Tuesday, May 31, 2016

ኢትዮጵያውያን ምን እስኪፈጠር ነው የምንጠብቀው? (ስዩም ወርቅነህ)

3618556593_4674679485


~ 2.4 ሚሊዮን የአማራ ክልል ተወላጆች በህዝብ ቆጠራ ወቅት ጠፉ
~ ከ125 በላይ ህፃናት በጋምቤላ ክልል በሙርሌዎች ተዘረፉ
~ የእምነት ነፃነት በመጠየቃቸው ብቻ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው እስራት፣ ግርፋት፣ ግድያና እንግልት ዛሬም ቀጥሏል።
~ ላለፉት 25 ዓመታት በስርቱ ተላላኪዎች የተቃጠሉ ገዳማትና ቤተክርስቲያን ቁጥር ቀላል አይደለም።
~ ከ2000 በላይ ከብቶች በሙርሌዎች ተዘረፉ
~ ከ225 በላይ የጋምቤላ ተወላጆች በሙርሌዎች ተገደሉ
~ ከ400 በላይ የአኟክ ተወላጆች በህወሃት/ኢህአዴግ ተወላጆች በጠራራ ፀሃይ ተገደሉ
~ ከ200 በላይ ዜጎች ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ በህወሃት/ኢህአዴግ የፌደራልና የመከላከያ ሰራዊት ተገደሉ
~ ከ10 ዓመት በኋላ በሚደረገው ህዝባዊ ቆጠራ የጉራጌ፣ ኦሮሞ፣ አማራና የሌሎችም ዜጎች ቁጥር ቀንሷል
~ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከ80ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን አለቁ
~ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ አያሌ ኢትዮጵያውያን ሶማልያ ውስጥ ሰላም ለማስከበር በሚል ተልከው ተገድለዋል። የቀድሞ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስንት ሰው እንደሞተ ለመግለፅ ፓርላማ ውስጥ ተጠይቀው የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም ብለው እንቢ ማለታቸው የሚታወስ ነው።
~ አማራ ክልል ውስጥ ወላድ እናቶችን ክትባት በመስጠት እንዳይወልዱ ተደርገዋል። ያረገዙትም እንዲያስወርዳቸው ተደርገዋል።
~ ለሃገራችን የሚጠቅሙ አያሌ ኢትዮጵያውያን በሰበብ አስባቡ በእስር ቤት ታግደው ይገኛሉ።
~ ስርዓቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ምቹ ባለማድረጉ ምክንያት አያሌ ኢትዮጵያውያን ለስደት ተዳርገዋል። ያሰቡበት ያልደረሱትም የበረሃ ሲሳይ ሆነዋል። ሌሎችም በሜደትራኒያን ውቅያኖስ ተወስደዋል። በየበረሃው በባዕዳን ተደፍረው ለእብደት የተደራጉትና ለዘላለም የህሊና ጠባሳ እስረኛ የሆኑ ብዙ ናቸው። የዱር አራዊትና የአሳ መብል የሆኑትም ብዙዎች ናቸው።
~ 28 ኢትዮጵያውያን በISIS አንገታቸውን ተቀልተው ተገድለዋል።
~ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው Xenophobia እስከነ ህይወታቸው ከጎማ ጋር በመጠፈር ተቃጠለው ተገድለዋል። እሚከራከርላቸው አጥተው በየቀኑ የሚገደሉትም ቁጥር ስፍር የላቸውም።
~ የመን ውስጥ በተቀሰቀሰው የርስበርስ ጦርነት በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአየር መደብደባቸው የሚታወስ ነው።
~ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዋናው ቅጂ ተሰርቆ ወጥቷል።
~ በጎንደር በኩል ለሱዳን 160 ኪሎ ሜትር መሬት ወደ ውስጥ ተላልፎ ተሰጥቷል
~ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 25 ዓመታት ወደብ አልባ ተደርጋለች
~ ላለፉት 25 ዓመታት የተገደሉትና የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር በውን የሚታወቅ አይመስለኝም። በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ተቃውሞ እንኳን ከ200 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል፣ ከ3000 በላይ ታስረዋል፣ አያሌዎች ተደብድበዋል፣ ለስደት ተዳርገዋል።
~ በየአረብ ሃገራ በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይና በደል ለሁላችንም ግልፅ ነው
~ የማንነት ጥያቄ ባነሱት የወልቃይት ጠገዴ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር የሚዘገንን ነው።
~ ሌላም ሌላም……..
…,……………………..……..

ይህ ሁሉ በደል አልበቃ ብሎ ምን እስኪያደርጉን ነው የምንጠብቀው??

Monday, May 30, 2016

አርከበ እቁባይ የራሳቸውን ሞራል እየገነቡ ነው

equbai

ዘ-ሐበሻ) “የመለስ ራዕይ የሚባል በቃ” ሲሉ እየተከራከሩ ቆይተዋል የሚባሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘ልዩ’ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ “Made in Africa industrial policy in Ethiopia” የተሰኘውና በርሳቸው ስም ይጻፍ እንጂ እርሳቸው ይጻፉት አይጻፉት ያልተረጋገጠውን መጽሐፋቸውን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያነት በስጦታ መልክ አብርክቻለው በሚል ዜናውን በሚያዟቸው ሚዲያዎች በማስነገር በመገባት ላይ ናቸው::
“Made in Africa industrial policy in Ethiopia” የተሰኘውና በአቶ አርከበ ስም የወጣው መጽሐፍ አቶ አርከበ እንዳልጻፉት እየተነገረ ቢሆንም ዘ-ሐበሻ ለዚህ ጉዳይ ማረጋገጫ ማግኘት አልቻለችም:: ሆኖም ግን የመጽሐፉ ጸሐፊ ነኝ ያሉት አቶ አርከበ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት “መጽሐፋቸው” ለማስተማሪያነት እንዲውል ማበርከታቸውን በከፍተኛ የመንግስት ሚድያዎች እንዲዘገብ አድርገዋል::
ከዚህ ቀደም በርካታ ጥልቅ እውቀትን የያዙ መጽሐፍ የጻፉ ወገኖች መጽሐፍቶቻቸውን ለክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማስተማሪያነት ቢያበረክቱም እንደ አቶ አርከበ የመንግስት ሚዲያ ሽፋን ሳያገኙ ቀርተዋል

Ethiopia: Note the following points on this exam leakage vis-a-vis cancellation saga


fetena
One: There are some pseudo-moralists & rough dudes who accuse the Oromo activists for leaking & disqualifying this exam process that was meant to kill a generation of Oromo students. Ignoring regime apologists for the obvious reasons, we have learned that some Ethiopianists are also on this accusatory bandwagon. Well, what these pseudo-moralists say in a nutshell is that Oromo students who didn’t attend classes for over 18 weeks (the academic year has 32 effective weeks) had to sit for a national exam that’s administered at the country level (and graded as such) with literally no preparation for the exams. For them in effect, it would have been morally okey if regime retaliates for the protests by making the whole students from Oromia region fail to get pass marks or attain “bad grades” to be placed in any of the “not-good” streams of University studies. That’s the bottom-line of their morality. It ain’t only unjust & immoral thought, though, but a genocidal one indeed, if looked at its root.
Two: It’s has to be recalled that students, teachers, student families, Oromo elders etc filed their formal requests for the extension of the examination period, compensatory tutors for lost classes to cover all remaining subjects. The Oromia Education Department consented at the beginning. But because of the arrogance & ignorance of the TPLF oligarchic bosses who out-rightly rejected this public request thereby forcing the process go ahead, Oromo activists motivated by the mere sense of justice leaked the exam booklets first for Maths, English & Physics; then followed the rest, thereby effectively disqualifying the whole process that would be valid ONLY if secured.
Three: The exams were leaked days before, but the idea of dumping it on social media just a day before the exam date was a well-thought-out-strategy meant to minimize the psychological trauma it may carry onto students, esp on those from other regional states in Ethiopia (hence damage minimization measures taken :) ). By releasing it at night just before the exam date, we believe that most well to do students didn’t have to endure the stress that might have been entailed in the exam leaking news circulating for long.
Four: Once again, the regime is forced to cancel another thing after having refused to do so via a formally filed public requests in a peaceful & reasonable way. This is again a victory for the #OromoProtests. And we believe that the psychological damages entailed, resources wasted & feelings hurt are due all the responsibility of the regime that is addicted to doing everything by force.
Five: Making the exam cancelled ain’t the ultimate goal. Students in Oromia state should be compensated for the time they lost of their studies, tutors prepared for students to make up for lost classes, appropriate technical & psychological supports extended for students to help them get ready for the national exams. The students need to be normalized. They were being terrorized & brutalized by the Agazi killing squad throughout the academic year; they also lost some of their intimate friends & families. With all these, forcing them sit for the country-wide/national exam is an inexcusable crime.

Sunday, May 29, 2016

ጎንደር ህብረት አስቸኳይ መግለጫ – “የወልቃይት ጠገዴ፣ ቃፍቲያ፣ ሁመራና ጠለምት ህዝብ ፈጥኖ ደራሽ አጋር ይሻል




Gondor Hibret
ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ፤ አገር ሸንሽኖ፤ ህዝብን ከፋፍሎ፤ ለዘለዓለም የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም አለሞ እና ሸርቦ የተነሳውን ህልሙን ለማሳካት፤ የመጀመርያ የጥቃት ኢላማው ያደረጋት የጎንደር ክ/ሀገርን ነው። የዚም የመጀመርያው የግፍ ሰቆቃን እየተጋቱ ያሉት፤ ደግሞ ሰሜን ምዕራብ ክ/ሀገራችን ኗሪ የሆኑት የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ፀለምት ወገኖቻችን ናቸው።
ይሁን እንጂ፤ ከሰላሳ ዓመት በላይ የአካባቢዋን እና የዘር መሰረታቸውን ታሪክ ነጋሪ እንኳ እንዳይኖር፤ አንድ በዓንድ ለቅሜ አጥፍቻለሁ፤ ብሎ ያስብ የነበረውን ከንቱ የወያኔ ቅዠት አዲሱ ትውልድ፤ ለማንነቱ፤ ፍርሃትን ሰብሮ ወደ ትግል ከወጣ ውሎ ቢያድርም፤ አሁን ግን የነዚህ ወገኖቻችን የትግል ምዕራፍ የመጨረሻው የሞት ሽረት ደረጃ ላይ ደርሷል።

(ሁመራ ከተማ)

የዚህም አንዱ እና ዋንው ሀቅ፤ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ በጉልበት የጫነዉ የመስፋፋት እና የመሬት ቅርምት አባዜን ለመገደብ፤ በሁሉም የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነት ድጋፍ ማግኘቱ ነው። ከእንግዲህ በኋላ፤ የቃፍቲያ ሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብ የወያኔን የዘር አጥፊ በደል መሸከም ከሚችለዉ በላይ በመሆኑ፤ ትግስቱን ጨርሶ በአንድ ድምጽ ተማምሎ “የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር ተከዜን ተሻግሮ አያስተዳድረንም” ከሚል ዉሳኔ ላይ ደርሶ፤ የራሱን መሪና የጎበዝ አለቃ መርጧል። በጎንደሬነቱ፤ በአማራነቱ፤ በባህሉ፤ ለዘመናት በኖረበት መሬቱና በጠቅላላ ማንነቱ ላይ ግፍና መከራ ስለተፈጸመበት፤ በአንድ ድምጽ በቃለ መሃላ ነጻነቱን አዉጇል። ተወደደም፤ ተጠላም፤ ይህ የቃፍቲያ ሁመራ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ እና የጠለምት ህዝብ “ጎንደሬም አማራም ነን” በሚል መፈክር ለነፃነቱ ያቀጣጠለውን ትግል፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቅንነት መቀበል ሰባአዊነት ነው። በተለይ ደግሞ፤ ለዘመናት የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ፤ በጉርብትና ሲኖሩ፤ ተዋደው እና ተፈቃቅረው ያጋኙትን ተካፍለው ከመኖር ባሻገር፤ አንድም ቀን እንኳ፤ የመሬት ይገባኛል ግጭት አድርገው እንደማያውቁ እየታወቀ፤ በአሁኑ ሰዓት፤ የትግራይ ወገኖቻችን፤ ዘመን ካሳበጣቸው፤ ጥቂት ከውሥጣቸው በወጡ ቡድኖች ምክንያት፤ የተጠነሰሰውን፤ ታሪክን መሰረት ያላደረገ፤ የመሬት ሥግብግብነት፤ ተንኮል፤ በዝምታ፤ መመልከት፤ እጅግ አሳዛኝ የሆነ፤ የታሪክ ስህተት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ስለሆነም፤ የትግራን እና የጎንደርን ሕዝብ የወደፊት አብሮነት ታሪክ ለማስቀጠል ሲባል፤ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ፤ ወገኖቻችን ይዘው የተነሱበትን የማንነት ጥያቄ፤ የታሪክ እውነት መሆኑን፤ ማክበር እና መቀበል እንዳለበት ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን። አፈጣጠሩ እና ባህሪው አይፈቅድለትም እንጂ፤ ልብ ሰጥቶት የገዥዉ መደብም ቢሆን፤ ይህን የሕዝብ ውሳኔ ማከበር የጎንደርን ህዝብ ማክበር ነዉ የሚል እምነት አለን። ለዓመታት የጠዬቀዉ የጎንደሬነት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ጭቆናዉ በዝቶበት እራሱ በመረጣቸዉ መሪወች ለመተዳደር መወሰኑ ፍህታዊ እና ህዝባዊ እርምጃ ነዉ። መከበር ይገባዋል!!
ከእንግዲህ ይህንን ህሊናዉ የቆሰለ እንግዳ ተቀባይ ደግ ህዝባቸን ላይ፤ ተከዜን ተሻግሮ ከአድዋ በመጣ ፀረ ሽምቅ ሰራዊት ተኩሶ በመግደል፤ የበለጠ ሕዝባችንን ወደከፋ መተላለቅ የሚገፋ መሆኑን ተገንዝቦ፤ ጣቱን ከመሳሪያ ምላጭ አንስቶ፤ የወገኖቻችን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ እናሳስባለን።
ይህ ግፍ እና በደል የወለደውን፤ የጎንደሬ/የአማራ ማንነት ጥያቄ፤ ቆመንለታል ብላችሁ፤ ለ25 ዓመት በወያኔ፤ እየተሽከረከራችሁ ያላችሁ፤ የብ.አ.ዴን አባላት እና ካድሬዎች፤ የማንነታችሁ መፈተኛ ወቅት ላይ በመሆናችሁ እና፤ የመጨረሻ እጣ ፈንታችሁ ወቅት ላይ በመድረሳችሁ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ደወል፤ እየተደወለ ነው። በዚያው እንዳታሸልቡ፤ ከወገኖቻችሁ ጋር ለማንነታችሁ አብራችሁ በመቆም እስካሁን የበደላችሁትን ወገናችሁን ልትክሱ የግድ ነው። እንዲሁም፤ የሰባቱ አዉራጃ የጎንደር ህዝብ፤ ጥያቄው፤ የራሱ ማንነት ጭምር መሆኑን በማመን፤ በአስቸኳይ፤ በሚፈለገው ሁሉ ትብብሩን ማሳየት፤ የግድ እሚልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ፤ እስቸኳይ ታሪካዊ ምላሽ፤ ለወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት ወገኖቻችን እንዲያሳይ የጎንደር ሕብረት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳልንለን። የጎንደር ሕብረት የተመሰረተበት ቋሚ ዓላማም፤ ሁላችንም በሰላም እና በፍቅር ታሪካዊ፤ መልካዓ ምድራችንን ጠብቀን በጋራ እንድንኖር የሚያስችለንን ታሪክ ለማስጠበቅ ነው። በመሆኑም፤ ስማችን ጎንደር ነክ ይሁን እንጅ፤ ለትግራይም ሆነ፤ ለመላ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እኩል ፍቅር፤ እኩል፤ ተቆርቋሪነት እና ኃላፊነት ይሰማናል።
ሌላዉ ሳንጠቅስ የማናልፈዉ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ደግሞ ባለፈው ወር የጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመዉ የጀምላ ጭፍጨፋ ነዉ። የኢትዮጵያን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በተሸረበ ሴራ ምክንያት ወያኔ፤ ጠረፍ ጠባቂ፤ ፀጥታ አስከባሪ፤ የነበሩትን የታጠቁትን የአካባቢ ሚሊሻዎች፤ ትጥቃቸውን አስፈትቶ፤ ካምፕ ውስጥ እንደከብት በመዝጋቱ ምክንያት፤ አካባቢዉን ክፍት መሆኑን የተረዱ፤ ከ እንሰሳት ዝርፊያ አልፈው የሰው ህይወት ለማጥፋት ተዳፍረው የማያውቁ የደቡብ ሱዳን ኗሪ የሙርሊ ብሔረሰቦች በወሰዱት አሰቃቂ ርምጃ ከ200 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈዉ፤ 150 ታፍነዉ ሲወሰዱ፤ እጅግ ብዛት ያላቸውን ቤት እና ንብረት አቃጥለው፤ በሺ የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶችም ተዘርፈው ተወሥደዋል።
እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ በመተከል ቁጥራቸዉ ወደ 70 የሚደርሱ አርሶ አደሮች በሱዳን መንግስት ተጠልፈዉ መዳረሻቸዉ ጠፍቶ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችም ተዘርፈው ሲወሰዱ፤ እርምጃ የሚወስድ ቀርቶ፤ የሚጠይቅ መንግስት እንኳ አልተገኘም።
ይህ የሚያሳየው፤ አገራችንም ሆነ ሕዝባችን፤ መንግሥት ተብዬ አገር በቀል ጠላት ቅንብር፤ በውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የጥቃት አደጋ እንደተደቅነብን ነው። በመሆኑም፤ ኢትዮጵያ አገራችንም ሆነ የህዝባችን ደህንነት የሚጠብቅ መንግስት እንደሌለ አዉቀን በሞቱት ወገኖቻችን መሪሪ የሆነ ሃዘናችንን በሃገራዊ ቁጭት እየገለጽን፤ ለዘመድ አዝማድ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን እንላለን። የደቡብ ሱዳንም ሆነ የሰሜን ሱዳን መንግስት በወያኔ ቅጥረኞች ታፍነዉ የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከነንብረታቸዉ ወዳገራቸዉ በአስቸኳይ እንዲመለሱ፤ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን። የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብም፤ በዬአካባቢው የራሱን መሪ መርጦ፤ ደህንነቱን ጠብቆ፤ ዳር ደንበሩን እንዲያስከብር ጥብቅ መልክታችን እናስተላልፋለን። ከዉጭ አገር ጋር ተባባሪ የሆነዉ የወያኔን መንግስት እንደ አገር መሪ ቆጥሮ ህዝባችን እንዳይዘናጋ አደራ እንላለን።
በመጨረሻም በጎንደር ክፍለ ሀገር በቋራ ወረዳ የጓንግን ወንዝን ተሻግሮ ከኢትዮጵያ መሬት የሰፈረዉ የሱዳን ወታደር በአስቸኳይ እንዲለቅ እንጠይቃልን።
ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ዳር ድንበሩን ያስከብራል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ጎንደር ህብረት

ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ለኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ሲነግ ክሬዲት ሰጡ – “ተወልደ፣ ፃድቃን፣ ስዬና ተፈራ ዋልዋ ስለአሰብ ጥያቄ ያነሱ ነበር” አሉ



abebe Tekelehianot
(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ስልጣናቸውን እንዲያጡ የተደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት ደርግን ለመጣል ለተደረገው ትግል ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ሲነግና ወዘተ አስተውጽኦ እንደነበራቸው ተናገሩ:: ጄነራሉ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ግንቦት 20ን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር ስለአሰብ ወደብ ጉዳይም ተናግረዋል::
“ድሮም ቢሆን የኤርትራን ነፃነት ተቀብለው የአሰብ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ። እንደነ አቶ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ አቶ ስየ አብርሃ፣ አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ እኔም ጥያቄዎች የምናነሳበት ሁኔታ ነበር፡፡ በዝርዝር ባንወያይበትም። አሜሪካ ሄጄ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስሠራ ግን በዚህ ላይ ጥናት አካሂጄ የባህር በር መብታችንን በሕጋዊ መንገድ ማስመለስ እንደምችል የሚያረጋግጥ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። ባለማወቅና በመታበይ (Ignorance and arrogance) ያጣነው መብት ነው፡፡ አሁንም ግን ሕጋዊ መሠረት አለን፡፡”
ያሉት ጀነራሉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
አሁን እየተነሱ ባሉት የህዝብ እንስቅቃሴዎች ዙሪያ ከሪፖርተር:-
“ሕዝባዊ አመፅ እየታየ ያለው በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፉን በገለጸበት ማግሥት ነው፡፡ ይህን ያህል የሕዝብ ተቃውሞ መነሳቱ በምርጫ ሒደቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም?” የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ሜጀር ጀነራል አበበ ” የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች መደባለቅ አንዱ ትልቅ ችግር ነው። ኢሕአዴግ የመንግሥት ሚድያ፣ የመንግሥት ቢሮ፣ ገንዘብና አሉ የሚባሉ እርከኖችን ለፓርቲ ሥራ ስለሚያውል የፉክክር ሜዳው ዴሞክራሲን የሚያስችል (democracy enabling) እንዳይሆን አድርጎታል። ቻርለስ ቲሊ የሚባል ታላቅ የፖለቲካ ሳይንቲስት አንድ ፓርቲ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን ለብቻው ከያዘ ገና ከወዲሁ ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ያልሆነ፣ በሕዝብ ተቀባይነት የሌለው ምርጫ ነው ማለት ይቻላል ይላል። ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ከፋብሪካ እንደሚወጣ ወጥ ምርት አይደለም። የተለያየ ፍላጎት፣ ምርጫና ዝንባሌ ስለሚኖረው። አሥር በመቶ እንኳ ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ አያንፀባርቅም። የፌዴራሊዝም ባለሙያዎችና አገራዊ የውክልና ተቋማት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ማንፀባረቅ አለባቸው ይላሉ። ስለዚህ ኢሕአዴግ አሽነፍኩ ያለበት ሒደትም የታወጀው ውጤትም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ጭምር ነው። ውጤቱ ሲነገር ስቀን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አደጋው ፈጦ እያየነው ነው። ኢሕአዴግ ማሸነፍ አይችልም ነበር እያልኩ አይደለም፡፡”
ብለዋል::
ቃለምልልሱን እንደወረደ ለግንዛቤ እንዲረዳዎ እንደሚከተለው አቅርበነዋል:-

ሪፖርተር፡- መድበለ ፓርቲ ሥርዓትና ተቋማዊ አሠራር ከመገንባት አንፃር አሁን መሬት ላይ ያለው አሠራር ከሕገ መንግሥቱ ጋር ሲታይ ምንይመስላል?
ጄኔራል አበበ፡- በጣም ዘመናዊ ሕገ መንግሥት አለን። ሕገ መንግሥቱ ግሎባላይዜሽን፣ የሌሎች አገሮች ተሞክሮና የራሳችን ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የወጣ ነው። ነገር ግን ፍፁም ነው ማለት አይደለም። በመሠረቱ ሲታይ ግን ሕገ መንግሥቱ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍላጎትን ያሟላ ነው። መስተካከል ያለበት ነገርም ሊኖር ይችላል። አሁን ትልቁ ችግር ያለው በተግባር ማዋል ላይ ነው። የሕገ መንግሥት ተቋማት ነፃነት የተጠበቀ አይደለም። በእኔ ግምገማ ሁሉንም ሥልጣን የያዘው አስፈጻሚው አካል ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ከሚጠበቀው አንፃር ሲታይ ብዙ መሠረታዊ ችግሮች አሉበት። በሕገ መንግሥቱ የበላይ አካል ተቆጣጣሪ ሆኖ እያለ በተግባር ግን ሥራ አስፈጻሚ የሚያዘውን የሚፈጽም ነው፡፡ በተመሳሳይ ፍርድ ቤትም እንደዚያው ነው። በተለይ መንግሥትና ፓርቲ አንድ የሆኑበት አሠራር ነው ያለው። መለያየት አለበት። ይህ በጠቅላላ ሕገ መንግሥቱን የሚንድ አሠራር ነው። ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ህልውናም ትልቅ አደጋ ነው። ኢሕአዴግ መንግሥት በመያዙ ለአደጋው ዋና ድርሻ ቢኖረውም በአጠቃላይ ሲታይ ግን አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎችም ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው ናቸው። ሕገ መንግሥትን መሠረት አድርገው፣ በሕገ መንግሥቱ ያሉት ተቋማትን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ክፍተት ይታያል። አሁን ያለው መንግሥት ‹‹ከእኔ በላይ ማን አለ?›› የሚል እብሪትም ያለበት መንግሥት ነው። የዴሞክራሲ ምኅዳር እያጠበበ እያጠበበ ሄዷል። ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እየተገደበ ነው ያለው። አሁን ያሉትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደ ፀጋ አያይም፡፡ ኢሕአዴግ የተደራጀ የሕዝብ እንቅስቃሴ ሥጋት ይሆንበታል። ስለዚህ ፓርቲዎችን የማዳከም ሥራ ነው የሚሠራው። ይህም ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት አደጋ ነው።
ከተቋማት አኳያ ሲታይም በተለይ ፖለቲካዊ ተቋማት እንደ ፓርላማ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጠንካራ ናቸው ለማለት የሚከብድ ነው። ተቋማቱ ያረጁ ናቸው። ይኼ ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትና ለዴሞክራሲ አደገኛ ነው። ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን እንደ ፀጋ ዓይቶ አብሮ የሚሠራበትንና ተቃዋሚዎች የሚጠናከሩበትን ሁኔታ መፍጠር አለበት። የፕሬስ መብትን ማረጋገጥም አለበት፡፡ በተለይ የተደራጀ ሕዝብ ተቃውሞ በሚያሰማበት ጊዜ ይህን እንደ ትልቅ ሀብት ዓይቶ መደገፍና ሕዝቡን ሰምቶ የሕዝቡን ፍላጎት በተሻለ ለሟሟላት መንቀሳቀስ አለበት። አሁን የስኳር ኮርፖሬሽንን ስናየው 77 ቢሊዮን ብር ያህል የሚያንቀሳቅስና በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ እንዴት ነው አንድ ትልቅ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራን ድርጅት ማን ነው የሚያስፈራራው? እነዚህ ሰዎችስ ማን ናቸው? በስኳር ያለው ችግርም በሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳለ ባለሙያዎች መረጃ አላቸው። ለምሳሌ ግልገል ጊቤ ሦስት እስከ አሁን ለምን ተጓተተ? የሥራው ጥራትስ ምን ያህል ነው? አሁን የምንፈልገውን ኃይልስ አግኝተናል ወይ? በህዳሴ ግድብ ላይም ቢሆን ብዙ ባለሙያዎች ጥያቄዎችና ሥጋቶች ያነሳሉ።
ሪፖርተር፡- የትጥቅ ትግል ከማካሄድና ሲቪል መንግሥት ሆኖ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከመገንባት የቱ ይከብዳል ይላሉ?

abebe
ጄኔራል አበበ፡- የትጥቅ ትግል የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛን ለማስወገድ የሚካሄድ ትግል ነው፡፡ ስለዚህ የትጥቅ ትግል በኃይል የሚደረግ በመሆኑ በባህሪው ከዴሞክራሲ ጋር ግጭት ሊኖረው ይችላል። ምክንያቱም ማስገደድ ይኖረዋል።  ይህ የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛ በሕዝባችን ትግል ከተወገደ በኋላ በሽግግር መንግሥት ቻርተርና ቀጥሎ በመጣው ሕገ መንግሥት በኩል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መንደርደርያ የሚሆን ሥራ ተሠርቷል። በዚህም የሕዝቦች መሠረታዊ ጥያቄ ለመፍታት ትልቅ ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ያልተሻገርናቸው ፈተናዎች አሉ። በመጀመርያ ኢሕአዴግ ራሱን መቀየር ነበረበት። የትጥቅ ትግል አስተሳሰብና የአገር ግንባታ አስተሳሰቦች መሠረታዊ ልዩነት አላቸው። ኢሕአዴግ ራሱን ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ግብዓት ከሆኑ እሳቤዎች ጋር አጣጥሞ የሄደ አይመስለኝም። ኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የእኛ ትውልድ የአማፂ ትውልድ ነው። የአማፂ ትውልድ የዴሞክራሲ ትውልድ መሆን አይችልም። ስለዚህም ሌሎች ፓርቲዎችም ራሳቸውን በሕገ መንግሥቱና በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ እሳቤዎች ጋር ማጣጣም ይኖርባቸዋል። የእኛ ትውልድ ከራሱ እሳቤና ተግባር ውጪ ያለን አካል መብት የማያከብር ‹‹እኔ ብቻ ነኝ ልክ›› የሚል አክራሪነት የሚታይበት ትውልድ ነው። ተማሪ ሆነን ሰላማዊ ሠልፍ እንውጣ በምንልበት ጊዜ እምቢ የሚል ተማሪ ካለ ይመታል፡፡ ይህ በመሠረቱ ኢዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው። እንጭጭነትም ነው። ስለዚህ የኛ ትውልድ የዴሞክራሲ ትውልድ አይደለም፡፡ የአመፅ ትውልድ ነው፡፡ የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛ የነበረን ሥርዓት ግን በማስወገዱ እኮራበታለሁ።  ከዚያ በኋላ  አዲሱ ትውልድ ተረክቦ መሄድ ነበረበት፡፡ ሆኖም የእኛ ትውልድ አሁንም ሥልጣንን የሙጥኝ ብሎ አልለቅም በማለቱ አሁን ለሚታየው ቀውስ ምክንያት ሆኗል።
ሪፖርተር፡- ምን ማለት ነው ‹‹የሙጥኝ ብሏል›› ሲሉለምሳሌ ኢሕአዴግ ውስጥ መተካካት እየተደረገ እንደሆነ ይሰማል፡፡ የመተካካቱን ሒደት አላመኑበትም?
ጄኔራል አበበ፡- መተካካት ሲባል የትውልድ መሆን አለበት፣ የግለሰቦች አይደለም። የአሁኑ ትውልድ ብቃት ያለው ትውልድ ነው። ገና ሲወለድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያውቅ፣ ከመንግሥት የተለዩ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን የሚያነብ፣ የተለያዩ ሐሳቦችን የሚያውቅ፣ ዓለም አቀፍ ትስስር ያለው፣ በምርምር ብዙ ነገር ማድረግ የሚችል ትውልድ ነው። ስለዚህ መተካካት ሲባል የትውልድ መጎራረስ ነው። ካለፈው ትውልድ በጎ በጎውን ተምሮ የራሱን ጥበብ ጨምሮበት እንደ ትውልድ አገሩን ሲረከብ ነው መተካካት የሚባለው።
ሪፖርተር፡- ‹‹የዴሞክራሲ ምኅዳሩ እየጠበበ ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ኢሕአዴግን ባልመጣበት የሰላማዊ ትግል መድረክ ማሸነፍ ስለማይቻል አዋጪውየትጥቅ ትግል ነው››የሚሉ ተቃዋሚዎች አሉ። የእርስዎ ግምገማ ምን ይመስላል?
ጄኔራል አበበ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። ይህ ለዴሞክራሲው ምን ማለት ነው የሚለው በደንብ መታየት አለበት። መንገድ ተሠራ ሲባል ሕዝቦች የሚገናኙበት፣ አንዱ የአንዱን ባህል የሚማርበት ዕድል ሰፋ ወይም ተፈጠረ ማለት ነው። ስለዚህ የትብብርና የአስተሳሰብ አድማሱ የሚሰፋበት ዕድል አለ ማለት ነው። የውኃ አገልግሎት ተሠራ ማለት ያቺ ሚስኪን ሴት አራት አምስት ሰዓታት ለውኃ የምታጠፋውን ጊዜ ትቆጥባለች ማለት ነው። ጤና ኬላ ተሠራ ማለት ጤንነቱ የተጠበቀ ልጅ መማር ይችላል ማለት ነው። የአንደኛ ትምህርት መስፋፋት ማለት እኮ ለዴሞክራታይዜሽን ሰፊ ምንጣፍ እየተነጠፈ ነው ማለት ነው። አባትም፣ እናትም ልጅም ለፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚሆን ጊዜ አገኙ ማለት ነው። በአጠቃላይ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታው እየተቀየረ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ፍላጎቱ የሚጨምር ትውልድም እየተፈጠረ ነው። እዚህ ላይ ቅራኔ አለ፤ ሆኖም ይህንን ቅራኔ መፍታት የሚችል ትውልድ እየመጣ ነው፡፡ ይህ ትውልድ ያጣው ቦታ ብቻ ነው። በትጥቅ ትግል ዴሞክራሲን ማስፈን የሚለው ነገር አስቂኝ ነው። ትጥቅ ትግል ለዚህች አገር አይረባም፣ በጣም አደገኛ ነገር ነው። የዴሞክራሲ ምኅዳሩ እየጠበበ መሄዱ ወደ ትጥቅ ትግል እንድትገባ ምክንያት ሊሆን አይችልም። በዚህ ጠባብ ሁኔታም ጭምር ጠንካራና እውነተኛ ፖለቲካዊ አመራር መስጠት የሚችል ካለ መታገል ይቻላል፡፡ ስለዚህም ነው በርካታ ዜጎች አገር ውስጥ እየታገሉ ያሉት። ምክንያቱም ሕዝቡ በቦታው ነው።
የኢትዮጵያ ዴሞክራታይዜሽን በኢሕአዴግ ፈቃድ ላይ የሚመሠረት ነገር አይደለም። በተወሰነ ሁኔታ ኢሕአዴግ ጥሩ በሚሆንበት ጊዜ ሒደቱን ሊያፋጥነው ይችላል ወይም በተቃራኒው ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግን ፈቃድ መጠየቅ የለበትም። ሕዝቡ ይህንን ሥርዓት ያመጣው በራሱ ትግል ነው፡፡ የሚያስቀጥለውም ሕዝቡ ራሱ ነው። የ1997 ዓ.ም. ክስተት ሕዝብ ካመፀ ምን ማድረግ እንደሚችል ደንበኛ ማሳያ ነው። አሁን በኦሮማያና በትግራይ እምባሰነይቲ አካባቢ እየታየ ያለው የተደራጀ ሕዝባዊ የመብት ጥያቄ አለ። በሁሉም የሚታይ ባይሆንም አሁንም ኢሕአዴግ ውስጥ ሁሉንም ነገር በኃይል ለመፍታት የመፈለግና የመሞከር አዝማሚያ ይታያል። ይህንን የትጥቅ ትግል አስተሳሰብ አሽቀንጥረው መጣል አለባቸው። ምኅዳሩም ፍፁም ዝግ አይደለም፡፡ ጠባብ በመሆኑ ግን ብዙ መስዋዕትነትና ዋጋ ይጠይቃል።
ሪፖርተር፡- ሕዝባዊ አመፅ እየታየ ያለው በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፉን በገለጸበት ማግሥት ነው፡፡ ይህን ያህል የሕዝብ ተቃውሞ መነሳቱ በምርጫ ሒደቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም?
ጄኔራል አበበ፡- የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች መደባለቅ አንዱ ትልቅ ችግር ነው። ኢሕአዴግ የመንግሥት ሚድያ፣ የመንግሥት ቢሮ፣ ገንዘብና አሉ የሚባሉ እርከኖችን ለፓርቲ ሥራ ስለሚያውል የፉክክር ሜዳው ዴሞክራሲን የሚያስችል (democracy enabling) እንዳይሆን አድርጎታል። ቻርለስ ቲሊ የሚባል ታላቅ የፖለቲካ ሳይንቲስት አንድ ፓርቲ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን ለብቻው ከያዘ ገና ከወዲሁ ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ያልሆነ፣ በሕዝብ ተቀባይነት የሌለው ምርጫ ነው ማለት ይቻላል ይላል። ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ከፋብሪካ እንደሚወጣ ወጥ ምርት አይደለም። የተለያየ ፍላጎት፣ ምርጫና ዝንባሌ ስለሚኖረው። አሥር በመቶ እንኳ ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ አያንፀባርቅም። የፌዴራሊዝም ባለሙያዎችና አገራዊ የውክልና ተቋማት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ማንፀባረቅ አለባቸው ይላሉ። ስለዚህ ኢሕአዴግ አሽነፍኩ ያለበት ሒደትም የታወጀው ውጤትም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ጭምር ነው። ውጤቱ ሲነገር ስቀን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አደጋው ፈጦ እያየነው ነው። ኢሕአዴግ ማሸነፍ አይችልም ነበር እያልኩ አይደለም፡፡
ሪፖርተር፡- እየታየ ያለው የአስተዳደር ቀውስ የሥርዓት ችግር (Systemic Problem) ነው ብለው በቅርቡ በጻፉት ጽሑ ላይ ተከራክረውነበር። በመፍትላይም የሰጡት አስተያየት ነበር። ሥርዓታዊ ችግር ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ጄኔራል አበበ፡- መንግሥት ችግራችን የመልካም አስተዳደር ነው ብሎ ትልቁን ምሥል ወደ ጎን ትቶ ነገሩን ወደ ቴክኒካዊ ደረጃ አውርዶ ነው እያየ ያለው። እየተወሰደ ያለው ዕርምጃም ሥርዓቱን እንደ ሥርዓት የሚገመግምና የሚያስተካክል ሳይሆን፣ ታችኛው አመራርና ሲቪል ሰርቫንቱን ማዕከል ያደረገ ቁንፅል ነገር ነው። እኔ ደግሞ የምለው ‹‹ችግሩ ተራ የአስተዳደር ችግር ሳይሆን አጠቃላይ የዴሞክራሲ እጥረት የሚባል ነገር ነው፣ በአጭሩ ጉዳዩ የዴሞክራታይዜሽን ችግር ነው፤›› ነው። ጉዳዩ ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትና አሠራሮች ከመሥራት ወይም ካለመሥራታቸው የተያያዘ ነው። ቀላል ነገር አይደለም። መዋቅራዊ ችግርን አድበስብሶ ማለፍ ውጤቱ እስከ አገር ማፍረስ ሊዘልቅ ይችላል፡፡ ነገርየውን መመርመርና መፈተሽ ያለብንም ከዚህ አቅጣጫ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የሕዝቡን የተደራጀና የተናጠል ትግል ለማፈን የሚደረጉ ነገሮች ስለችግራችን ስፋትና ዓይነት ብዙ ነገር ይነግሩናል።
ሲቪል ማኅበረሰቡም ቢሆኑ የፓርቲ ተቀጥያ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ያለው፡፡ ሥራ ለማግኘት አባልነትና ድጋፍ መለኪያ ሲሆን ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ጥሰት መሆኑን መገንዘብ አለብን። ለምሳሌ ኦሮሚያ ውስጥ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ብንመለከት ለዴሞክራሲ ትልቅ ግብዓት ይሆን ነበር፡፡ መንግሥት ብስለቱና ብልኃቱ ስለሌለው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ፅንፈኞችና አክራሪዎች ሕዝቡ በማይፈልገው መንገድ ለመጠቀም ችለዋል፡፡
እነዚህ ኋላቀር ፅንፈኞች ደግሞ ይህንን ተገቢ ትግል በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲሰፍንና ግጭት እንዲቀሰቅሱበት ለመጠቀም ሞከሩ፡፡ በተወሰነ ደረጃም ተሳካላቸው። ጥያቄው ሕዝቡ ወዳልፈለገው አቅጣጫ ለመውሰድ የሞከሩ ፅንፈኞች የአቅማቸውን ያህል ቢጥሩም የሕዝቡ ጨዋነት ግን የሚገርም ነበር፡፡ ይህ ጨዋ ሕዝብ ላይ የደረሰው ሞት፣ የአካል ጉዳትና ውድመት በጣም አሳዛኝ ነው። ከዚህ ሒደት የምንማረው በገዢው ፓርቲና በሕዝቦች መካከል ትልቅ ክፍተት እንዳለ ነው። ሕዝቦች በገዢው ፓርቲ መሪነት አንድ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ኢሕአዴግ ግን  ቆሟል ወይም ወደኋላ እየነጎደ ነው። ከሕዝቦች ፍላጎትና ዕድገት ጋር አብሮ መሄድ አልቻለም።
ሪፖርተር፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ‹‹ሕዝቡን አስለቅሰነዋል፣ በድለነዋል››ብለዋል። ይቅርታምጠይቀዋል።
ጄኔራል አበበ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንደዚያ ማለታቻው የሚመሠገን ተግባር ነው፡፡ አንድ ዕርምጃ ወደፊት መሄድ ነው። በኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሩ በኩል የሚገለጸው ነገርም አንዳንዴ ተስፋ የሚሰጥ ነው። ይቅርታ ማለት ሕዝብን ማክበር ነው፣ ትልቅነት ነው። ይቅርታ ማለት መጀመሩ በራሱ እንደ ትልቅ ነገር አድርጌ ነው የምቆጥረው። ለዚህም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይቅርታ ብቻውን ግን በቂ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ችግሩ መላውን ኢትዮጵያ የሚያስለቅስ ከሆነ ነገሩ ሥርዓታዊ ነው ማለት ነው። ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበትም ይህ ችግር ከየት ይመነጫል የሚለው ነው። የፍትሕ መጓደል፣ ሙስና፣ አስተዳደራዊ በደል በተለያየ መጠን ይኖራሉ፡፡ ሆኖም የዴሞክራሲ ምኅዳሩ ሲጠብ ችግሮቹ ይጎለብታሉ፡፡ በተቃራኒው የዴሞክራሲ ምኅዳሩ ሲሰፋ ችግሮቹ ይቀጭጫሉ፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ይሳተፋል፡፡ በሰላማዊ ሠልፍ፣ ሐሳቡን በነፃነት በመግለፅ፣ በነፃ በመደራጀትና በመሳሰሉት ይሳተፋል። ኢዴሞክራሲያዊ ኃይሎችና ክራይ ሰብሳቢዎችን ይታገላቸዋል ማለት ነው፡፡ ለግላዊና ለቡድናዊ መብቱ ዘብ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ችግሩን ሲገመግሙ ከላይ ከቁንጮው ነበር መገምገም የነበረባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የቀረበው ጥናት ጥሩ ነበር፡፡ ቀጣይ ዕርምጃዎቹ ግን መሠረታዊ ስህተት ነበረባቸው፡፡ ከላይ መጀመር ሲገባው የሆነው በተገላቢጦሽ ነበር።
ሪፖርተር፡- ‹‹በተገላቢጦሽ›› ሲሉ ምን ለማለት ነው?
ጄኔራል አበበ፡- ጥናቱ መገምገም የነበረበት መዋቅራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ነበር። በፓርቲና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት፣ የዳኞች አሿሿም፣ የከፍተኛ ባለሥልጣናት የምልመላና የግምገማ ሥርዓት፣ በፓርላማውና በሥራ አስፈጻሚው መካከል ስላለው ግንኙነት፣ የሚዲያው ሁኔታ፣ የፍርድ ቤቶች ነፃነት ነበር መገምገም የነበረበት፡፡ በፓርቲውና በሕገ መንግሥቱ መካከል የሐሳብ ቅርበት ወይም ልዩነት አለ ወይ ብሎ መገምገም ነበረበት። ነፃ የሆኑ የሕዝብ አደረጃጀት አለ ወይ? የግል ፕሬሱና ሲቪል ማኅበረሰቡ በነፃ ይንቀሳቀሳሉ ወይ? ፓርቲዎቹስ መተንፈሻ አግኝተዋል ወይ ብሎ መታየት አለበት። ሲጠቃለል ሕዝቡ ትርጉም ያለውና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ እንዲያደርግ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ ብሎ ነው መገምገም ያለበት። በአስገዳጅ ስብሰባዎች እጅ እንዲያወጣ ማድረግ አይደለም ተሳትፎ ማለት። አንዳንድ በጎበኘሁዋቸው አካባቢዎች ‘አንድ ለአምስት’ የሚባል አደረጃጀት አደገኛ የስለላ መዋቅር እየሆነ ነው። ማኅበራዊ እሴቶቻችንን የሚበጣጥስና ማኅበራዊ ኑሮን ሊያናጋ በሚችል መንገድ ሥራ ላይ እየዋለ ሳይ በጣም ደንግጬያለሁ። ባልና ሚስት፣ ልጆችና ወላጆች በአጠቃላይ ቤተሰብ ቤተሰቡን የሚሰልልበትና የሚያስፈራራበት አሠራር እየሆነ ያለበት አጋጣሚ ስላለ ቆም ብሎ ማሰብ ይጠይቃል። ቤተሰብን ይበትናል። አደረጃጀቱም በኃይል ስለሆነ ግለሰባዊ ቅንነትንም ይገድላል። ስለዚህ ኢዴሞክራሲያዊ እየሆነ የመከባበር፣ የመተማመንና የአብሮነት እሴቶችን ይገድላል። በዘመናት የተገነባ እሴት በዓመታት ዋጋ ቢስ ሆኖ ብዙ ዋጋ እንዳያስከፍለን እሠጋለሁ።
ሪፖርተር፡- በቅርቡ በትግራይ ክልል የእምባሰነይቲ ሕዝብ ‹‹ወረዳችን ይመለስልን›› የሚል ጥያቄ አንስቷል። ይህ ሕዝብ የሕወሓት ኮር ቤዝ የሚባልነበር። በድርጅቱየተሰጠው መልስና ጥያቄው እንዴት ያዩታል?
ጄኔራል አበበ፡- በመጀመርያ የእምባሰነይቲ ሕዝብ እንደዛ ጨዋነት በተሞላው፣ የሞራል ልዕልናውን ባረጋገጠ መንገድ ጥያቄውን በተደራጀ መንገድ ማቅረቡ ሊያስመሰግነው ይገባል፡፡ እኔም በግሌ ያለኝን ልባዊ አክብሮት መግለጽ እወዳለሁ። በዚህ ሒደት ሁለት ነገሮች አሉ። የሕዝቡ ተገቢ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ መንግሥትም ያገባኛል ማለቱ የግድ ነው፡፡ የበጀትና ተያያዥ ነገሮች ስላሉ። መንግሥት ግን ሲያገባው እንዴት ነው መልስ የሚሰጠው የሚለው መታየት አለበት። መጀመሪያ ጥያቄ ለምንድነው ወረዳ የሚፈልገው የሚለው ከሕዝቡ ፍላጎት ጋር አስተሳስሮ መመለስ ነበረበት፡፡ ይህ ለሃያ ዓመታት የቆየች ችግር በጥናት በተረጋገጠ መንገድ አልተመለሰም። የሕዝቡን ጥያቄ አክብሮ ከማዳመጥ ይልቅ የት ትደርሳላችሁ የሚል የትዕቢት መልስ መንግሥት መስጠቱን ሕዝቡ በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ገልጿል፡፡ ይህ አሳፋሪና አሽማቃቂ መልስ ነው። ይህ ሕዝብን መናቅ ነው፡፡ ሕዝብን ማዳመጥ እየጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ከሕዝብ ጋር ሆነህ መፍትሔ መሻት የሚባል ነገር የለም ማለት ነው። ሰማንያ አንድ ወረዳ ቢፈጠር ለልማት እንቅፋት ይሆናል የሚል ሥጋት እንኳን ቢኖራቸው፣ ሥጋታቸውን ከሕዝቡ ጋር ሆነው ተመካክረው ወረዳ መሆን የሚሰጠውን ጥቅም በሆነ አሠራር ሕዝቡ እንዲያገኝ ለማድረግ ፍላጎት አለማሳየታቸው ያሳዝናል። ነገሩን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ ጥያቄው የእምባሰነይቲ ብቻ አለመሆኑን እያወቁ ማስፈራራትን እንደ መፍትሔ መውሰዳቸው ነው።
ችግሩ የኪራይ ሰብሳቢ፣ የጥገኛ አመራር፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ሴራ አድርገው ማየታቸው ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው አይመስለኝም፡፡ ሕዝቡን ሞኝ ነህ፣ ተታለህ ነው፣ ስለራስህ ምንም አታውቅም እያሉት ነው። ይህ ደግሞ ከማሳዘን አልፎ ከባድ አላዋቂነት ጭምር መሆኑን ነው የሚያሳየው። በኦሮሚያም የተባለው ተመሳሳይ ነው፡፡ በሁሉም ክስተቶች የእገሌ የእገሌ እየተባለ ሕዝብን ማሸማቀቅ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ሲጀመር መንግሥት የት ነበርና ነው?
ሪፖርተር፡- ከኦሮሚያ ቀጥሎ በቅርቡ የታጠቀ ኃይል በሕገ መንግሥታዊ ተቋማት ላይ የበላይነት ከያዘ፣ የፖለቲካ ፍላጎት ሊያሳድር ይችላል የሚል አስተያየትም ሰጥተው ነበር፡፡ ዕውን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሥጋት ይኖራል?
ጄኔራል አበበ፡- የደኅንነትና የዴሞክራሲ እጥረት ዋናው የድህንነታችን ጥያቄ ነው። በአፍሪካ እንደምናየው የታጠቀው ኃይል ከትጥቅ በላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ተፅዕኖ አለው። በሲቪል ቁጥጥር ሥር ካልዋለ ራሱን ንጉሥ ወይም አንጋሽ የመሆን ፍላጎት ሊያዳብር ይችላል። ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት ሕጉ በሚያስቀምጠው መንገድ መሥራት ካልቻሉ አጠቃላይ መዛባት ይፈጠራል። ሕገ መንግሥቱ በተለያዩ ተቋማት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት በሥርዓቱ ደንግጓል፡፡ ሕጉ በተገቢ መንገድ በማይተገበርበት ጊዜ ግን መዛባት ይፈጠርና ጉልበት የበላይነት ያገኛል። ሥልጣን አስፈጻሚው ዘንድ ሲጠቃለል የመጀመሪያው የአደጋ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከአስፈጻሚው ጋር ደግሞ ሲቪልና የደኅንነት አካላት አሉ። እዚህ ጋ መዛባት ሲፈጠር ጠቅላላ ኃይሉ ወደ ታጠቀው ይጠቃለላል። ካልተዛባ ቦታውን ይይዛል፣ አገሩንም ይጠብቃል፣ የውጭ ጠላትን ይመክታል ይከላከላል። ካልሆነ ግን ፖለቲካዊ ፍላጎት አዳብሮ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። ሕገ መንግሥቱ መሠረት ተደርጎ ካልተኬደ ሲቪሉ በታጠቀው ኃይል ሥር ይወድቃል። አሁን አንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ነው። ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር ተያይዞ የተሰማው ነገር የዚህ ምልክት ነው እንዴ? እንድትል ያደርጋል።
ሪፖርተር፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየመን የሳዑዲ ዓረቢ እንቅስቃሴ አለ፡፡ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂ ቡድኖች በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ላይ ብዙጉዳት አድርሰዋል፡፡ቀጣይነት ያለው ከኤርትራ የሚመጣ አደጋ አለ። እርስዎ እንደ የሰላምና የደኅንነት ባለሙያና የቀድሞ ጄኔራል እንደመሆንዎመጠን በዚህ የደኅንነት ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ?
ጄኔራል አበበ፡- ባለሙያ ለመባል እንኳን ያስቸግረኛል። ጋምቤላ ላይ የተፈጠረው ትልቅ ጉዳይ ነው። ብዙ ሰው ነው የሞተውና የተጎዳው። ለቤተሰቦቻቸውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፅናቱን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ። ለብቻው ስታየው የሚያጋጥም ነገር ነው ለማለት የሚቻል ይሆናል። ነገር ግን ብዙ ጥያቄዎች ያሉበት ነው። ሙርሌዎች እንዴት ብለው ነው ልባቸው ሞልቶ ለቀናት ተዘጋጅተውና ሠልጥነው ያጠቁት? እንዴት ብለው ነው የደፈሩት? እዚያ አካባቢ ያለው የደኅንነትና የመከላከያ ኃይሎች ምን ይሠሩ ነበር? በአካባቢው ሠራዊት ነበር? አልነበረም? ለምንድነው በአጭር ጊዜ ምላሽ ያልተሰጠው? ሕፃናቱን ማስመለስ ለምንድነው የዘገየው? ሲደጋገምና ተመሳሳይ ክስተቶች በርከት ብለው ሲታዩ ጥያቄ መነሳቱ የግድ ነው። ይኼ ነገር የሥርዓቱ ችግር ሊሆን ይችላል ተብሎ ከብሔራዊ የደኅንነትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ከፖሊሲው ማኔጅመንት፣ ከሥራ አስፈጻሚውና ከተወካዮች ምክር ቤት ሚና ጋር አያይዞ ማየት ያስፈልጋል። የሥርዓቱ በሽታ ማሳያ ሊሆን ይችላል። ፓርላማው ሐዘን ከማወጅ የዘለለ ለምን ተከሰተ ብሎ አስፈጻሚውን መጠየቅና ማጣራት አለበት፡፡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥንም ቢሆን ይህ ነገር ለምን ተከሰተ ተብሎ ሊጠየቅና ማብራርያ ሊሰጥ ይገባዋል። መከላከያ ሚኒስትሩም እንዲሁ። ይህ ክስተት ሥርዓቱን እያስተካከልን እንሄዳለን የሚል በጎ አስተሳሰብ ካለ አጠቃላይ ሥርዓቱን ለመፈተሽ ይጠቅመናል፡፡ ክስተቱ የውድ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑ ሳይረሳ።
ሳዑዲዎች የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች ላይ የጦር መርከቦቻቸው ሲያሰፍሩ ኢትዮጵያን አንነካም፣ ዓላማችን የመን ላይ ነው እያሉ ይምላሉ ይገዘታሉ፡፡ እኛ እንደ ሞኞች ብለውናል ብለን ነው መሄድ ያለብን? የፈለጉትን ነገር ለማድረግ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው? ሳዑዲ ዓረቢያ አሥራ አምስት ቢሊዮን ዶላር አካባቢ በሱዳን ኢንቨስት እያደረገች ነው፡፡ ለሱዳን ወታደራዊ ድጋፍ እየሰጠች ነው፡፡ ሱዳን ሠራዊትዋን ወደ የመን ልካለች፡፡ በሳዑዲና በኢራን መካከል ከነበረው ፍጥጫ ተነስተው ሱዳንና ሶማሊያ ከኢራን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቋርጠዋል። ይኼ የሱዳንና የኢራን እንጂ እኛ ጋ ሊከሰት አይችልም የሚባል ነገር ልክ አይደለም። አጠቃላይ ሁኔታው ምን ይመስላል የሚለው ነገር መጤን አለበት። የኤርትራም ጉዳይ ከዚህ ጋር ተያይዞ ነው መታየት ያለበት።
ሪፖርተር፡- በቀጣናው እየታየ ያለውን የደኅንነት ሥጋት ለመቆጣጠር ከውስጥ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?
ጄኔራል አበበ፡- በዚህ ጊዜ ደግሞ ለዘመናት የኢሕአዴግ ባህል የነበረው የጋራ አመራር እየጠፋ ነው፡፡ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ባልተቋመበት፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጽሕፈት ቤት ባልነበረት ሁኔታ አደጋ ተከስቷል። በዚህ ላይ አንድ የጻፍኩት ጽሑፍ አለ። በጥናቴ ያገኘሁት ነገር ቢኖር ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በአዋጅ ቢቋቋምም፣ ሴክሬታሪያት የሌለውና አልፎ አልፎ እንደሚሰበሰብና የተጠናከረ አደረጃጀት እንደሌለው ነው። የዚችን ትልቅ አገር ደኅንነት በዚህ መልኩ መያዝ የለበትም፡፡ ጥንቃቄና ጥልቅ ትንተና የግድ ነው። ከየዘርፉ ምሁራን መሰብሰብ አለባቸው፡፡ ሥጋቶችና ፀጋዎች በደንብ መለየት አለባቸው፡፡ ትንበያዎችና ቅድመ ዝግጅቶች መደረግ አለባቸው። ነገሮች ከተፈጠሩ በኋላ እሳት ለማጥፋት አይደለም መሮጥ ያለብን፡፡ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት የሚያስችል አቅም ልንገነባ ይገባናል፡፡ ታላቅ አገር ይዘን ንህዝላል መሆን አንችልም። የሁሉም የትምህርት ተቋማት፣ ኤምባሲዎችና ቆንፅላ ጽሕፈት ቤቶች፣ የደኅንነትና የወታደራዊ መረጃ፣ የቲንክ ታንኮችና ዓለም ላይ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎችን መሠረት እያደረገ ሴናርዮዎች (ቢሆኖች) ማቅረብ የሚችል በትልቅ አቅም የሚንቀሳቀስ የደኅንነት ሴክሬታሪያት ያስፈልገናል። ለምሳሌ ከተቋማዊ አሠራር አቅጣጫ ብናየው በተከታታይ የኤርትራ መንግሥት ሉዓላዊነታችንን እየደፈረ ዜጎቻችንን ይጠልፋል፣ አልፎ አልፎ ይመለሳሉ፡፡ ፓርላማው ግን አንድም ቀን ቢሆን አስፈጻሚውን ለምን እንዲህ ሆነ ብሎ ሲጠይቅ ዓይተን አናውቅም። ሙርሌዎች እንደዚህ ሲያበሳብሱን ፓርላማው ለምን ማለት ነበረበት፡፡ የሚመለከተው አካል መጠየቅና ኃላፊነት መውሰድ ነበረበት።
ሪፖርተር፡- ከኢሕአዴግ ነባር አመራሮች ወጣ ያ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ያጣችው ‹‹በኢሕአዴግ አላዋቂነት ነው›› ብለዋል፡፡ በጥናታዊጽሑፍዎ ድምዳሜምሰፍሮ ይገኛል። እውነት ሕጋዊ መሠረት አለን ማለት ነው?
ጄኔራል አበበ፡- ድሮም ቢሆን የኤርትራን ነፃነት ተቀብለው የአሰብ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ። እንደነ አቶ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ አቶ ስየ አብርሃ፣ አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ እኔም ጥያቄዎች የምናነሳበት ሁኔታ ነበር፡፡ በዝርዝር ባንወያይበትም። አሜሪካ ሄጄ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስሠራ ግን በዚህ ላይ ጥናት አካሂጄ የባህር በር መብታችንን በሕጋዊ መንገድ ማስመለስ እንደምችል የሚያረጋግጥ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። ባለማወቅና በመታበይ (Ignornace and arrogance) ያጣነው መብት ነው፡፡ አሁንም ግን ሕጋዊ መሠረት አለን፡፡ ዝርዝር ነገር የሚፈልግ ካለ የመመረቂያ ጽሑፌ ላይ አስፍሬዋለሁ፡፡
ሪፖርተር፡- በአሰብ ጉዳይ ላይ ካደረጉት ጥናት ውጪ በተግባር የመሥራት ዕቅድ አለዎት?
ጄኔራል አበበ፡- አዎ፡፡ የአገር ጉዳይ ስለሆነ ነው። በእኔ አረዳድ የባህር በር ሳናውቅ ያጣነው አገራዊ ፀጋችን ነው። በእርግጥ የባህር በር ጉዳይ ከአጠቃላይ ሕገ መንግሥታዊና ፖለቲካዊ ሥርዓቱ አንፃር ካልታየ የወራሪነት ባህሪ ያለው አደገኛ ነገር ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህም ተጠንቅቄ የማነሳው ጉዳይ ነው። የባህር በር ጉዳይ በጣም አስፈላጊ ነው ስል የሞት ሽረት ጉዳይ አድርጌ አላየውም። ከኢኮኖሚም ከፀጥታም አኳያ በጣም ያስፈልገናል፡፡ ግን ሕጋዊና ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ነው መሆን ያለበት። አሁን ያለውን ሥርዓትና መሠረታዊ የፖለቲካ እሴቶቻችን በሚንድ መልኩ መሆን የለበትም። አሁን ያለን ሕገ መንግሥት ለሌሎች ሕዝቦችና አገሮች አርዓያ መሆን የሚችል የዳበረ ሕገ መንግሥት ነው። ስለዚህም የአሰብ ጉዳይ ተነስቶ ሕገ መንግሥቱን ለመሸርሽርና ለመናድ በሚደረግ እንቅስቃሴ አልሳተፍም። ይህ ሕጋዊ መብታችን ግን መረጋገጥ አለበት ብዬ ስለማምን በቻልኩት መጠን እንቅስቃሴ አድርጋለሁ።
ሪፖርተር፡- ኢሕአዴግ ከክፍፍሉ ከ1993 ዓ.ም. በፊትና በኋላ እንደ ድርጅት ውስጣዊ ጥንካሬው እንዴት ያዩታል?
ጄኔራል አበበ፡- ኢሕአዴግ በ1993 ዓ.ም. ቀውስ ውስጥ ሲገባ የድርጅቱ አባል አልነበርኩም፡፡ የአየር ኃይል አዛዥ ነበርኩ። ስለዚህ ድርጅት ውስጥ የነበረውን ነገር በዝርዝር አላውቅም፡፡ ሆኖም ከሁለቱም አንጃዎች በኩል የትጥቅ ጊዜ ጓደኞቼ ስለነበሩ በሁለቱም ጎራ የነበረውን ሁኔታ እሰማ ነበር። ከድርጅቱ ጋር በነበረን ሥነ ልቦናዊ ትስስርም ድርጅቱ እንዲፈርስ አንፈልግም ነበር። ቁውሱን ለመፍታት የተደረገው ድርጊት ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ያሳደረ ነበር። ሒደቱ እልባት ያገኘው ኢዴሞክራሲያዊና ኢሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ነበር። የመንግሥት ሚዲያ የአሸናፊው አንጃ ሚዲያ ሆኖ ተሸናፊው አንጃ ሐሳቡን የሚገልጽበት ዕድል ተነፍጎ፣ ጄኔራሎችም ጭምር በጉዳዩ ፖለቲካዊ መግለጫ የሰጡበት ሕገ መንግሥታዊነት፣ ፌዴራሊዝምንና የድርጅትን ሕገ ደንብ ገደል የከተተ ሒደት ነበር። ለስዬ ተብሎ ሕግ እስከማውጣት ድረስ ተኪዷል፡፡ ፍርድ ቤት ሲለቀው ፖሊስ በጉልበት ይዞታል። በአጠቃላይ የቀውስ አፈታት ሒደቱ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን የተወው ትምህርትም አደገኛ ነው። በውስጥ የፓርቲዎችን መብትም የናደ ነበር። በተለይ ኦሕዴድና ደኢሕዴን ላይ የተሠራው ሥራ ህልውናቸውንና ነፃነታቸውን በሚንድ መልኩ ነበር የተካሄደው። በዚያ መልኩ መለያየታችን ያሳዝነኛል።
ሪፖርተር፡- በ1993 ዓ.ም. የተከሰተውን ቀውስ በመፍታት ረገድ የታየው ፀረ ዴሞክራሲ አሠራር ከዚያ በፊት አልነበረም ይላሉ?
ጄኔራል አበበ፡- መለያየቱ ራሱ የነበረውን አቅም የበተነ ነበር፡፡ ትልቅ ብቃትና ዕውቀት የነበራቸው ሰዎች በአገር ግንባታ እንዳይሳተፉ ያደረገ ነገር በመሆኑ ያሳዝነኛል። በተጨማሪም አሸናፊው አንጃ የደኅንነት መዋቅሩን የሰው መብት በሚጥስና ፍራቻን ለማንገሥ ባለመ ሁኔታ ነበር ሲያንቀሳቅስ የነበረው። እንዲህ ዓይነት ዝንባሌዎች ከዚያ በፊት አልነበሩም ማለቴ አይደለም። ምናልባት እኛ ላይ ስለተፈጸመ ሊሆን ይችላል ያስተዋልነው ወይም መጠኑ ከፍ ብሎ ሊሆን ይችላል። በሰዓቱ የነበረን አስተሳሰብ ‹ከኢሕአዴግ መስመር ውጪ ሁሉም የጥፋት መስመር ነው› ብሎ የሚያምን ስለነበር ተቃዋሚዎችን እንደ ፀጋ የማያይ፣ እግራቸውን እንዳይተክሉ የሚያደርግ አስተሳሰብ ነበር፡፡ ጎልቶ የታየን ግን እኛ ላይ ሲደርስ ነው። ስለዚህ 1993 ዓ.ም. ብቻውን መለያ አይሆንም። እንደኔ አመለካከት ኢሕአዴግ የተሻለ ዴሞክራቲክ ድርጅት ነበረ ብልም ሙሉ በሙሉ ዴሞክራቲክ ነበር ለማለት አልችልም። ከቀውሱ በፊት ፓርላማው ማኅተም መቺ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቶች ነፃነት አልነበራቸውም፡፡ ‹ቼክ ኤንድ ባላንስ› የነበረበት የሥልጣን ክፍፍል አልነበረም፡፡ ከዘጠና ሦስት በኋላ ግን ባሰበት።
ሪፖርተር፡- ለወጣቱ ትውልድ ምን ይመክራሉ?
ጄኔራል አበበ፡- ወጣቱ ትውልድ ያለፈው ትውልድ የሠራውን ሥራ ዕውቅና እየሰጠ ሲያበላሽ ደግሞ አታበላሽ ማለት መቻል አለበት፡፡ ያለውን ብልሽት ለማስተካካል መሥራት አለበት፡፡ ማማረር ብቻ መፍትሔ አይሆንም። በምሬት መጀመር ባህርያዊ ነው። ወጣቱ ትውልድ በሚያምንበት አደረጃጀት እየገባ መታገል አለበት። በግልና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሸሸጉ ማፊያዎችን መታገል አለበት። አገሪቷ በመስቀለኛ መንገድ ነው ያለችው፡፡ የወጣቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። በፌስቡክም፣ በትዊተርም፣ በየጋዜጣና በየመጽሔቱ በትጋት የሚሳተፉ ወጣቶችን በርቱ ማለት እወዳለሁ።

Saturday, May 28, 2016

የትምባሆ ሞኖፖል ለጃፓን ኩባንያ ተሸጠ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

የግንቦት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (May 27, 2016 NEWS)
#የትምባሆ ሞኖፖል ለጃፓን ኩባንያ ተሸጠ
#የግብጽ አውሮፕላንን በመፈለግ ላይ የሚገኙት ባለሙያዎች በራዲዮ መገናኛ አንድ መሳሪያ አገኙ
#የእንግሊዝ የጦር መርከቦች ወደ ሊቢያ ሊላኩ ነው
#የጣሊያን ጠረፍ ጠባቂዎች ከ4000 በላይ ስደተኞችን አዳኑ
#በጊኒ ቢሳዎ የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ አባላት በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
 የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ንብረት የሆኑትን መሸጥና መዝረፍ መለያ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ከአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በሕዝብ ሀብትነት የተመዘገበውን የትንባሆ ሞኖፖል ለጃፓኑ ኩባንያ መሸጡ ታውቋል። ወያኔ የሽያጩን ውል በሚመልከት ከኩባንያው ጋር በቅርቡ አንድ ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖልን ለመግዛት አንድ የእንግሊዝና የአሜሪካ ኩባንያ 230 ሚሊዮን ዶላር አቅርበው እንደበርም ታውቋል። ጄቲ የተባለው የጃፓን የትንባሆ ኩባንያ ግዥውን መፈጸሙን ሲገልጽ በአፍሪካና በመካከለኛ ሰፊ ገበያ እንዳለውም ተገልጿል። የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ጀመሮ በሕዝብና በአገር ስር የነበሩ ንብረቶችን በመሸጥ የወያኔ መሪዎችን ያከበረ መሆኑ ይታወቃል።

