ነብዩ ሲራክ ላለፉት አስርት አመታት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምጽ በመሆን በአረቡ ዓለም ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን መረን የለቀቀ ስቃይ እና በደል መቋጫ እንዲበጅለት በድህረ ገጹ በማስተጋባት ላይ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ በተለይ ያለምንም ቅድመዝግጀት እና ሁለትዮሽ፡ስምምነት በቤት ሰራተኝነት በደላሎች ተወናብደው ቁም ስቅላቸውን እያዩ ሰለሚገኙ እህቶቻችን አሰቃቂ ተእይንት በማለዳ ወጎቹ በማስቃኘት በአጭር ግዜ ውስጥ የአያሌ ወገኖችን ትኩረት መሳብ የቻለና የጉዳዩ ባለቤት በሆነው ህዝብ ዘንድ አንድናቆትና ክበርን ያተረፈ መሆኑም ይነገራል።
በሌላ አቅጣጫ በጋዜጠኛው ዘገባዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ካድሬዎች እና አንዳንድ የሰራተኛ እና አስሪ ኤጀንሲ ባለቤቶች አይን የሚደረግበት ክትትል የጋዜጠኛው ን የስደት አለም ህይወት ውስብሰብ እና የከፋ አድርጎታል ። ጋዜጠኛው በስደት አለም ከሚገኝበት ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በግሉ ተከራይቶ ከሚኖርበት የመኖሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲፈናቀል ከሚሸረብበት ሴራ እና ኮሚኒቲ አካባቢ እንዳይደርስ እይተደረገበት ካለው ተጸኖ ባሻገር የመንግስት ካድሬዎች እና ፡ደላሎች በህይወቱ ላይ የሚሰነዘረውን ዱላ በመጋፈጥ መራራውን ጽዋ በአደባባይ ለመቀበል ተገዷል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን ለማጥፋት በተለያየ አቅጣጫ መልኩን እየለዋወጠ የሚሰነዘረው ጥቃት ፍጹም ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው በመሆኑ የጋዜጠኛው ደህንነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ፡ መግባቱን ብዙዎች ይናገራሉ። በተለይ ጋዜጠኛው የሚከተለውን ሃይማኖት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የአባራኩ ክፋይ ከሆነው ሙስሊም ወገኑ ጋር ለማጋጨት እነዚህ ወገኖች በድህረ ገጻቻቸው ከሚያሰሙት ሴጣናዊ ጩሀት ባሻገር ከአመት በፊት ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያን ህግ በመተላለፍ በጥብቅ የተከለከሉ የአልኮል መጠጦች እና መስል አይምሮ አደንዛዥ እጽ ንግድ ላይ የተሰማራ አስመስለው በሃሰት ወንጀላ ለወህኒ በመዳረግ ጋዜጠኛው የስይፍ ሰለባ እንዲሆን በጋዜጠኛው ህይወት ላይ የተቃጣው ሙከራ ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ አስደንግጧል በጅጉም አሳዝኗል ።
የዚህ ጋዜጠኛ የብዕር ጩሀት እንቀልፍ የነሳቸው የመንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ጋዜጠኛው ለረእፍት ወደ ሃገር ሲያቀና ለማፈን የነበራቸው እቀድ ይዚሁ እርኩስ ተግባራቸው አንዱ አካል እንደነበረም ይነገራል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በአረቡ ዓለም እንደ ጨው ተበትነው በሚገኙ ወገኖቻችን ዙሪያ በሚያቀርበው መረጃ በዲፕሎማቶቻችን ስራ ላይ ተጸኖ ፈጥሯል በሚል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ከጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢደርሰውም ጋዜጠኛ ነብዩ ግን በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ ትዕይንት እያየማለፉ ሊከፍለው የማይችለው እዳ ሆኖበት ከህሊና ጸጸት ለመዳን በሙያው ያስተማረውን ህዝብ ውለታ ለመክፈል ዛሬም የሚመጣውን ሁሉ ለመጋፈጥ እውነታዎችን መዘገቡን ቀጥሎሏ ።
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሰሞኑንን ለፓስፖርት እድሳት ወደ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት አቅንቶ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች ጋዜጠኛው የነዚህ ካድሬዎች እና ምስለኔዎች ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ጋዜጠኛው ቀደም ሲል በወገኖቹ ዙሪያ በድሀረ ገጹ ሲያቀርባቸው በነበሩ መረጃዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ነብዩ ሲራክ በጃችን ገባ ሲሉ መደመጣቸውን የሚገልጹ ምንጮች የጋዜጠኛው ፓስፖርት እድሳት በ ድርጅታዊ ውሳኔ በገወጥ ሊታገድ እንደሚችል ስጋታቸውን አክለው ገልጸዋል።
በዚህ ዙሪያ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን በአካል አጊቷ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ይህ ጋዜጠኛ ከተለመደው የእንገለሃልን እና በጃችን ትገባለህ ተራ የስልክ ማስፋራሪያ ባሻገር እስካሁን ምንም አይነት ችገር እንዳልገጠመው የሚገልጹ ምንጮች ፡ ጋዜጠኛው በጀመረው በጎ ተግባር እንደሚቀጥል እና እስከ ዛሬ ሲያቀርባቸው በነበሩ ዘገባዎቹ በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን መከራ እና ስቃይ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment