Tuesday, August 25, 2015

Sport: ገንዘቤ ዲባባ ያሸነፈችው በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ ፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ ነው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46176#sthash.E51VwfPV.dpuf


BEIJING, CHINA - AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women's 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)
BEIJING, CHINA – AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women’s 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                (ኢብራሂም ሻፊ)
ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ድልን ተጎናፅፋ የኢትዮጵያ ህዝብ ኩራት ትሁን እንጂ ቤይጂንግ ከመምጣቷ በፊት የተቀናጀ የስም ማጥፋት ሲካሄድባት እና የተለያዩ ውሃ የማይቋጥሩ ክሶች ሲቀርቡባት የከረመች አትሌት ናት፡፡ የዚህ የተቀናጀ የስም ማጥፋት እና ክስ አቀናባሪ ደግሞ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ (በዋናነት ዱቤ ጅሎ) ነበር፡፡ የቱታ እና ስኒከር ጫማ እርጥባን የሚጥልላቸው አንዳንድ “ጋዜጠኞች” ደግሞ የስም ማጥፋቱ እና የክስ ማርቀቁ ተባባሪዎቹ ነበሩ፡፡
ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆናለች ተብላ ተከሳለች፡፡ አዎን በእርግጥም ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ሮጣለች፡፡ ሞናኮ ላይ የዓለም 1500 ሜትር ሪከርድ ያሻሻለችው አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ሳይፈቅድላት ነው፡፡ እዚህ ላይ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ “አትሩጡ” ቢልም ለምን አትሩጡ እንዳለ አጥጋቢ ምክንያት አልነበረውም፡፡ የቱታ እና ስኒከር እርጥባን ተቀባዮችን “ጋዜጠኞች” ምክንያትን ሰምተን የፌዴሬሽኑ ምክንያት ነው ካልን “ፋቲግ” (ድካም) እንደ ሰበብ ቀርቦ ነበር፡፡ እግዜር ያሳያችሁ ሞናኮ ላይ የዳይመንድ ሊግ ውድድሩ የተደረገው ጁላይ 17/2015 ነበር፡፡ ድካም እንደ ሰበብ የቀረበው ኦገስት 22/2015 ለሚደረግ ውድድር ነው፡፡ አንድ ውድድር ከወር በላይ ቀርቶት ገንዘቤን “አትወዳዳሪ……ትደክሚያለሽ” ማለት ምን ዓይነት ሙያዊ ውሳኔ ነው? አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ይሄን ሰበብ አድርጎ በዓለም ቻምፒዮንሺፑ 1500 ሜትር እንደማትሮጥ አሳውቆ ነበር፡፡ ገንዘቤ የግድ እንደምትሮጥ ስታሳውቅም ያደራጃቸውን ጋዜጠኞች ተጠቅሞ “ፋቲግ…..