tobaco 

ከጥቂት ቀናት በፊት ከፓሪስ ወደ ካይሮ በመብረር ላይ እንዳለ ባልታወቀ ምክንያት በሜዲትራኒያን ባህር የወደቀውን የግብጽ የመጓጓዣ አውሮፕላን ስብርባሪ በተለይም ድምጽን እና የሁኔታ መረጃዎችን የሚቀርጹትን መሳሪያዎች በመፈለግ ላይ የሚገኙት ባለሙያዎች አንድ ከአውሮፓላኑ ካቢን በስተርጅባ የሚገኝና አውሮፕላኑ ያለበትን ቦታ መረጃ አሰባስቦ የሚያስተላልፍ መሳሪያ በራዲዩ ግንኙነት ያገኙ ሲሆን ይህ መሳሪያ ከተገኘ ምናልባት በአውሮፕላኑ ውስጥ የሚሰሙ ድምጾችንና የሁኔታ መረጃዎችን የሚቀርጹት መሳሪያዎችም አብረው ሊገኙ ይችላሉ የሚል ተስፋ ከፍ ብሏል። የድምጽና የሁኔታ መረጃ መቅረጻዎች የሚቀመጡት በአውሮፓላኑ መጨረሻ ላይ ነው። የተገኘውን የራዲዮ መገናኛ መሰረት በማድረግ ፈላጊዎቹ በሚቀጥሉት ቀናት ጥልቅ በሆነው ውሃ ውስጥ ፍለጋቸውን አጠናክረው የሚያካሄዱ መሆናቸው ተገልጿል። 66 መንገደኞችንና የአውሮፕላን ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረውና የግብጽ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ለወደቀበት ምክንያት የተለያዩ ግምቶች ይሰጡ እንጅ የመውደቁ ምክንያት ይህ ነው የተሰጠ መደምደሚያ የለም ። አውሮፕላኑ ከራዳር ውጭ ከመሆኑ በፊት በመታጠቢያ ቤቱና በሌላው የአውሮፕላኑ ክፍል እሳት መነሳቱን የሚያሳይ መረጃ መሬት ላይ ባለ መሳሪያ ተመዝግቧል የሚል ዜና መሰራጨቱ ይታወሳል።
 የእንግሊዝ የጦር መርከቦች ወደ ሊቢያ የሚላኩ መሆናቸውን የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኪዮ ላይ ለተሰበሰበው የሰባቱ ሃብታም አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ገልጸዋል። የጦር መርከቦች ከሊቢያ ወደ አውሮፓ የሚጎርፍ ስደተኞችን በመቆጣጠርና ህገ ወጥ አስተላላፊዎችን በመያዝ ስራ ላይ እንደሚሰማሩ እንዲሁም በዚህ በኩል እንግሊዝ ቀዳሚ ሚና እንደምትጫወት ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት የሊቢያ የአንድነት መንግስት ከአውሮፓ ህብረት ወታደራዊ እርዳታ የጠየቀ ምመሆኑ ሲታወቅ ከተጠየቁት እርዳታ ውስጥ የሊቢያን የጠረፍ ጠባቂዎች በወታደራዊ ትምህርት ማሰልጠንና ስደተኞችን በመቆጣጠር በኩል ሊጠቅሙ የሚችሉ ወታደራዊ መሳሪዎችን የሚጨምር መሆኑ ይታወሳል።
 በተያያዘ ዜና ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2008 ዓም የጣሊያን ጠረፍ ጠባቂዎችና ሌሎች ከ4000 በላይ ስደተኞች ከሞት አደጋ ያዳኑ መሆናቸው ሲገለጽ ከሊቢያ ጠረፍ አጠገብ ሁለት ጀልባዎች በመግልበጣቸው ከ100 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በባህር ውስጥ ሳይሰጡ አይቀርም የሚል ግምት ተወስዷል።
 የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት ሕገ መንግስቱ ከሚፈቅድላቸው ውጭ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሾማቸው የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ ደጋፊዎች በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤተ መንግስት አካባቢ ተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ጥቃት የፈጸሙ መሆናቸው ተዘግቧል። በሕገ መንግስቱ መሰረት ገዥው ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መሰየም ሲገባው የፓርቲው አባል የሆኑት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በማን አለብኝነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሾመው በስራ ማስቀመጣቸው ከፓርቲው ባለስልጣኖች ጋር ቅራኔ ውስጥ የጨመራቸው መሆኑ ታውቋል። ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2008 በመቶ የሚቆጠሩ የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች ቤበተ መንግስቱ ላይ ድንጋይ በመወረወና የላቲክ ጎማዎችን በማቃጠል ተቃውሟቸው የገለጹ መሆናችው ተነግሯል።

Friday, May 27, 2016

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?

ሥራየ መምህርነት ነው፡፡ በአንድ የመንግሥት የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ አስተምራለሁ፡፡ ሰሞኑን ታዲያ የግንቦት 20 የኢትዮጵያ የነፃነት ቀን እንደመሆኑ የበዓሉን መቃረብ አስታክኬ በየምገባባቸው በርካታ ክፍሎች ትምህርቱን ከመጀመሬ በፊት “እንኳን አደረሳችሁ” እላለሁ፡፡ ይሀንን የምለው ኢሕአዲግ መራሹ ዴሞክራሲያዊው መንግሥታችን ጨቋኙን የደርግ መንግሥት ደምስሶ ሕዝባዊ መሠረት የተላበሰና በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመትከሉ ነው፡፡ በግንቦት 20 1983 ዓ.ም የተመሠረተው ይህ በሕዝቦች መፈቃቀድ የተገነባ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ኢትዮጵያን ከመፈራረስና እንደሶማሊያ ከመበታተን የታደገ በመሆኑ ዕለቱ ብቻ ሣይሆን ወሩ በሙሉ በድምቀት ቢከበርና ለዚህ የላቀ ማኅበረሰብኣዊ ደረጃ ያደረሱን እንደክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መለስ ዜናዊና አባይ ፀሐዬን የመሰሉ ዕንቁ ታጋዮቻችንም ቢወደሱ አግባብ ነው ብለን የምናምን ኢትዮጵያውን እጅግ ብዙ ነን – በሀገር ውስጥም  – ወላ ከሀገር ውጪም፡

TTPLF


ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አንዳንድ የዴሞክራሲ ምንነት ገና ያልገባቸው ተማሪዎችና መምህራን በዚህ ታላቅ በዓላችን ላይ ሲያላግጡና ሲያሾፉ ስመለከት በጣም እበሳጫለሁ፡፡ ሀገራችን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲን ለማየትና በተግባር ለማጣጣም በመታደሏ መደሰትና ጮቤ መርገጥ ሲገባን ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ በማቆጥቆጥና ብሎም በማበብ እንዲሁም ሥር በመስደድ ላይ የሚገኘውን የኅብረ ብሔራዊ ዴሞክራሲና የፌዴራል ሥርዓት ለማጠየም የሚደረገው የአንዳንድ የዋህና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ተንኮል ይገርማል፤ ያሳዝናልም፡፡ የሚወራ ነገር ቢያጡ ዴምክራሲያዊው ሥርዓታችን “የጥቂት ዘረኞች ደባ የሚንጸባረቅበት ነው” በሚል አፍራሽና መሠረተ ቢስ ክስ ሕዝባዊውን ሥርዓት ለማጠልሸት በከንቱ የሚንፈራገጡ ወገኖች አሉ – ግን በጣም ጥቂት በመሆናቸው የትም አይደርሱም፡፡
እኔ በምሠራበት ትምህርት ቤት የአንድ ሕዋስ ተጠሪ ነኝ፡፡ መሪ ድርጅታችን ኢሕአዴግ ከመሰል ፓርቲዎች ጋር በእኩል ዕድልና በእኩል ሜዳ ተወዳድሮ ካሸነፈ በኋላ በሥሩ ሕዝቡን አንድ ለአምስት ሲያደራጅ ከቀዳሚ ተሰላፊ መምህራን መካከል አንዱ ነኝ፡፡ ስለዚህም በትምህርት ቤቴ የበኩሌን ድርሻ እያበረከትኩ እገኛለሁ፡፡ በተቃዋሚ ሚዲያዎች ራሴን ለማስተዋወቅ ጥረት ባደርግም እስካሁን ዕድል አልተሰጠኝም፡፡ ዛሬ የሞከርኩት ከተሳካ ግን ደስ ይለኛል፡፡ በዚያውም ልዩነቶችን ለማትበብ ይረዳል፡፡ ሰሚ አጥቶ እንጂ በሕዝባዊ ማዕበል የምርጫ ሣጥን በትረ ሥልጣን የጨበጠው ኢሕአዲግ ሥልጣን መረከብ የሚችል ሌላ ብቁ ፓርቲ ወይ የፖለቲካ ኃይል ካገኘና ተወዳድሮ ካሸነፈው በሰላም ለማስረከብ ብዙ ጊዜ ቃል ገብቷል፤ በተግባርም አሳይቷል፡፡ ለምሣሌ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከደቡብ ሕዝቦች መመረጣቸው የሚያሳየን የፌዴራሉ ሥልጣን ከአነሳው የትግራይ ብሔር ወጥቶ ወደብዙኃኑ የደቡብ ብሔር ብሀየረሰቦች የመዛወሩን ብሥራት ነው፡፡ ይህንን የሥልጣን ሽግሽግና የኃይል ሚዛን ለውጥ አሌ የሚል ሰው ቢኖር ማር እያላሱት ጨው እንግሊዝ ነው የሚል ዳተኛ ሰው ነው፡፡ ይገርማል፡፡
በሰሞኑ የደረሰብኝ የተማሪና የማህምራን ለበጣና ፌዝ ግን መቼም ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በየክፍሉ ስገባ “እንኳን አደረሳችሁ” ስል “ለምኑ?” ይሉኛል፡፡ “እንዴ! ለታላቁ የግንቦት 20 በዓል ነዋ!” ስላቸው ይስቁብኛል፡፡ “ምን የሚያስቅ ነገር ተገኘ? ‹እንኳን አደረሳችሁ› ማለት ነውር ነው እንዴ?” ስላቸው አሁንም የበለጠ ይስቃሉ፡፡ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የሚስቁብኝ ደግሞ አንድም ሣይቀሩ ሁሉም ናቸው፡፡ ያደሙብኝም መሰለኝ፡፡ ወደ ፓርቲ ጽ/ቤት ሄጄም እንደዚሁ ብል ሣቁብኝ፡፡ የነሱን ሣቅ ግን ከዐይናቸው ውስጥ ነው ያነበብኩት፡፡ ምክንያቱም ዋናው ሰብሳቢያችን አቶ ጎይቶም ሐጎስ አብሮን ስለነበረ ደፍረው በጥርስ በሚገለጥ ሣቅ ስሜታቸውን ሊያሳዩኝ አልቻሉም፡፡ ብቻ ከሁኔታቸው እንደተረዳሁት ግን ለምንም ነገር እንዳልደረስን የሚያሳብቅ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ነገር የኢሕአዲግን ያጎረሰ እጅ እንደመንከስ ነው፡፡
ግን ለምን?
ተማሪዎቼን ስጠይቅ “ጋሼ፣ ይሄ በዓል እኮ ለእናንተና ለአለቆቻችሁ እንጂ ለኛ ለተራው ሕዝብ ከመከራና ስቃይ ውጪ ያመጣልን ነገር የለም፡፡ ስደት፣ እስራት፣ የኑሮ ውድነት፣ ግርፋት፣ ሞት፣ ሙስና፣ ዘረኝነት፣… ነው ያመጣብን፡፡ ስለዚህ ለኛ እርግማናችን እንጂ በዓላችን አይደለም፡፡ የናንተው በዓል ነው፡፡ እዚያው ጨፍሩ፤ ከተራበው ሕዝብ አፍ እየቀማችሁ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለመጠጥና ለምግብ፣ ለሴትና ለዳንኪራ አውሉት፤ ነገ ግን እንደምትጠየቁበት ዕወቁ፤ እናንተ በአማራ ስም የምትነግዱ ብአዴኖች ደግሞ ያላወቅንባችሁ መስሏችኋል፡፡ በሣምንታት ዕድሜ ለደረቀ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ሁለት ቢሊዮን ብር ማውጣታችሁን ሰምተናል – በስማችን ያን ሁሉ በጀት ቀረጠፋችሁት፡፡ ውኃው ለምስኪኑ ገበሬ ቢደርስ እንኳ ብትበሉትም ምንም አልነበረም፤ ግን አንዲት ቡትሌ ውኃ ሣትሰጡት  በጥቂት ሚሊዮኖች ሊያልቅ በሚችል ቁፋሮ ሰበብ ሁለት ቢሊዮን ብር መዝረፍ የግፍ ግፍ ነው፤ ልጅ አይውጣላችሁ ” አሉኝ በማን አለብኝነት ድፍረት፤ ደግነቱ ምን እንደተናገሩ በውነቱ አልሰማሁም፤ የኮሚቴ አባል እንደመሆኔ ስለበዓሉ ዝግጅት እያሰላሰልኩ ነበር፡፡ በግማሽ ልብ እንደሰማሁት ግን እውነቱ  ይህ እንዳልሆነ ሁላቸውም ልቦናቸው ያውቃል፡፡ እንዲህ መናገራቸው ራሱ የዴሞክራሲያችን ውጤት መሆኑን ያወቁት ደግሞ አይመስሉም፡፡ ከኢሕአዴጋዊ ዴሞክራሲያችን ጋር ወደፊት!
የመምህራን ማረፊያ ውስጥ ያገኘኋቸው መምህራን ደግሞ “ለምኑ ነው ‹እንኳን አደረሳችሁ› የምትለን?” በማለት በቁጣ ነው ያበሻቀጡኝ፡፡ የለውጡን ጠቃሚነት ላስረዳቸው ብሞክርም አንድም ሰው የሰማኝ የለም፡፡ እንዲያውም አንዱ በንዴት እየፎገላ፡-
“ሰማህ ወንድም ጓድ ካድሬ! እንዲያውም ከነፃነት በኋላ ግንቦት 20 የሚባል ቀን ከናካቴው እንደማይኖር ካሁኑ ላርዳህ፤ ቁርጥህን ዕወቅ፡፡ ግንቦት 19 ይባልና በቀጥታ ወደ ግንቦት 21 ይኬዳል፡፡  ስሟን ቄስ ይጥራውና ይቺ ግንቦት 20 የሚሏት ቀን ጳጉሜ ላይ ትደረብና ከነፃነት በኋላ የምትኖረው ጭንጋፏ የጳጉሜ ወር በያመቱ 6 ቀናት ይኖራታል፤ በአራት ዓመት አንዴ ደግሞ 7 ትሆናለች፡፡ ግም-ቦት ያኔ በድምሩ 29 ቀናት ብቻ ይኖሩታል ማለት ነው፡፡ ግንቦት 20 በአሜሪካና በአውሮፓ ኃያላን ሀገራት ቡራኬ የኢትዮጵያ ውድመት ለኢትየጵያውንና ለዓለም መርዶ የተነገረበት፣ የዚህች ታሪካዊ ሀገር መፈራረስ የታወጀበት ዕለት በመሆኑ ቀኒቷ የተረገመች ናት፡፡ አሁን ለይመስልና ለታይታ ያህል የሚያከብሯትም እንደርሷው የተረገሙ ያንተው አለቆች ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህ ‹እንኳን አብሮ አደረሰን› የሚል ሰው አገኛለሁ ብህ አትድከም፡፡…” አለና ወሽመጤን ቆረጠው፡፡ ኧረ የራሱ ወሽመጥ ይቆረጥ፤ የኔስ ገና ነው፡፡
ከትምህርት ቤት ውጪም የትም ሄጄ “እንኳን አደረሳችሁ” ስል የማገኘው መልስ ተመሳሳይ ነው፤ መሣቅ የሚችሉ ይስቃሉ፡፡ የፈሩ ደግሞ ገላምጠውኝ በሆዳቸው የስድብ መዓት ያወርዱብኛል፡፡ አንዱ በሆዱ ምን አለኝ “አንት አጋሰስ ሆዳም! ቆይ ታያለህ! አሁን ሆድህን ሞላህና አብረህ ታረጠርጣለህ አይደል? ይህ ክፉ ቀን የማያልፍ መስሎህ ነው አይደል?”፡፡ እኔም በሆዴ “ መስሎሃል! ሆዴስ አልሞላም፡፡ ግን እንደዚህ ያለ የደስታና የድሎት ዘመን ሀገርህ ኢትዮጵያ መቼም አታገኝም፡፡ እንደ ኢሕአዴግ ፍትህንና ሰላምን ከነፃነትና እኩልነት ጋር አስማምቶ በሀገር ላይ የሚያነግሥ መንግሥት መቼም አይመጣም፡፡ የደርግና የቀደሙት መንግሥታት ሕዝባቸውን በውሸትና በማስመሰል ቀጥቅጠው ይገዙ ነበር፡፡ ኢሕአዲግ ግን በእውነትና በትክክለኛ ፍትሃዊ የዴሞክራሲ ሥርዓት አንዱን ጎሣ ከሌላው፣ አንዱን ሃይማኖት ከአንደኛው ሳያበላልጥና እንደቀድሞዎቹ ክፉዎች መንግሥታት ለማጋጨት ሳይሞክር ያስተዳድራል፡፡ ለዚህም ነው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሚቸግረው ነገር ሁሉ እየረዳ አቅፎና ደግፎ የያዘው” አልኩ፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባል፡፡ የርሱን ብሶት እንደሰማሁለት የኔን ምሥክርነት ሰምቶ ከሆነ እሰዬው ነው፡፡ ምነው ሁሉንም እንደኔ ልብ ሰጥቶት ኢሕአዲግን ለተጨማሪ 100 ዓመታት በመረጠው!
ግን ሰውን ምን ነካው? “እንኳን አደረሳችሁ” ሲባል ብሶቱን የሚያሰማው በርግጥ ምን ደርሶበት ይሆን? የኔ መነፅር ተበላሽቶ ይሆን ወይንስ ሕዝቡ እንዳለ ተሳስቶ ነው ልበል? የትኛውን እንደምል ጨነቀኝ፤ እስኪ ማለት ያለብኝን ንገሩኝ፡፡

ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው

በዚህ በያዝነው ወር በየዓመቱ ስለግንቦት 20 በተለያየ መልኩ ይሰበካል፣ ይገለጻል። ለሀገራችን ኢትዮጵያ ታምራዊ ለውጥ እንዳስመሰገበ ሁሉ ወሩን ሙሉ ሲተረክ መስማት እንደ ሀገራዊ መዝሙር የተለመደ ሆኗል:: በተለይ የሥርዓቱ ባለቤቶችና ደጋፊዎች ምስኪኑን ሕብረትሰብ ሳይቀር በማስገደድ ቀኗን “ልዩ ቀን” “የድል ቀን” “የስኬት ቀን” በማለት ሰይመው በአስረሽ ምችው ሲከበር ማየት ድፍን 25 ዓመታትን አስቆጠረ።

eprdf-tplf

ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ደርግ ኢሰፓ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮታል ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሦስት ብለው እንዳበሰሩን በእርግጥ ለጥቂቶች ግንቦት 20 የድል ቀን ነው:: ምክንያቱም ሀገሪቱን በአንባገነናዊ አገዛዝ ለማስተዳደርና የስልጣን ጥማታቸውን ለማርካት መሰረት የጣሉባት እና የአስራ ሰባት ዓመት የልፋት ዋጋቸውን ያገኙባት ልዩ ቀን ናትና:: በዚች ቀን ህብረተሰቡን በምስጢራዊ የአገዛዝ ስልት ለማስተዳደርና ስልጣናቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ የነበራቸው ሕልም እውን የሆነባት ቀን ናትና በልዩ አከባበር ቢያከብሯት ሲያንሳት እንጂ አይበዛባትም::
የተወሰኑ የስራዓቱ አቀንቃኞችም ስለቀኗ መልካምነትና ከዚያች ቀን በኃላ አገራችን ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና የገስገሰች፣ የዜጎች አኩልነት የተረጋገጠባት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ ሰባዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የታየባት፣ ህብረተሰቡን በእኩል የሚያስተዳድር መንግስትና ሕግ መንግስት የተመሰረተባት አገር እንድትሆን ግንቦት 20 ታሪካዊ የድል አሻራ እንደጣለች በኩራት አፋቸውን መልተው ይናገራሉ:: ይባስ ብለው ከውጭ ወራሪ ወይም ቅኝ ግዛት ኢትዮጵያን ነፃ ያወጧት ይመስል ግንቦት 20ን የነፃነት/ሀገራዊ ቀን ለማድርግ የሚሞክሩ ብልጣብልጥ የስራዓቱ ደንገጡሮችም አሉ::
በእርግጥ የደርግ አንባገነን መንግስት የአጼ ኃይለ ስላሴ መንግስትን ገርስሦ በምትኩ ወታደራዊ ጁንታ በመመስረት ስሙን በመቀያየር አገዛዙ ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያን በብዙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተለይ ሀገሪቱን መለወጥ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡትን 60 ሚኒስተሮች በመረሸን፣ ነጭና ቀይ ሽብር በማለት ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማስጨፍጨፉ የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግን ስርዓት አንቅሮ ተፍቶት ነበር። የለውጥ ያለሽ ብሎ በመጮህ ከደርግ አረመኔያዊ የጭካኔ አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው የሚችል መለኮታዊ ኃይል እስኪፈልግ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ለውጥ ፈላጊ ሆነ።
ህወሓት የህዝቡን ብሶትና እሮሮ ተጠቅሞ 17 ዓመት ጫካ ውስጥ ያረገዘውን መርዝ ለመርጨት ግንቦት 20 ደርግን ገርስሦ በትረ ስልጣኑን ጨበጠ። እዚህ ላይ ወያኔ የደርግን ስርዓት ሳያይና በትንሹም ቢሆን ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ሳያደርግ ለትግል ወደ ጫካ መግባቱ ሀገራዊ ለውጥ አሳስቦት ሳይሆን የብሄር ፖለቲካ ጥማት እንደሆነ በትክክል መገንዘብ ይቻላል፤እያየነውም ነው። የብሄር ፖለቲካ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችን ለምታስተናግድ ሀገር ቀርቶ ለየትኛውም የአለም ሀገራት የማይበጅ መሆኑ የታወቀ ነው። ኢትዮጵያም የከፋፍለህ ግዛውና የጎሳ ፖለቲካ እንደማይጠቅማት ከዘመነ መሣፍንት ትምህርት ቀስማ ነበር። ዳሩ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግን ሥርዓት ጥላቻና ሽሽት ዘረኛው ወያኔን ግንቦት 20 በሩን ከፍቶ እጁን ዘርግቶ ተቀበለ።
ወያኔዎች የደርግን ሥርዓት ገርስሰው መንግስቱ ኃይለ ማርያምን ወደ ዝምባብዌ ካስኮበለሉ በኋላ ሥልጣናቸውን ለማጽናት የይስሙላ ህገ መንግሥት አርቅቀው አጸደቁ። ለተወሰኑ ዓመታትም የነጻነት በርን ለመከፈትና ስላምና መረጋጋትን ለማስፈን የመጡ እስኪመስል ድረስ ሰላምን ሰበኩ። ከደርግ ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በሙሉ እስር ቤት ወረወሯቸው። ከገጠር እስከ ከተማ ህብረተሰቡ ለራሱ መጠበቂያ ብሎ የገዛዉን ትጥቅ ሳይቀር በሙሉ አስፈቱ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግንቦት 20 በየዓመቱ “የድል ቀን” እያለ እንዲዘምር ተደረገ።
በእውኑ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው? ይህ ጥያቄ በተለያየ መልኩ በሁላችንም አይዕምሮ ውስጥ እንደሚመላለስ እርግጠኛ ነኝ። መልሳችን ግን በራሳችን ምዕናባዊ እይታ ስለምንመለከተው የተለያየ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን ከሁለት አማራጮች ሊዘል አይችልም። ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔዎች እንደሚሉት “የድል ቀን” ወይም ብዙዎች እንደሚስማሙበት “የውድቀት ቀን” መሆን አለበት። ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ግንቦት 20ን “የድል ቀን” ማለታቸው በእርግጥም ትክክል ናቸው። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የአንባገነን ስልጣናቸውን ያፀኑበት እና በሦስቱም ዘርፍ ማለትም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩበት ቀን ነውና።
እውነታው ሲገለጥ ግን ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የውድቀት እና የውርደት ቀን እንጂ በምንም መመዘኛ የድል ቀን ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ለአንድ ሀገር የድል ቀን ሲባል ዜጎቿ እኩል ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል በጎ አጋጣሚ ወይም የኩራት ምንጪ ሲፈጠር ብቻ ነው። ግንቦት 20 ግን ከዚህ በተቃራኒው መሆኑን ግልጽ ሊያደርግ የሚችል ብዙ ማሳያዎች ከመኖሩም ባሻገር በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ችግር ዘርዝሮ መናገር ይቻላል።
“የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”
የኢትዮጵያ ህዝብ ከግንቦት 20 የተቀበላቸውን ገጸ እርግማኖች ለማሳያ ያክል እንደሚከተለው እናያለን፤

የብሄር ፖለቲካ የተፀነሰበት
የህወሓት ማፍያ ቡድን ገና ከጅምሩ ሃገራዊ ፍቅር ሰንቆ እንዳልመጣ ከስሙ መረዳት ይቻላል። የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ብሎ መሰየሙ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ እንዳልቆመ ለመረዳት ነብይነት አያሻውም ነበር። የከፋፍለህ ግዛው መርህን በማንፌስቶው ይፋ አድርጎ ይንቀሳቀስ እንደነበር ሰነዶች ህያው ማስረጃ ናቸው። ለስልጣን ማራዘሚያ በዋናነት የተጠቀመበት ዋናና ትልቁ አጀንዳ የብሄር ፖለቲካን ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ካልሆነ በስተቀር ከስልጣን ሊወርድ የሚችልበት ምንም አይነት አጋጣሚ እንደሌለ በሚገባ ያውቃልና። የብሄር ፖለቲካ እያራመደ እርስበርሳችን እንዳንተማመን በብሄር ለያይቶናል። ይሄ የናንተ መሬት ነው፣ ይህ ደግሞ የነሱ ነው ወዘተ እያለ በቡድን ከፋፍሎናል። በብሄሮች መካከል መግባባት እንዳይኖር እነእገሌ እንዲህ አደረጓቹህ፣ ታሪካችሁ እንዲህ ነው በማለት መጀመርያ መምጣት ያለበት ብሄር ነው ወዘተ እያለ የብሄር ጥላቻ እንዲሰፍን ሀውልት ሰርቶልናል። አንድ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከማለት ይልቅ በውሸት የብሄር እኩልነት ስም ኦሮሞ፣አማራ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እያለ በየቦታው እራሱን እያዋረደ እርስ በእርሳችን በጥላቻ እንድንናቆር ማድረጉ የወያኔ የብሄር ፖለቲካ ውጤት ነው። ስለዚህም ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የድል ቀን ሳይሆን የብሄር ፖለቲካ የተፀነሰበት የውርደት ቀን ነው። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”
ትውልድ ገዳይ ሥርዓተ ትምህርት የተቀረጸበት
ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሀገር ተተኪ ዜጋ ፈጣሪ ተቋም እንደመሆናቸው መጠን የሃገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ፣ ታሪክንና ባህልን ከማሳወቅ ባለፈም በማንነት ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለው ዜጋ ለማፍራት የሚቀረጸው ሥራተ ትምህርት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ነገር ግን ወያኔ የቀረጸው ሥርዓተ ትምህርት ግን ትውልድን ገዳይና የተማሪዎችን አይዕምሮ ለምርምርና ጥናት የማይጋብዝ ዘላቂና አስተማማኝ ያልሆነ ጥራት የጎደለው ሥርዓተ ትምህርት ነው። ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎችን በጥሩ ሥነ ምግባርና ባህልን ከማሳዎቅ አንጻር አስተምሯቸው ዝቅተኛና ከዚህ ግባ የማይባል መሆኑ ለትውልዱ መጥፋት ሌላው የወያኔ የስርዓቱ ውጤት ነው። ትምህርት ቤቶችን ስንመለከት ከተቀረጸላቸው ሥርዓተ ት/ት ጀምሮ ትውልድን ለመቅረጽ ቀርቶ በዜግነት ደረጃም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚናገር ትውልድ እንዲጠፋ በማድረግ ረገድ ግንቦት 20 የራሷን ጥቁር ጠባሳ ጥላለች። አንዳንድ የዘመነ ወያኔ ተማሪዎች የሀገረን ታሪክ በሚገባ ካለማዎቅ የተነሳ ቅኝ ግዛት በተገዛን ኑሮ ሲሉ መስማት የሥርዓተ ትምህርት ውድቀቱን ማሳያ አንዱ መንገድ ነው።
የሃገር ዳር ድንበር የተደፈረበት
አንድ ሀገር የድል ቀን የምታከብር ከሆነ ለሀገርና ለህዝብ የሚቆረቆር መንግሥት አላት ማለት ነው። መንግሥት ካለ ደግሞ የሃገር ሉዓላዊነት ተጠብቆ፣ ታሪኳ ሳይበረዝና ሳይፋለስ ለትውልድ መተላለፍ ይችላል ማለት ነው። ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ግን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ዳር ድንበሯ የተደፈረባት፣ ወደቧን ያጣችበትና ታሪኳ የተበረዘበት ዘመን ነው። ድሮ አባቶቻችን ቅኝ አንገዛም በማለት ታሪካችንና ባህላችን ሊበረዝ ከቶ አይችልም ብለው አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ ውድ ህይወታቸውን ሰውተው ዳር ድንበሯን ከነሙሉ ክብሯ ያቆዩልንን ሀገር ወያኔ ለአረብና ህንድ ባለሃብቶች ማቀራመቱ ሳያንሰው ሱዳን የድርሻሽን ውሰጅ ብለው በመማጸን ላይ እንደሆኑ ስንሰማ በእውነትም ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የውርደትና የውድቀት ቀን ነው። ዜጎቿ በሄዱበት ሞትና እንግልቱ ሳያንሳቸው በእራሳቸው ሀገር በሌላ ዜጋ እንደ እንስሳ ደማቸው ሲፈስና ህጻናት በገፍ ተግዘው ሲሄዱ ከማየት በላይ ምን የተለየ ውርደትና ውድቀት ይኖራል። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”
ህዝቦቿ ለሞት፣ለስርና በስደት ለውርደት የተዳረጉበት
በወያኔ አገዛዝ ከ1983 እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከግንቦት ወር ጀምረን በግፍ ውድ ህይወታቸውን በስውርና በአደባባይ የተቀሰፉ፣ ለስር፣ ለእንግልትና ለስደት የተዳረጉ ዜጎችን የሰማይ አምላክ ይቁጠራቸው እንጂ በአኃዝ ማስቀመጥ እጅጉን ይዘገንናል። ተፈጥሯዊና ሰባዊ መብቶች በይፋ ተገርስሰዋል። የስርዓቱ አባል፣ ደጋፊና አገልጋይ ካልሆነ በስተቀር በሀገሩ ምድር ቀና ብሎ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመደራጀት እና የመስራት መብቶች ፈጽመው መገደባቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። ወያኔዎች ግንቦት 20ን የድል ቀን ብለው ማክበር ከጀመሩ ጀምሮ በሀገሪቱ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈሷል። ህዝቦቿ በሄዱበት ሁሉ የውርደት ካባ እየተከናነቡ ተቆርቋሪ ያጣ ዜጋ በመሆኑ ዋይታና ልቅሶው ከመቸውም በላይ ጨምሯል። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ አገራችን የተለያየ መልክና መገለጫ ያላቸው በርካታ መንግሥታትን ያስተናገደች አገር ብትሆንም ለዘመናት ታሪኳን፣ ባህሏን፣ እምነቷን፣ አንድነቷን፣ ድል አድራጊነትን እና ዳር ድንበሯን ጠብቃ አስጠብቃ የኖረች እና መተሳሰብን፣ መከባበርን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ዘርንና ጎሳን መሰረት ሳታደርግ ለዘመናት የቆየች የጀግኖች አገር ነበረች። ነገር ግን ግንቦት 20 የለገሰን የአሳርና የግፍ ፍሬዎች በቀላሉ የማይሽሩ እኩይ ተግባር ናቸውና ታሪካዊ አገራችንን አደጋ ላይ ጥሏታል። ስለሆም ጊዜ ሳንሰጥ “የድል ቀን” የሚለውን ተረት ተረት ወደ ጎን በመተው በአንድነትና በህብረት ዛሬውኑ የውርደትን ቀን ወደ የድልና የክብር ቀን ሊቀየር ይገባል። ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የድል ቀን ሳይሆን የሞት፣የውድቀትና የውርደት ቀን ተብሎ ይስተካከል!ምነው ሽዋ! ድንቄም የድል ቀን…………

One Response to ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው?

“የትግራይን የብሔር እኩልነት እስከመገንጠል ድረስ፤ የራሱንም ሪፐብሊክ ለመመሥረት ይታገላል የሚል በፕሮግራሙ ነበር” – ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን

ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን፤ መሥራችና የቀድሞው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ፖሊት ቢሮ አባል ስለ ድርጅቱ አመሰራረት፣ የትግል እንቅስቃሴ ታሪክና ሚናዎች ይናገራሉ

https://youtu.be/4Zaa7Za2jl8

hqdefault

የራስ መንግስት መመስረትና ነጻነት ምንና ምን ናቸው? – (ሊያነቡት የሚገባ)

ዛሬ መጻፍ የፈለግሁት በእንግሊዝኛ Independence እና Freedom ስለሚባሉ ሁለት የፖለቲካ ትግል መሰረታዊ ፍሬ ሀሳቦች ነው። ወደ አማርኛ ስንመልሳቸው Independence ማለት «ተለይቶ የራስ መንግስት መመስረት» ወይንም «የራስ አገር መፍጠር» ማለት ሲሆን Freedom ማለት ደግሞ በሚኖሩበት አገር ውስጥ ነጻነት ማግኘት ወይንም ነጻ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ ለIndependence የሚደረግ የፖለቲካ ትግል ማለት ተለይቶ የራስ መንግስት ለመመስረት ወይንም የራስ አገር ለመፍጠር የሚደረግ ትግል ማለት ሲሆን ለFreedom የሚደረግ ትልግ ማለት ደግሞ በሚኖሩበት አገር ውስጥ ለነጻነት ወይንም ነጻ ለመሆን የሚደረግ ትግል ማለት ነው

Tensaye

በአገራችን ላለፉት ሃምሳ አመታት በብሄረሰብ ማንነት የተሰባሰቡ የዘር ድርጅቶች ያደረጉት የLibration ፍልሚያ [ዛሬም እያደረጉት ያለው የፖለቲካ ቁማር ጭምር] ለነጻነት የተደረገ ንቅናቄ ሳይሆን ተለይቶ የራስን መንግስት ለመመስረት ወይንም የራስን አገር ለመፍጠር ያካሄዱት ትግል ነው። በመሰረቱ ለነጻነት መታገል በብሔረሰብ መደራጀትን አይጠይቅም። በብሄረሰብ ተደራጅቶ መታገል ሊያስገኘው የሚችለው ብቸኛ ግብ የራስ መንግስት መመስረት ወይንም የራስ አገር መፍጠር ብቻ ነው። በብሄረሰብ ተደራጅቶ የራስ መንግስት ለመመስረት መታገል ነጻነትን ሊያጎናጽፍ አይችልም። የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል የኦሮሞ ገበሬ የመሬት ባለቤት ሊሆን አይችልም። የኦሮሞ ገበሬ የመሬት ባለቤት ሊሆን የሚችለው ለነጻነት በሚደረግ ትግል ብቻ ነው። የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል የመሬት ባለቤት መሆን የሚቻል ቢሆን ኖሮ ዛሬ የትግራይና የኤርትራ ገበሬ የመሬት ባለቤትና ባለ መብት በሆነ ነበር።
የአገራችን የብሔረሰብ ድርጅቶች ትልቁ ስኬት እናቱ ገበያ የሄደችበትን የብሔረሰባቸው አባል እናትህ ሞታለች ብለው ማስለቀስ መቻላቸውና «ጭቆና እየደረሰበኝ ያለው ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች [ማለትም ጨቋኞቹ] የብሔረሰቤ አባላት ስላልሆኑ ነው» ብሎ የሚያምን ትውልድ መፍጠራቸው ብቻ ነው። ይህን ስብከታቸውን ለማንበርም «ተጨቆነ» በሚሉት ብሔረሰብና «ጨቋኝ» ነበር ባሉት ብሔረሰብ መካከል ምንም አይነ ግንኙነት ወይንም ዝምድና እንደሌለ የፖለቲካ ታሪክ ፈጥረዋል። «ተጨቆነ» በሚሉት ብሔረሰብ መካከልና «በጨቋኙ» ብሔረሰብ መካከል የነበሩትን ትስስሮችና አንድ የሚያደርጉትን ክሮች ሁሉ በጥሰዋል። በአንድነቱ ጊዜ «የኔ ብሔረሰብ አባላት ናቸው» የሚሏቸው ሰዎች የነበራቸውን አስተዋጽኦ አሳንሰዋል፤ አኮስሰዋል። ሰዎቹንም ጭቃ ቀብተዋቸዋል። የነበራቸውን ሚናም እንዳልነበረ አድርገውታል። ራስ አበበ አረጋይ፣ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ፣ገረሱ ዱኪ፣ ይልማ ደሬሳ፣ ራስ መንገሻ ስዩም፣ ራስ ስዩም መንገሻ፣ ሀረጎት አባይ፣ ሎሬንሶ ታዕዛዝ ወዘተ የራስ አገር ለመፍጠር በታገሉና አሁንም እየታገሉ ባሉ የዘር ፖለቲከኞች ፕሮፓጋንዳ ዶግ አመድ ሆነዋል።
ዛሬም ድረስ የአገራችን የዘር ድርጅቶች «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚሉት የዘር ቅስቀሳ የራሳቸውን አገር ለመመስረት ሲሉ የብሔረሰቦቻቸው አባላት የሆኑ ወገኖቻቸው ትግል እንዲያደርጉ የሚያነሳሱበት ዋነኛ ዘዴያቸው ነው። ተከታዩም ስላልነቃ ጥሪያቸውን ሰምቶ አብሯቸው ይጎተታል። እነዚህ የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች «ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች የሚጨቁኑኝ የብሔረሰቦቻችን አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚለውን ያረጀ ስብከታቸውን የበለጠ ለማሳመን ደግሞ በአንድነቱ ጊዜ የነበሩ የብሔረሰባቸው አባላት የሆኑ ልሂቃን ለአገራቸው ሲሉ ያደረጉትንም አዲስ ትርጓሜ በመስጠት ስራዎቻቸውንና ሰዎቹን አሳንሰዋቸዋል።
ባለ ቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን የዚህ የማሳነስ ዘመቻ ሰለባ ነው። ባለ ቅኔው ጸጋዬ «በማናቸውም የአለም ህዝብ ታሪክ ውስጥ የሚገኝ የየአገሩ ወንዝ ጉዞ የየአገሩ ሰፊ ህዝብ የየትውልድ ጉዞ ተምሳሌት ሆኖ ይቀረጻል» በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት እንደ አባይ፣ አዋሽ፣ ዋቢ ሸበሌ፣_ ተከዘ፣ መረብና ሌሎቹንም ወንዞች ከኢትዮጵያ አፈጣጠር ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክና ትውልዶች ጉዞ በተምሳሌትነት ለማሳየት በኢትዮጵያውያንና በባዕድ የስነጽሁፍ ሰዎች ሳይቀር እንደተቀረጹ ያስረዳና ከባዕድ አገራትም ኤፍራጦስና ጤግሮስ በሜሶፖታሚያ፤ ቴምስ በእንግሊዝ፤ ሚሲሲፒ በአሜሪካና ዶን በሩሲያ የየዘመኑ ታላላቅ ጸሀፍት ዘንድ የየአገራቱን ህዝብ ታሪክና የየትውልድ ጉዞ ለማሳየት በተምሳሌትነት እንደቀረቡ አውስቶ እሱም በብዕሩ የኢትዮጵያን ታሪክና የየትውልድ ጉዞ በአዋሽ ተምሳሌትነት የጻፈውን አስደማሚ ግጥም ኦነጋውያን «ስለኦሮሞ ህዝብ እጣ ፈንታና መጻኢ እድል» የጻፈው አድርገው በማሳነስ አዲስ ትርጓሜ ሰጥተውበታል።
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች በአንድነቱ ጊዜ የነበሩ አንዳንዶቹን የብሔረሰባቸው አባላትና አስተዋጿቸውን ደግሞ እንዳላዩ አልፈዋቸዋል። የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ የዘፈናቸውን በርካታ የኦሮምኛ ዘፈኖች፤ዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግስት ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው እነ ጥላሁን ገሰሰና ብዙነሽ በቀለ የዘፈኑትን ያንን ሁሉ የኦሮምኛ ዘፈን ኦነጋውያን እንዳልነበረ ቆጥረውታል። ሻዕብያም በበኩሉ ከጥላሁን ገሰሰና ብዙነሽ በቀለ እኩል የትግርኛ ዘፈናቸው ሸክላና ካሴት ይሸጥላቸው የነበሩትን እነ በረኸት መንግስተዓብንና ትበርህ ተስፋሁነኝን እንዳልነበሩ፤ በኢትዮጵያ ማዕቀፍም ያ ሁሉ ነገር እንዳነበረ በመቀስቀስ በውሸት አገር ፈጥሯል።
የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች ከዚህ በከፋም በአንድነቱ ጊዜ የነበሩና እስከመጨረሻው ድረስ በኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ጸንተው የቆሙትን የብሔረሰባቸው አባላት ስለኢትዮጵያ ያደረጉትን ሁሉ የከሀዲዎች ድርጊት አድርገው አጣጥለውታል። ራስ ጎበና ዳጨ፣ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎና አስፍሀ ወልደ ሚካዔል የዚህ የዘረኞች የከሀዲነት ክስ ሰለባዎች ናቸው። በቤተ ኦነግ «ጎበና» የሚለው ስም ሲጠራ የክህደት፣ የጸረ ኦሮሞነትና የጥፋት ተላላኪነት መገለጫ ሆኗል። ይህ ሁሉ ትርክት «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚለውን በብሔረሰቦቻቸው አባላት ላይ አስርጸው የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚያደርጉትን ትግል ለማቃናት ነው።
ዛሬ ዛሬ ደግሞ «ብዝሀነትን» ወያኔና ኦነግ ከደደቢት በረሀና ከሞቃድሾ ቤተ መንግስት ስበው ያመጡት አንዳች አዲስ ጽንሰ ሀሳብ ሆኖ እየተሰበከ ይገኛል። ላስተዋለው ግን በተለይ በኢትዮጵያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ውስጥ ብዝሀነት አዲስ አይደለም፤ በቤተ መንግስት ደግሞ በጉልህ ይታይ ነበር። አዎ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በቤተ መንግስታቸው ከነ ራስ አበበ አረጋይ፤ከነ ራስ ስዩም መንገሻ፤ ከነ ዋቆ ጉቱ፣ ከነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ከነ ራስ መስፍን ስለሺ፣ ከነ ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ከነ ተድላ ባይሩ፣ ከነ ሐረጎት አባይ፣ወዘተ ጋር ሲገናኙ በአማርኛ ያወሩ ነበር። እንኳን ያንድ አገር ሰዎች የተለያዩ አለም መሪዎች እንኳ ዋይት ሀውስ ሲሄዱ ከአሜሪካን ፕሬዝደንቶች ጋር የሚነጋገሩት በእንግሊዝኛ ነው። ሁለት ሰዎች ይግባቡ ዘንድ በአንድ ቋንቋ ማውራታቸው ግድ ነው። «የብዝሀነት አባት» ተደርጎ በካድሬዎቹ የሚሰበክለት መለስ ዜናዊም ከነ አባዱላ ገመዳ፣ ከነ አባተ ኪሾ፣ ከነ ኩማ ደመቅሳ፣ ከነ አብዱል መድጅ ሑሴን፣ ከነ ግርማ ብሩ፣ ከነ ጁኔይድ ሳዶ፣ከነ አልማዝ መኩ፣ ከነ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግስት ሲገኛኝ የሚያወራው በአማርኛ ነበር።
ሌንጮ ለታም በመስ ዜናዊ ቦታ ቢቀመጥ ኖሮ ከነ ስዬ አብርሀ፣ ከነ ካሱ ኢላላ፣ ከነ አብዱል መጂድ ሑሴን፣ ከነ መብርሀቱ ገብረሕይወት፣ከነ ተኽሉ ተኽላይ ጋር ሲገናኝ የሚያወራው በአማርኛ ነበር። ልዩነቱ ወንበሩ ላይ የሚቀመጡት ሰዎች እንጂ የብዝሀነት አይደለም። ሆኖም ግን ታሪክ የሚጻፈው በየዘመኑ አሸናፊዎች ነውና የኢትዮጵያ ብዝሃነት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ያልነበረ፤ በመለስ ዜናዊ ቤተ መንግስት ግን ከደደቢት ተስቦ እንዳዲስ የተጀመረ ተደርጎ ተጻፈ። ዛሬ በአፍ የሚሰበከው «ብዝሀነት» የነጻነት ፍቺ ቢሆን ኖሮ «ብዝሃነት ተከበረ» በተባለበት በመለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የኦሮምያ ምስለኔ ከነበረው ከኦሮሞው አባዱላ ገመዳ በላይ በኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ የነበሩት ኦሮሞው ራስ መስፍን ስለሺ የተሻለ ነጻነት አይኖራቸውም ነበር።
የራሳቸውን አገር ለመመስረት የታገሉት ኤርትራውያን ለነጻነት ስላልታገሉ ለሰለሳ አመታት ያህል ታግለው የራሳቸውን አገር መመስረት ከቻሉ በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸውን ነጻነት ጭምር ለኢሳያስ አስረክበው ከሰላሳ አመት የበረሀ ትግል በኋላ ያገኙት ነገር ቢኖር ነጻነት ሳይሆን በባርነት የሚኮሩበት የራስ ቴምብርና ባንዲራ ብቻ ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ኤርትራ ነጻ ፓርላማ ነበራት። ኤርትራ ወደናት አገሯ ከተቀላቀለች በኋላም ኤርትራውያን እንደራሴዎች በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ እንዴት ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ የአስመራ ከንቲባ የነበሩት የደጃዝማች ሐረጎት አባይ ልጅ ኤርትራዊው ስዩም ሀረጎት «The Bureaucratic Empire Serving Emperor Haile Selassie» በሚል ርዕስ በጻፉት ድንቅ መጽሀፋቸው በሰፊው አቅርበውታል። ኤርትራውያን ጫካ የገቡት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸው ነጻነት አነሰን በሚል ነበር።
የራሳቸውን አገር ለመመስረት ባደረጉት ትግል ግን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸውን መብትም ከናካቴው አጥተዋል። «የነበራቸው ነጻነት አነሰን፤ ይጨመርልን» ብሎ ዱር ቤቴ ያለው የኤርትራ ህዝብ ለሰላሳ ዓመታት ያህል ታግሎ የራሱን መንግስት ሲመሰርት የነበረውንም ነጻነት አጣ። የኤርትራ ህዝብ ለሰላሳ ዓመታት ያህል የራስ አገር ለመመስረት ባደረገው ተጋድሎ የነበረውን ነጻነት ሽጦ ያገኘው ጥቅም የኢሳያስ ቴምብርና ባንዲራ ብቻ ነው። ለኤርትራውያን ይህ የኢሳያስ ቴምብርና ባንዲራ ከመለስ ዜናዊ ቴምብርና ባንዲራ ጋር በምን እንደሚለይ አላውቅም። እንዴውም በዘር ሀረግ ከኢሳያስ በላይ መለስ ዜናዊ ኤርትራዊ ነው።
የሆነው ሆኖ ነጻነት የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል አይገኝም። እንዴውም በተግባር እንደታየው ከሆነ የራስ አገር ለመመስረት የታገሉ ህዝቦች የነበራቸውን አንጻራዊ ነጻነት አጥተዋል። ኤርትራውያን የዚህ ትራጀዲ ዋና አብነቶች ናቸው። ኦነግ በሚያደርገው የራስ አገር የመመስረት ትግልም ቢሆን የሚገኘው የነጻነት «ትሩፋት» ኤርትራውያን ካጋጠማቸው የከፋ፤ ምናልባትም ሶማሊያ ውስጥ እንደተከሰተው አይነት የርስ በርስት መተላለቅ ሊሆን እንደማይችል ዋስትና የለም። ኦነግ የሚመሰርታት ኦሮምያ የምትባለዋ «አገር» ከሶማሊያ የከፋ ሁኔታ ሊያጋጥማት የማትችልበት ዋስትና እስካሁን ያቀረበ ኦነጋዊ አላጋጠመኝም። ዛሬ ኦሮምያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለች ብቻ የማይታይ የሚመስለው የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች ኦነግ የኦሮሞ አገር ሲመሰርት ያቆጠቁጡና እንደሶማሊያ ጎሳዎች የፖለቲካ መሳሪያ ሆነው እንደማያገለግሉ ዋስትና የለም።
አንዳንዶቹ ኦነጋውያን ያለ ኦሮምያ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ይላሉ። ያልገባቸው ነገር ቢኖር ያለ ኢትዮጵያ ኦሮምያም እንደማትኖር ነው። ኢትዮጵያ በመኖሯ ኦሮምያ ውስጥ ያሉት የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች የግጭትና የርስ በርስ መከሳከስ መንስዔዎች አልሆኑም። ኢትዮጵያ ባትኖር ኦሮምያ ውስጥ ያሉት የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች ገንትረው እንደ ሶማሊያ የመከሳከሻ፣ የመፈረካከሻና የሞት ማንገሻ መሳሪያዎች አለመሆናቸው ዋስትና የለም። ስለዚህ የኦሮምያ መኖር ለኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆነውን ያህል የኢትዮጵያ መኖርም ኦሮምያ እንደሶማሊያ እንዳትሆን ትልቅ ዋስትና ነው። ይህን የሚጠራጠር ካለ ያስብበት።

