Monday, April 11, 2016

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች – ሚያዝያ 2, 2016


dollar
ሚያዚያ 02ቀን 2008 ዓ.ም. (April , 2016)
  አጫጭር ዜናዎች
·       በርሀብ ከተጠቃው ሕዝብ የእህል እርዳታ እያገኘ ያለው እጅግ በጣም ጥቂቱ መሆኑ ተነገረ
·         በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙትን የኦሮሞ ገበሬዎች የማፈናቀሉ እቅድ አለመሰረዙ ታወቀ
·         በአዲስ አበባ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ደረሰ
·        በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጎርፍና የእሳት ቃጠሎ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
·         ወያኔ በቫይበርና በሌሎች አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ሊያስከፍል እና ቁጥጥር ሊያደርግ ነው ተባለ
የውጭ ምንዛሪ ጠፋ እየተባለ ባለበት ሁኔታ ወያኔ በየኤምባሲው የአባይ ግድብ ግንባታ አምስተኛ ዓመት በዓል በሚል ፈንጠዝያ በማዘዙ በየኤምባሲዎቹ የወያኔ ባለስልጣኖች ቅዳሜ እለት በውስኪና በቢራ ሲራጩ ቆይተዋል ። ወያኔና አፈ ቀላጤዎቹ ልብወለድን በማጥንጠን ስራው ከቆመ ስምንት ወር የሆነውን የአባይ ግድብ ልክ ቀን ተሌት እንደተገነባ አስመስለው ሰዉን በማታለል ከገንዘቡ ሊለያዩ ደፋ ቀና ማለታቸውም መቀጠሉ ተዘግቧል ። የፖለቲክ ተንታኞች ግን በአሁኑ ዙር ለወያኔ ሰለባ የሚሆን ዜጋ የለም ሊኖር አይገባም ሲሉ አሳስበዋል ። በሙስና የሚጠየቀው የወያኔ ጄኔራል ክንፈ ሜቴክ በሚለው መበዝበዣ ተቋም አማካኝነት ግድቡ የሚያስፈልገውን 10 ትላላቅ ተርባይን ለመስራት ስራውን ከተረከበ በኋላ የግድቡን ስራ ለሁለት አመት እንዲዘገይ የተደረገ ሲሆን እስካሁን ድረስ ለስምንት ወር ያህል ስራው መቆሙ ይታወቃል። ለቻይናና ቡልጋሪያ በተሰጠ ኮንትራት የመጣው ተርባይን የሚገጥም ሆኖ ባለመገኘቱ ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተሉ ተጋልጧል ። ሜቴክ( የሚሊቴሪ ቴክኖሎጂ ተቋም) በሚል ስም በመለስ ዜናዊ የተቁቋመውን መስሪያ የሚመራው ጄኔራል ምንም የቴክኒክ ዕውቀት የሌለው ሲሆን በመስሪያ ቤቱ የተቀጠሩት 95 በመቶ ወያኔዎችና የትግራይ ተወላጆች ደግሞ ለታጋይ ጡረታ በሚል የተመደቡ እንጂ እንኳን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከክላሺን መፍታትና መግጠም ውጪ ችሎታ የሌላቸው መሆኑ ይታወቃል።
 ወያኔ አደገ ተመነደገ የሚለው ኤኮኖሚ ወደ ውድቀት እያመራ ነው በማለት የፖለቲካ ታዛቢዎች አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ ። ድርቅና ረሃብ፤የኑሮ ውድነት፤ በስፋት የሚታየው ስራ አጥነት፤ የመብራት ሀይል እጦት፤ የ ፋብሪካዎች ምርት መተጓጎል፤ የአርሶ አደሩ ከመሬቱ መፈናቀል፤ የጦርነት ሁኔታ መብዛት እና ሌሎች ሁኔታዎች ለዚህ የአይቀሬ ለተባለው ውድቀት አስተዋጾ እየሰጡ መሆናቸውም ተሰምሮበታል ። ከሁሉም በላይ ግን ሞኝ የያዘው ፈሊጥ እንዲሉ የወያኔ የዘረኝነትና የብሄር ብሄርሰብ አባዜ ብዙ ቀውስ ማምጣቱ ተጠቅሷል ። የብሄረሰብ ኮታ ተዋጾ በሚል ምንም ችሎታ የሌላቸው ሰዎችን በሀላፊነት ቦታ ተመድበው ስራን በየፈርጁ መበደላቸው ላለው ቀጣይ ለሆነው ሁለገብ ቀውስና ውድቀት ተጠያቂ ነው ብለዋል ። በየቁልፍ ቦታዎች የተመደቡት ወያኔዎች የዘር ኮታን ከማብዛት ውጪ ይህ ነው የሚባል ችሎታ እንደሌላቸው ተቋሞችን ለኪሳራ ማብቃታቸው ምስክር ነውም ተብሏል

