ2006 ይጀመራል በማለት በነሃሴ ወር 2005 ዓ.ም ቃል ቢገቡም የመንገድ ስራው ፐሮጀክት በዚህ አመት ተጀምሮ በመጓተት ላይ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ፡፡ የሳትኮን ባለቤት አቶ ሳሙ ኤል ተኽላይ የሰራተኞችን ደመ ዎዝ ለወራት በመ ከልከልና በማ ሰቃየት፣የመ ኪ ና ክራይ በወቅቱ ባለመ ክፈልና ስራን በማጓተት በተደጋጋሚ ቢከሰሱም፣ ገዢ ው ፓ ርቲ ለሁሉም ፕሮጀክቶቻቸው ከለላ በመ ስጠት ከተጠ ያቂነት ነጻ ሲያደርጋቸው መ ቆየቱን ታዛቢዎ ች ይናገራሉ፡፡ ሳትኮን ኮንስትራክሽን በህውሃት መንግስት ታቅፈው በአዲስ አበባ በስፋት ከሚንቀሳቀሱ የህወሃት ደጋፊ የሪልስቴት ባለሃብቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በርካታ የግንባታ ስራዎችን ያለ ጨረታ ይወስዳል። አምባሳደር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ አካካየ ሪልስቴት፣ክንዴ ሃጎስ ሪልስቴት፣ ተክለብርሃን አምባዬ ሪልስቴት፣ ጊፍት ትሬዲንግ፣ ሲቲ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስብሃቱ እና ቤተሰቡ ትሬዲንግ ከህወሃት ጋር በቅርብ የሚሰሩ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ናቸው። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45883#sthash.TaaxBlzE.dpuf

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ለጋንቦ ወረዳ አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ የቪዲዪ ማስረጃ ደርሶናል (ቢቢኤን

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45886

“አንገነጠልም – ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው” – ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ (የሚደመጥ) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45891#sthash.yeuCYWBk.dpuf

“አንገነጠልም – ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው” – ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ (የሚደመጥ) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45891#sthash.yeuCYWBk.dpuf

Wednesday, August 12, 2015

ኦቦ ሌንጮ ለታ ተመላሽ ዲያስፖራ የመሆን መብቱ ለምን ተከለከለ?



lencho leta


ከአብሼ ገርባ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ ኦቦ ሌንጮ ያለኝ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ ጏዙን ጠቅልሎ ሀገር ቤት መግባቱ ይታወቃል:: ሆኖም በፍጥነት በመጣበት እግር ሀገሩን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ:: የሌንጮ ለታን መባረርና አሁን ያለውን የዲያስፖራ ጥሪ ስንመለከት የተለየ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እንደማይፈቀድና ዶላርና ቦዶ ሀሳብ ብቻ ይዞ መምጣት እንደሚቻል ነው:: አንድ የኦሮሞ ዲያስፖራ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በዚህ ሀገር ውስጥ አንድም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ብሎ በአንድ ቀን አዳር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመኖሩን ገምግሞ ምስክርነት መስጠት የሚችል ጭንቅላት ያለው ዲያስፖራንም ለማየት ችለናል:: ኢህአዴግ ፖለቲካውን መቶ በመቶ ዝግ በማድረግ ዶላሩን ብቻ አምጡ እያላቸው ነው:: ዋናው ቁልፉ ግን ሀገሪቱን አንቆ የያዘው የዶላር ችግር ሳይሆን ፖለቲካው ስለተቆለፈበት ነው:: በኔ ግምት የዲያስፖራ ዶላር አይደለም የአሜሪካ ዶላር ጠቅላላ ተሰብስቦ ቢመጣ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር እስካልተፈታ መፍትሄ ሊሆን አይችልም - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45638#sthash.05OcEyYk.dpuf

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

ማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !
==================================
* ህጻን የደፋረን የ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል ?
* ፍርዱ ቅጣት ነው? ወይስ ማበረታታት ?
* ህግ አውጭና አስፈጻሚ አካላት ወዴት ናችሁ?
* ወላጆቿ ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!”ይላሉ

የኢፊድሬ ህገ መንግሰት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል ። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል ! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል ። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም ። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር ዝርዝሩ ሰፋ ያለ ይሆናል ። ዳሩ ግን የህግ እውቀት ኖሮኝ ያንን ለመተንተን ባይዳዳኝም በህግ አስከባሪዎች ፍትህ እየጎደለ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል ዘልቆ ቢያመኝ እንደ ዜጋ በጎደለው ፍትህ ተቃውሞና በቅሬታየ ዙሪያ የዜጋ ድምጼን ማሰማት ግድ ብሎኛል …
ዛሬ ዛሬ የምንሰማው ሰው በሰው ላይ ቀርቶ በእንስሳ ላይ መፈጸም የሌለበትን ርክሰት የተጠናወተው ወንጀል ጀሯችን ሆኗል ። በተለይ በአቅመ ደካማ ህጻናት ታዳጊዎችና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እያደር መክፋቱ ጸሀይ የሞቀው እውነት ሆኗል። በዚህ ረገድ እየተኬደ ያለውን የከፋ ወንጀል ሳስበው ” ወደ የት እየሄድን ይሆን? ” እያልኩ ያስፈራኛል ! የአጉራ ዘለል አስገድዶ የመድፈር ወንጀለኞች መስፋፋት ፣ እያደር ውሎ አዳራችንና አብሮነታችን እንዳያጎድፈውም በአስፈሪ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ! ሴሰኛ ወንጀለኛ ሽምጥ ጋልቦ እዚህ ሲደርስ ወንጀሉን በጥብቅ ተከታትሎ የማያዳግም ቅጣት አርአያነት ያለው ውሳኔ ቢሰጥ ዛሬ እዚህ ባልተደረሰ ነበር ፣ ይህ አይፈጸምምና ፣ ይህ አልተደረገምና ዛሬ ውርደትን መከናነብ ግድ ብሎናል ። የተከናነብነው ውርደት ምክንያት የሆነን ወንጀልም ሊሰሙት ከሚችሉት በላይ ሰቅጣጭና የከበደ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ አይገድም !
ይህን ሁሉ የምለው በአንዲት የ4 ዓመት ከ6 ወር ብላቴና ተዳጊ ላይ የተፈጸመው ወንጀልና ተመጣጣኝ ያልሆነውን የፍርድ ውሳኔ ወደምቃዎምበት የማለዳ ወጌ የመረጃ ግብአት ለመዝለቅ ነው ! እንደኔ የፍትህ መዛባት ዘልቆ ያመማችሁ ተከተሉኝና ፍርዱን ስጡ … !
በያዝነው ሳምንት ማህበራዊ መገናኛ ድህረ ገጾችን ቀልብ የሳበው ጉዳይ መካከል የ4 ዓመት ከ6 ወሯ ታዳጊ መደፈርን ተከትሎ የተላለፈው ዜና የብዙዎቻችን ቀልብ ስቧል ። ለዚህ መሰሉ ዜና አዲስ ባይንሆንም ብላቴናዋ መደፈሯ ሳይሰማ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በመጨረሻ ው የፍርድ ውሳኔ ጋር ሰማን ፣ በውሳኔውም ደፋሪው የ4 ወር እስራት ቅጣት ፍርድ መሰጠቱን በአንድ ላይ ሲነገረን ማመን ከተቸገሩት መካከል አንዱ ነበርኩ። የጉዳዩን ጭብጥ ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ያገኘሁት መረጃ ይዠ የዜጋ ተቃውሞ ድምጼን በማለዳ ወጌ ላሰዳ ስውተረተር በድሬ ትዩብ ስሟን በመጥቀስ በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበ አንድ ዘገባ ለወጌ መረጃ ግብአትነት ተጠቅሜበታለሁ ። ትክክለኛ ስሟ ስለመሆኑ ግን ማረጋገጫ አላገኘሁም ። ስሟ ቢታወቅም መግለጹ አስፈላጊ ባለመሆኑ የድሬ ትዮብን ስም ተቀብየ እዘልቃለሁ ። ከዚሁ በተጨማሪ ሌላም ሌላ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጣራት ሞክሬ በእርግጥም ወንጀሉ ለመሰራቱና ፍርደ ገምድል ብይን የመሰጠቱ ሁነኛነት አረጋግጫለሁ !
የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚስረዱት ታዳጊዋን የ4 ዓመት ከ6 ወር ተዳጊዋን አሚራ ትባላለች ። ኑሮዋም አዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ እንደሆነ ተጠቁሟል። ደፈረ የተባለው አስነዋሪ ወንጀል ፈጻሚ የ25 ዓመት ጎረምሳ ነው። በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት የአሚራ ቤተሰቦቿ ቤት ጎን ተከራቶ ነበር አሉ ።