የባሮ ቱምሳ ሞት ለዚህ አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ክርስቲያኑ ባሮ ቱምሳ በጭንቅላቱ የሳለውን የኦሮሞ አገር ይዞ ለመታገል ሀረር ሲመሽግ የእስላሚክ ኦሮምያ ታጋዮች «ክርስቲያን ነጻ አያወጣንም» በሚል አርደውታል። ኢትዮጵያ ባትኖር ኖሮ በበባሮ ላይ የደረሰው በሌንጮ ለታና በገላሳ ዲልቦ ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለም ነበር። በሌንጮ ለታና በገላሳ ዲልቦ ላይ የሚደርሰው በኦሮሞ ክርስቲያኖችና በዋቄ ፈታ ስርዓት አማኞች ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለም።
ዛሬ ላይ የኦነግን ሀሳብ የሚያቀነቅኑ የኦሮሞ ኤሊቶች በተለይ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትን በሚያራምዱ ምሁራን ላይ የሚያካሂዱትን የጥላቻ ፖለቲካና መረን የለቀቀ ቀፋፊ ንግግር ለተመለከተ ኦነግ በለስ ቢቀናው በሚፈጥረው አገር የሚገዛቸው ህዝቦች እድል ፈንታ ከኤርትራውያን ይዞታ የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። የሚገርመው ግን አብዛኛው የነዚህ ዘረኛ የኦነግ ኤሊቶች ተካታይ የሆኑ ወጣት ኦሮሞዎች ዘረኞቹ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኞችን ለማሸማቀቅ የጥላቻ መርዝ በሚተፋው ምላሳቸው የሚረጩትን መረን የለቀቀ ስድነት እያዩ «አበጃችሁ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ናችሁ» ማለታቸው ነው። አላወቁትም እንጂ ይህ መርዘኛ ምላስ ነገ በለስ ቀንቶት አዲስ አገር ሲመሰርት ቀድሞ የሚበላው እነሱን ነው። ኢሳያስ አፈወርቂ ሻዕብያን ለመንግስትነት ከማብቃቱ በፊትም ጫካ እያሉ «ማንካ» በሚባለው የሻዕብያ «የህንፍሽፍሽ» እንቅስቃሴ በሃሳብ የተለዩትን የትግል አጋሮቹ የሆኑትንና በቀማዳዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የፊት ተዋናይ የነበሩትን እነ ዮሀንስ ስብዓቱን በሀሳብ ስለተለዩ ብቻ ገድሏቸዋል። ዮሀንስ ስብዓቱን ግን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ታስሮ በይቅርታ ምህረት ተሰጥቶት ከእስር የተነቀቀ ነበር።
እንግዲህ ይታያችሁ ዮሀንስ ከኢሳያስ በሀሳብ ስለተለየ ለነጻነት ታገልሁ በሚለው ኢሳያስ ተረሸነ። ዮሀንስ ስብዓቱ ግን ዲሞክራሲ የለበትም በተባለበትና ዘመንና «ሪያክሽነሪ» በተባሉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ምህረት የተሰጠው ነበር። ኢሳያስ አፈወርቂ በተማረኩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ላይም ይለማመድባቸው የነበረውን የግፍ አይነት በወቅቱ ባይናቸው ያዩ የነበሩ የትግል ጓዶቹ የወዲ አፈወርቂን ድርጊት ከጀግንነት ቆጥረውት ነበር። የኢሳያስ ጓዶች ኢሳያስ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የፈጸመውን ግፍ በኛ ላይ ሊፈጽመው ይችላል ብለው አላሰቡም ነበር። በአንድ የተወሰነ የታሪክ ወቅት የሚከሰት የጭካኔ ድርጊት ግን ሁሌም Precedence አለው። ቶላና ጫላ አብረው ሳሉ ጫላ በበየነ ላይ የሚፈጽመውን ዘግናኝ ድርጊት ጫላ በቶላ ላይ ላለመፈጸሙ ዋስትና የለም። እንዴውም ጫላ በበየነ ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት በቶላ ላይ ሊፈጸመው እንደሚችል precedence አለ። ኢሳያስ አፈወርቂም በነዮሀንስና በተማረኩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ላይ ያደረገውን ግፍ የራሱን አገር ሲፈጥር ከሁሉ አስቀድሞ ያስቀጠለው አብረውት በነበሩ፤ ግፍ ሲፈጽም እያዩ «አበጀህ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ነህ» ባሉት የእድሜና የትግል አጋሮቹ ላይ ነው።
በኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ አራማጆች ላይ መርዝ ከመርጨት የማይቦዝነው የኦነግ የምሁር ሊጎች ምላስም ነገ አገር ሲመሰርት ቀድሞ የሚበላው ዛሬ አጅበው «አበጃችሁ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ናችሁ» የሚሉትን ጭፍን ደጋፊዎች ነው። እነዚህ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኞች ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ አብረው እያሉ ማምጣት ያልቻሉትን ነጻነት የራሳቸውን መንግስት መስርተው ሊያመጡት አይችሉም። «የምጨቆነው ጨቋኞቹ ወገኖቻችን ስላልሆኑ ነው» በሚል ያስተሳሰብ ዝንፈት ያሰለፉት ኃይል ይህንን እውነት ያስተዋለው አይመስልም። የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ ጨቋኝ እንጂ ጭቆና እንደማይቀየር የተገነዘቡት አይመስልም። ጨቋኑ መሬት ነጣቂ ከሆነ የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ መሬት ነጣቂው ቢቀየር እንጂ መሬት ነጠቃው እንደማይቀር አላጤኑትም።
እንዴውም በሚመሰርቱት የራሳቸው አገር በንጉሱ ዘመን ከነበረውና «የማንም ንብረት ለግለሰብ ተብሎ አይነካም» ከሚለው ህገ መንግስታዊ መብት አኳያ ካየነው ደግሞ ቁልቁለቱ በጣም ቁልቁል ነው። የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ ገራፊ ቢቀይሩ እንጂ ግርፊያ አይቀርም። በኢትዮጵያዊ ብሔርተኞች ላይ ዛሬ መርዝ የሚተፋው የኦነጋውያን ዶክተሮች ምላስ ነገ ላይ አገር ስለመሰረቱ precedenሱ ጥሩ ሊሆን አይችልም። ኤርትራ የሆነው ኦነግ በሚፈጥረው አገር አይሆንም ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው። ኤርትራ ላይ የምናየውን ፊልም ኦነግ በሚፈጥረው አገር የማናይበት ምንም ምክንያት የለም። ለምን ቢባል የራስ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ትግል እንደማትጨቆን፤ እንደማትገደል፤ ንብረትህን እንደማታጣ፤ ነጻነትህን እንደማትገፈፍ ዋስትና ሊሰጥ አይችልምና ነው። በኤርትራና በደቡብ ሱዳን እንደታየው የራስ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ትግል ላለመጨቆን፤ ላለመገደል፤ ንብረትን ላለማጣት፤ ነጻነትህን ላለመገፈፍ ዋስትና አይሆንም።

ከዚህ በተጨማሪ የራስ መንግስት ለመመስረት የታገሉት ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን ለመውቀውስ የሚያዳግት ጨካኝ አገዛዝ «ተጎናጽፈዋል»። ለመውቀስ የሚያዳግት ያልሁት ስለ አንድ ነገር ነው። ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን በርሀ ሲወርዱ «ጭቆና እየደረሰብን ያለው ስልጣን ላይ ያለው የኔ ዘር ስላልሆነ ነው፤ የኔ መንግስት ስላልሆነ ነው» በሚል መነሻ ስለሆነ ዛሬ በትግላቸው የኔ የሚሉት መንግስት አቁመው ሲጨቁናቸው «የኔ መንግስት ጨቁኖኛል» ብለው ለመውቀስ፤ የነበራቸው ነጻነት እንዳጡ ለመናገርና ለመታገል ያሳፈራቸው ይመስላል። የራስ መንግስት ለመመስረት ያታገሏቸው ፋኖዎች ነጻነት ሊሰጧቸው እንደማይችሉ በሚጭኗቸው የጭቆና ቀንበር ውስጥ ገብተው ሲገነዘቡት ፋኖዎቹ እንደሸወዷቸው ቢገባቸውም የውሽማ ለቅሶ እያለቀሱ እንዳይነወሩ የከፋ የራስ የግፍ አገዛዝ ተሸከመው መኖርን ይመርጣሉ።
ስለዚህ የነጻነት አንኳሮች የሆኑት የንብረት መብት፣ በራስ ሀብት የማዘዝ ሙሉ መብት፣ ሀሳብን የመግለጽ መብት፣ንብረት የማፍራት መብት፣ በእኩልነት የመተዳደር መብት፣ወዘተ የራስ መንግስት ለመመስረት በሚታገሉ ቡድኖች ሊረጋገጥ አይችልም።
የራስ መንግስት ለመመስረት የሚታገሉት ፋኖዎች አላማቸው የራሳቸውን ባንዲራ ፈጥረው፤ የክብር ዘብ አሰልፈው የህይወት ዘመን ፕሬዝደንት ሆነው የሚገዘግዙት አገር ለመፍጠር እንጂ ትክክኛ የህዝብን የመናገር፣ የመወከልና የንብረት መብት ነጻነት ለማምጣት አይደለም። ለዚህ ቢሆን ኖሮ የታገሉት የየለቱ ንግግራቸውና ተግባራቸው ሁሉ በራስ ሀብት ስለማዘዝ፣ ስለመናገር፣ ስለመወከልና ስለንብረት ማፍራት መብት ነጻነት ምስክር ሆኖ ይታይ ነበር። ኦነጋውያንም የሚታገሉት ለነጻነት ቢሆን ኖሮ የተለየ አስተሳሰብ ባላቸውና በሰላ በሚሞግቷቸው የኢትዮጵያ ብሔርተኞች ላይ አይን ያወጣ ስድብ፣ ዘለፋ፣ ማዋረድ፣ ተክለ ስብዕና ገደላ፣ ጥላቻና ርኩስ መንፈስ የተሞላበት ንግግር በማራባት አይጠመዱም ነበር። ለነገሩ ነጻነት ለማምጣት የራስ መንግስት ለመመስረት መታገል አያስፈልግም። የራስ መንግስት ለመመስረት ሳትነሳ በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትህ ታገኛለህ። የኦነጋውያን መንፈስ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። የራሳቸውን መንግስት ለማቆም ሲሉ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን የሚተባበሩ ይመስለኛል። ከሰይጣን መንፈስ ነጻነት ሊቀዳ አይችልም። ከሰይጣን መንፈስ የሚቀዳው ሁሉ ብሩቁ የሆነ ጨካኝ አገዛዝ ብቻ ነው።

ከፍ ብዬ በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትህ ታገኛለህ ብያለሁ። ይህን ስል በአንድነት ለነጻነት መታገል የራስ መንግስት መስርቶ ለነጻነት ከመታገል በብዙ እጥፍ ይቀላል ለማለት ነው። ዛሬ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ብትሆን ኖሮ 95 ሚሊዮን ህዝብ ለነጻነት አብሮ ይታገል ነበር። 95 ሚሊዮን ህዝብ ለነጻነት አብሮ ሲታገል የነጻነት ቀን ሩቅ አይሆንም። ዛሬ የራሳቸውን መንግስት የመሰረቱት ኤርትራውያን ብቻቸውን ቢታገሉ ግን ከአምስት ሚሊዮን ኤርትራውያን ግማሹ ያልህ እንኳ ለነጻነት ለመታገል መነሳቱ ያጠራጥራል። ከፍ ብዬ ኤርትራውያን ለመውቀስ የሚያዳግታቸው አገዛዝ አቁመዋል ብዬ ነበር። ዛሬ ምንም እንኳ በባርነት እየኖሩ ቢሆንም የታገሉለት አገዛዝ ስለሆነ ብቻ ግን የኢሳያስን አገዛዝ «የኛ መንግስት ነው» ብለው ተቀብለው ለመኖር የቆረጡና ለነጻነት ትግል የማይደፍሩ ቁጥራቸው የማይናቅ መሆኑ እሙን ነው። ይህንን አጥር ሰብሮ ለነጻነት ለመታገል የሚነሳው ኤርትራዊ ቁጥር ግፋ ቢል ግማሹ የኤርትራ ህዝብ ቢሆን ነው። በዚህ ስሌት መሰረት የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሊታገል ቢነሳ 2.5 ሚሊዮን ኤርትራዊ ለነጻነት ሊታገል ይችላል ማለት ነው። 2.5 ሚሊዮን ኤርትራዊ በአገሩና 95 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ በአንድነት በሚያደርጉት የነጻነት ትግል መካከል ያለው የነጻነት ቀን ርዝማኔ ልዩነት ግልጽ ነው። 95 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ በአንድነት አይደለም ታግሎ ተራራ ላይ ወጥቶ ሽንቱን ቢሸና የማይቆም ናዳ ይፈጥራል። በአድነት ለነጻነት የመታገል ጥቅሙ ይህንን ያህል ጥልቅ ነው።
«እየተጨቆንን ያለነው ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች የብሄረሰባችን አባላት ስለልሆኑ ነው» በሚል የነጻነት ጥማትን የራስ መንግስት በመመስረት ለማስተንፈው መሞከር መዳረሻው እንደ ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ለነጻነት ዋስትና የማይሰጥ የራስ መንግስት ማቆም ብቻ ነው። ውጤቱም የነበረውን አንጻራዊ ነጻነት በባርነት ቀይሮ ለማማረር የሚቸግር ጨካኝ አገዛዝ ተከናንቦ የሚገኘው ነገር ጥቅም ከተባለ ብጣቂ የቴምብር ወረቀትና የራስ ባንዲራ ብቻ ነው። ትርፉም የነበረን አንጻራዊ ነጻነት መጨረሻው በማይታወቅ ባርነት መቀየር ብቻ ነው።
ስለዚህ «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» በሚል ቅስቀሳ ዘረኛ ድርጅቶችን የምትከተሉ የኔ ትውልድ ወጣቶች አትሸወዱ። «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» በሚል የራስ መንግስት ለመመስረት ድርጅት አቁመው እየታገሉ ያሉት የብሔረሰባችሁ አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ነጻነትን ሊሰጧችሁ አይችሉም። ነጻነት የሚገኘው በአንድነት በሚደረግ የነጻነት ትግል ብቻ ነው። የብሔረሰባችሁ አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ነጻነትን ሊሰጧችሁ ከፈለጉ አገር መመስረት ሳይነሱ በአንድነት ታግለው ሊሰጧችሁ ይቻላቸዋል። የራስ መንግስት ለመመስረት ቢነሱ ግን ግፋ ቢል የሚያቆሙላችሁ አገዛዝ እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ አይነት መንግስት ነው። ይህም ሲደላ ነው። እንደ ሶማሊያ መሆን አለና። ስለሆነም እነሱን በጭፍን ከመከተል ከጥላቻ ወጥታችሁ ዛሬ በሌሎች ላይ እያደረጉት ያለውን ክፋት ነገ አገር ሲመሰርቱ በማይመቻቸው የብሔረሰባቸው አባል ላይም ዛሬ በሌሎች ላይ እያደረጉት ያለውን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ዋስትና የላችሁም። የዛሬ ድርጊት የነገ precedence አለው፤ የዛሬ ድርጊት የነገን ቁልፍ ይይዛልና። በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትን የማታገኝበት ምንም ምክንያት የለም። የራስ መንግስት የመመስረት አባዜ የተጠናዎታቸው ዘረኛ ግለሰቦች ትናንሽ ኢሳያስ አፈወርቂዎች ብቻ ናቸው። ኢሳያስ አፈወርቂ የራስ መንግስት በመመስረትና በነጻነት መካከል አንዳች ግንኙነት እንደሌለ፤ እንዴውም ተቃራኒ እንደሆኑ ፐርፈክት የሆነ ምሳሌ ነው። አበቃሁ!