ፋቲግ……..” እያለ ውርድ ከራሴ የሚመስል አይነት ማስታወቂያም ሲሰራ ሰንብቷል፡፡ በጣም የሚገርመው አሁን የዓለም ቻምፒየንሺፑን ድሎች እየተቆጣጠሩ የሚገኙት ከሞናኮ በኋላ በለንደን ጁላይ 24/25 (ሁለት ቀናት) አሸናፊ የነበሩ አትሌቶች ናቸው፡፡ ሞ ፋራህ፣ ዩሴን ቦልት እና ዳቪድ ሩዲሺያ ለዚህ እንደማስረጃ መነሳት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ከገንዘቤ በኋላ ዳይመንድ ሊግ ለሮጡ የውጪ ሀገር ሯጮች “ፋቲግ” ሲሉ አትሰሙም፡፡ የእነርሱ እኮ ርቀቱ አጭር ነው የሚል ሰበብ እንዳይቀርብ ደግሞ ሞ ፋራህ ለንደን ዳይመንድ ሊግ የሮጠው 3000 ሜትር ነው፡፡ ይኽን ርቀት 7፡34.66 ፉት ብሎት ኦገስት 22/2015 የዓለም 10000 ሜትር ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ የ5000 ሜትር ውድድሩን በድል ለመወጣትም ቀናት እየተጠባበቀ ነው፡፡ “ፋቲግ” የሚለው ቃል ሞ ላይ አይሰራም ገንዘቤ ላይ ግን ይደሰኮራል፡፡
ገንዘቤ ከጓደኞቿ (ኢትዮጵያዊያን ሌሎች አትሌቶች) ጋር አልተለማመደችም ተብላ ተከሳለች፡፡ እኔ ደግሞ ይኽች ዕፁብ አትሌት ለምን ብቁ ባልሆነ አሰልጣኝ ትሰለጥናለች? ለምን ከብቃቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ተቀባይነቱን በሚያስቀድም አሰልጣኝ ትሰራለች? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ገንዘቤ በሞስኮው የዓለም ቻምፒዮንሺፕስ 1500 ሜትርን ተወዳድራ ስምንተኛ ከወጣች ወዲህ የወሰነችው ምርጡ ውሳኔ ከታታሪው አሰልጣኝ ጃማ አደን ጋር መስሯቷ እና የልምምዷን አጠቃላይ መልክ መቀየሯ ነው፡፡ ጃማ አደን ሱዳናዊውን አቡበክር ካኪን (800 ሜትር) የዓለም ሻምፒዮን እንዲሁም ፤ አልጄሪያዊውን ቶውፊቅ ማክሉፊን (1500 ሜትር) የኦሊምፒክ አሸናፊ ማድረግ የቻሉ ድንቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮን ከገንዘቤ በተጨማሪ ሙሳብ ባላ (800 ሜትር) እና አያልነህ ሱሌይማንን (1500 ሜትር) የመሳሰሉ ምርጥ አትሌቶችን የሚመሩ ምርጥ አሰልጣኝ ናቸው፡፡
ገንዘቤ በእርሳቸው መሰልጠን ከጀመረች በኋላ ከቤት ውስጥ ውድድሮች አሸናፊነት ወደ ሁሉም መስክ አሸናፊነት ቀይረዋታል፡፡ የ2015 አንዳንድ ድሎቿን ብንመለከት ይሄን ይመሰክራሉ፡፡ ዩጂን፣ ኦስሎ እና ፓሪስ ላይ የተደረጉ ተከታታይ የ5000 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ልዕልቷ ሳትቸገር አሸንፋቸዋለች፡፡ ሞናኮ ላይ እርሷ የአንድ ዓመት ህፃን ሳለች (ከ22 ዓመታት በፊት የተመዘገበ) በቻይናዊቷ ኩ ዩንዢያ የተያዘውን 1500 ሜትር ሪከርድ ሰብራለች፡፡ ከ2014 ጀምራ 1500፣ 3000 እና 5000 ላይ የተፎካከሯትን በሙሉ ረታለች፡፡ ታዲያ ይህን ድል እንድታስመዘግብ የረዳት አሰልጣኝን ጥላ ስራውን ከፖለቲካ ፓርቲ በተሰጠው መታወቂያ ወደሚያፀድቅ አሰልጣኝ ለምን ትጓዛለች?

ገንዘቤ የዛሬውን እና መጪዎቹን ድልሽን ለእልፍ ዓመታት ስንዘክረው እንከርማለን፡፡ ዛሬ ኬንያውያን እና ሆላንዳዊያንን ጭምር አላሸነፍሽም፡፡ በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ፣ ፍርደ ገምድልነት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ውሳኔን፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ አሸንፈሻል፡፡ በድጋሚ እንኳን ደስ ያለሽ ገንዘቤ……….!!!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46176#sthash.E51VwfPV.dpufBEIJING, CHINA - AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women's 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)

No comments:

Post a Comment