ከውሳኔው አስቀድሞ ተከሳሽ አሚራን ስለመድፈሩ ክስ ቀርቦበት ፣ ጉዳዩ በፖሊስ ቀርቦና ተጣርቶ ተከሳሽ ተይዞ በፊዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ችሎት የቀረበ ሲሆን በ30 ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቀ። ክሱን በዋስ ወጥቶ እንዲከላከል በፊዴራድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ያ ከሆነ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ተከሳሽ ለብይን ቀረበ ። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የቀረበለትም ምርመራ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ” ተከሳሽ ድንግልናዋን ባይገስም በእጆቹ የማህጸኗ ግድግዳ የመሰንጠቅና የመላላጥ ጉዳትና ማድረሱና በማህጸኗ የመቅላት ምልክት በመታየቱ !” በሚል ማስረጃ ፍርድ ቤተ ተከሳሽን ” ሞከርክ ” በሚል ወንጀለኛ ሲል የ4 ወር እስራትን አስተላልፎበታል ። ይህው ፍርድ ቤት ገና የትምህርት ገበታ ያልቀመጠችን ታዳጊ ብላቴና አመራን የደፈረበትን የጨካኝ ድርጊት ከደፈረ ሞከረ ቀይሮ በቀረበ ማስረጃ በፍትሀ ብሔር ህግ 6264 ሀ መሰረት ውሳኔ መሰጠቱ ተነግሮናል ። አስገራሚ ፣ አስደንጋጭና አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ !
ክሱን አቀለለ ወደተባለው ምክንያት ስንሄድ ደግሞ ይበልጡኑ እንታመማለን … ወንጀለኛው ” የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛና በቀጣዩ አመት ተመራቂ !” መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቦ በፍርድ ቤቶ ተቀባይነት ማግኘቱ አገኘ ብለውናል ። ለእኔ የክስ ማቅለያ የቀረበው ሀሳብ የተማረ የተመራመረው ” የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ” ነኝ ባይ ወንጀለኛ ነው ፣ ምንም የማታውቅን እምቦቃቅላ ታዳጊ ገላን በአሻው መንገድ አድርጎ ገፎታል ፣ ገፈፋውም የተፈጸመው በአንድ አዋቂ መሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊያከብድ እንጅ ሊያቀል ባልተገባ ነበር ባይ ነኝ ። ይህ ያቀረበው የክስ ማቅለያ ይልቁንም በሰነድ ተረጋግጦ ክሱን ማጠንከር ሲገባው ክሱን ማቅለያ ሆኖ መቅረቡና ከምን ወደ ምን እንደቀለለ ያልተገለጸው ማቅለያ ተቀባይነት ማግኘቱ በራሱ በምንም ሚዛን ፍትሃዊነት የለውም ! ይህን ለመናገር ሰብእናና የራስን ፍርድ መስጠት እንጅ ግዴታ ህግ ማጥናት አያስፈልገውም …
የህዝብን መብት ለማስጠበቅ የተሰየሙትን የፍትህ አካላት የሙያ ብቃት ጥያቄ ውስጥ የጣለው ይህ መሰሉ አሳዛኙ የፍትህ ውሳኔ ማህበረሰቡ በፍትህ እንዳይተማመን ከማድ ረግ ባሻገር በህግ ጥላ ስር መጠበቁን በጥርጣሬና እንዲ ያይ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም ። ከዚህም አልፎ ተርፎ በአሚራ ደፋሪ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሀገሬው ፍትህ አጥቶ የሚንገዋለል እንዲሆን አድርጎታል ወደሚል መደምደሚያ አድርሶኛል … የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞ ች ጉዳይ መስፋፋትና ገደብ ማጣት በተደጋጋሚ በመንግ ስት ላይ የሰላ ወቀሳ ይቀርባል ። በተለይም የህግ ጥበቃ ውንና ቅጣቱን ከማጠንከሩ በተጓዳኝ ተማኝነት እንጅ የሙያ ብቃት ሚዛን ሆኖ ቅጥር ስለማይፈጸም ተደጋጋሚ ችግሮች ተስተውለዋል ። የፍትህ አካላት ብዛት እንጅ ጥራት የጎደላቸው መሆኑ ከዚሁ ጋር ይጠቀሳል ። የተባለውን ወቀሳ እውነታነት እንዳለው ለመረዳት የአሚራን አይነት በደል ተሰርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከት ብቻ ማየት ከበቂ በላይ ይመስለኛል ።
