(ዘ-ሐበሻ) ካለምንም በቂ ካሳና ካለምንም የሕዝብ ይሁንታ በመርካቶ አካባቢ በተለምዶው አሜሪካን ጊቢ አካባቢ በርካታ የድሆች መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ቤቶች በልማት ሰበብ ዛሬ እንደፈረሱ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ::
እነዚህ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ለረዥም ዓመታት የኖሩት ወገኖች የሚኖሩበት ቤት ለሃብታሞች በሚሊዮኖች ብር ስር ዓቱ እየቸበቸበው ሲሆን ለነዋሪዎቹ በቂ የሆነ ካሳ አለመከፈሉ ብዙዎችን እያስቆጣ ነው::
ዛሬ ከፈረሱት መኖሪያ ቤቶች በተቸማሪ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችም እንደፈረሱ ያስታወቁት ምንጮች ሕዝቡ መሬቱ ለሃብታሞች ሲሰጥበት በቁጭት እየተምከነከነ መሆኑን አስረድተዋል::
No comments:
Post a Comment