Wednesday, August 12, 2015

ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስተርነታቸው ይቀጥላሉ ተባለ

(ዘ-ሐበሻ) በኦህዴድ; በብ አዴን እና በሕወሓት ውስጥ በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እየታመሰ የሚገኘው የኢሕአዴግ መንግስት በመጪው መስከረም ወር በሚመሰረተው “አዲሱ” መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ቦታውን ይዘው እንዲቆዩ እንደሚያደርግ የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:

hailemariam

 በአሁኑ ወቅት በሶሥቱ ትላልቅ ፓርቲዎች ውስጥ የተፈጠረው አለመተማመን ሃይለማርያም በቦታቸው እንዲቆዩ እንደኢያደርጋቸው የሚገልጹት ምንጮች በተለይም በብ አዴን እና በ ኦህዴድ ውስጥ ተገቢ የሚባል ጥያቄ የሚጠይቁ አባላትን በሙስና ለማሰር ሃሳብ እንዳለ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል:: ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን በያዝነው ወር ድርጅታዊ ጉባኤያቸውን በተናጠል በማካሄድ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ አባላት ያሏቸውን የሥራ አስፈፃሚ አባላትን የሚመርጡ ሲሆን እነዚህ አባላትም በያዝነው ወር መጨረሻ ወይንም በመስከረም ወር መግቢያ በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ የግንባሩን ሊቀመናብርት ይመርጣሉ ተባሏል:: የኢሕ አዴግ ሊቀመንበርም ሃይለማርያም ደሳለኝ ሆነው እንደሚቆዩና ሆኖም ግን ሌሎች ድርጅቱን ብዙ ዓመት አገልግለዋል የተባሉ ባለስልጣናት እንደሚሸኙ ተገልጿል:: የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ቦታን ሕወሓቶች አሁንም የሚፈልጉት ሲሆን የራሳቸውን ሰው ለማስቀመጥ ከላይ ታች እየተሯሯጡ ይገኛሉ:: ሆኖም ግን እርስ በ እርሳቸው መግባባት ስላልቻሉ ኃይለማርያም እንዲቀጥሉ ምክንያት ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45821#sthash.HpYmMfm2.dpuf

No comments:

Post a Comment