Wednesday, August 26, 2015

Sport: ኢትዮጵያዊያኑ 3 አትሌቶች በቤጂንጉ የ5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ላይ ይሳተፋሉ

The men's 5000m heats at the IAAF World Championships, Beijing 2015 (Getty Images) © Copyrightበሙለታ ንገሻ በ15ኛው የቤጂንግ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በሶስት አትሌቶች ትወከላለች። ሌሊት 10 ስአት ከ35 ላይ በተደረገ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሀጎስ ገብረ ህይወትና ኢማና መርጋ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል። ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጎስ ገብረ ህይወት ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን፥ ኢማና መርጋ አምስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ነው ያለፈው። አትሌት ዮሚፍ ቀጄልጃ ውድድሩን 13:19.38. በሆነ ሰዓት የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ የነበረውን ሞህ ፋራህን ቀድሞ በመግባት የማጣሪያ ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩ ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን፥ 10 ስዓት ላይ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ፥ አትሌት ህይወት አያሌውና ሶፊያ አሰፋ ኢትዮጵያን ከዚህ ያልተለመደ የውጤት ማሽቆልቆል ይታደጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገ ሌሊት 10 ስአት ከ40 ላይ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ፣ አልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ጎይቶም ገብረ ስላሴ ይወዳደራሉ። በዚሁ ቀን ሌሊት 11 ከ35 በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ አማን ወጤ፣ ዳዊት ወልዴ እና መኮንን ገብረ መድህን ይሳተፋሉ። እሁድ ነሃሴ 24 2007 ዓ.ም 8 ስአት ከ30 ሌሊት በሴቶች ማራቶን ትርፌ ፀጋዬ፣ ማሬ ዲባባ እና ትእግስት ቱፋ የሚወዳደሩ ሲሆን፥ ቀን 8 ስአት ከ15 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር፤ 8 ስአት ከ45 ላይ ደግሞ የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ይከናወናሉ። ትናንት በተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ በ4 ደቂቃ 08:09 ሰከንድ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማስገኘቷ ይታወሳል። በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን 1 የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአለም 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ገንዘቤ ዲባባ፣ በወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ እንዲሁም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ገለቴ ቡርቃ ናቸው ሜዳልያዎቹን ያስገኙት። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች በወንዶች ውድድር ድል የራቃት ኢትዮጵያ፥ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከሜዳልያ ውጪ ሆናለች። ኢትዮጵያ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ያልሆነችበት 15ኛው የቤጂንግ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአንፃሩ ለኬንያውያን ስኬታማ ነው ማለት ይቻላል። ኬንያ እስካሁን 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ ሜዳልያዎችን በማግኘት ከአለም ሀገራት በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ብሪታንያ በ3 ወርቅ በ2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ጃማይካ በ2 ወርቅ እና በ1 ነሃስ በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46193#sthash.fSZPgGXF.dpuf

No comments:

Post a Comment