በአሚራ ውሳኔ አሰጣጥ እንዳየነው ከምንም በላይ የፍትህ ስርአቱ በወንጀለኛውም ሆነ በጠበቆች የቀረበውን የተውተፈተፈ መከላከያና ቅጣት ማቅለያ መቀበላቸው ለፍትህ አካላት የደረሱበትን ደረጃ ያሳይ ከሆነ መልካም ነው ። የአሚራን ጉዳይ በግርድፉ ላየ ለተመለከተው ጥፋታቸውን በአዞ እንባ ለመሸፋፈን ከተጉ ወንጀለኞች ጎን ለገንዘብ ብለው ጥፋቱን ለማቅለል ሚሞግቱት ጠበቆች ሰብዕና ያማል ፣ የዳኞቹ ውሳኔ አሰጣጥና ውሳኔ ማቅለያ አቀባበል ደግሞ ይገርማል ፣ ይደንቃል … ! ይህ መሰል ከእውነታው ጋር የሚጋጭ የተፋለሰ ፍርድ በአደባባይ ሲሰጥ ህጉን ማስከበር ያለባቸው አቃቤ ህግ ተወካዮች የታሉ ? ፍትህ ወዴት ነህ ? ያስብላል …
በሰብዕና ላይ ወንጀል ሲሰራ በቸልተኝነት መመልከት ሊቆም ይገባል ። የሴቶችን መብት ለማስከበር ተብሎ የወጡት ሕጎች ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አካል የሆነ የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን በ2005 ዓም መቋቋሙን ከሰማን አመታት ተቆጥረዋል ። ኮሚሽኑ በሴቶችና በሕጻናት ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተገን እንደሚሆን ቢጠቀስም ለአሚና የጎደለ ፍትህ ድምጹን ሲያሰማ አለመታየቱ ግር ያለው እኔን ብቻ ከሆነ መልካም ነው ፣ ግን አይመስለኝም ። ” መብቷ ይከበር ፣ ፍትህ ጎድሎባታል፣ ፍትህ ታግኝ ” የምንላት ታዳጊዋ አሚራ ያለ ፈቃዷ አይደለም ገላዋ የጸጉር መጠምጠሚያ “ሂጃቧ ” ሊነካ አይገባም ፣ ከተነካ ህግ ተጥሷል ! አሚና ድንግልናዋ አልተገሰሰም ፣ ማህጸኗ ግን ተነካክቷል ብሎ ወንጀለኛን ከአስገድዶ መድፈር ወንጀል ማራቅ ፣ ማሸሸት ፍትህን ማረጋገጥ ሳይሆን ፍትህን ማርከስ አድርጌ ነው የምቆጥረው ። ወንጀለኛው ” አስገድዶ የደፈረ ” ለመባል አሚራ በጭካኔ ተደፍራ እንደተገደለችው እንደ ሀና ኦላንጎ መሆን አልነበረባትም ! አሚራም ሀና እንደሆነችው ባትሆንም በአሚራም ማህጸን ዙሪያ ክብረ ነክ የመድፈር ሙከራ አድርጓል ። የቀረበው ማስረጃ የሚየስረዳው አርቆ አሳቢው የተማረ ጎልማሳ ምንም በማታውቀው የ4 ዓመት ከ6 ወር ታዳጊ ህጻን ላይ ወንጀል አስገድዶ መድፈር ለመሆኑ ሌላ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለ ብየ አላምንም!
የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን ሴቶች ሥርዓተ-ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶባቸው እንዲህ ሲመለከት አብሮ ከተጎጅ ወገኖች ጎን መቆም ፣ የሕግ ጥበቃ ማቆም ፣ የህግ ጠበቃ የማቆም አቅም ከሌለው የህግ ጥሰቱን በአደባባይ ተቀውሞ ስታዳጊዋ ብላቴና ስለአሚራ ፍትህ ማግኘት ድምጹን ሊያሰማ ይገባል !
በፍርድ ገምድሉ ውሳኔ ያዘኑ ቤተሰቦች ወላጆቿ ፍትህ ጎድሎባቸው ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!” ማለታቸው ስሰማ የእነሱም ጩኸትና አቤቱታ የእኔም ለአሚራና ቤተሰቦቿ ፍትህ ርትዕ ይከበርላቸው የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል ! ከምንም በላይ የሴት ልጅ በረከት የታደልኩ አባት እንደመሆኔ የሴት ልጅን ወሰን የሌለው ፍቅር አውቀዋለሁና ከአሚራ ቤተሰቦች ጋር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ፣ በጎለው ፍትህ አምርሬም አዝኛለሁ … !
ፍትህ ለህጻን አሚራና ቤተሰቦቿ ስል እጠይቃለሁ
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45788#sthash.wt3wNo5i.dpuf