national bank of ethiopia

 በፓናማ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ደብቀዋል ተብለው ከተጋለጡት መሪዎችና ባለሀብቶች ውስጥ በርካታ ገና ስማቸው ያልተገለጠ ወያኔዎች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል ፡፤ በቅርቡም ማንነታቸው በይፋ ይታወቃል የተባለ ሲሆን በርካታ ወያኔዎች በማሌዚያ፤በለንደን፤በኒውዮርክና ስዊስም ገንዘብ ሰርቀው ማስቀመጣቸው ከዚህ በፊት መጋለጡ ይታወሳል ።
 በደቡብ ሱዳን ለወያኔ የተሰጠው የቀድሞ የጋምቤላ አስተዳዳሪ ኦኬሎ አኳይና አምስት አብረው ተከሳሾች በተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ መባላቸው ታወቀ ። ኦኬሎ ተሰዶ የኖርዌይ ዜጋ ቢሆንም ኖርዌይ የረባ ጠበቃም እንዳልቀጠርችለት የሚያሙ ታዛቢዎችም አልጠፉም ተብሏል ። ኦኬሎ ወያኔ በጋምቤላ ባደረገው ጭፍጨፋ ዋናው ተጠያቂዎች መለስ ዜናዊ፤አባይ ጸሃዬና በወቅቱ ባለስልጣን የነበረው ኦክተር ባርናባስ ናቸው ብሎ በመክሰሱ ወያኔ ሲያሳድደው እንደነበር ታውቋል ። በሰው ፍጅት ወንጀል አባይና ባርናባስ አሁንም ቢሆን መከሰስና ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ግለሰቦች ናቸው በማለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ከዚህ በፊት መግለጹ የሚታወቅ ነው ።
 ተጨማሪ የቤት እስራዔሎች ቤተሰቦች በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሊመጡ ስለሚችሉበት ሁኔታ የእስራዔል ገዥ ፓርቲ ከአጋሮቹ ጋር ስምምነት የደረሰ መሆኑን በዚህ ሳምንት በሰጠው መግለጫ ገልጿል። በመመሪያ መሰረት 1300 የሚሆኑት እንዲመጡ የተፈቀደ ሲሆን ወደፊት ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊጨምር የሚችል መሆኑን ተገልጿል። ባለፈው ወር በእስራዔል አገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል እንዲመጡ በመጠየቅ ከፍተኛ ትዕየንተ ሕዝብ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የእስራዔል መንግስት ነገሩን ችላ በማለት ኢትዮጵያውያኑን የፈቃዱን ውሳኔ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ባለፉት ጥቂት ቀናት አንዳንድ የፓርላማ አባላት ባደረጉ ጥረትና እንዲሁም ተቃውሞውና አድማው የጋራ መንግስቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ስለገባው ገዥው ፓርቲ ሀሳቡን ቀይሮ ቤተእስራኤሎቹ ወደ እእስራኤል እንዲመጡ ፈቅዷል።
 በአስመራ ከተማ በግድ ታፍሰው በካሚዮን ተጭነው ወደ ጦር ማሰልጠኛ ሲወሰዱ የነበሩ ወጣቶች ከተሳፈሩባቸው መኪናዎች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በሻዕቢያ ወታደሮች በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። የተገደሉትና እና ምን ያህል እንደሆኑ ለጊዜው ባይታወቅም ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ካሚዮኖቹ የሚሄዱበትን መንገዶ በአውቶቡስ አማካይነት ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ የወጣቶቹ ዘመዶችና ጓደኞች በሙሉ በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። የሻዕቢያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ የሰጠው መግለጫ የለም። በሻዕቢያ ውስጥ የወታደራዊ አገልግሎት የጊዜ ወሰን የሌለው መሆኑ ሲታወቅ አብዛኛዎቹ እድሜ ልካቸውን ሲያገለግሉ የሚቆዩ መሆናቸውና የኑሮው ሁኔታቸውም በጣም አሰቃቂ እንደሆነ ይነገራል። ይህ አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታና የሻዕቢያን አፈና ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች እና ወደ አውሮፓ መሰደዳቸው በየጊዜው የተገለጸ መሆኑ ሲታወቅ የሻዕቢያ አገዛዝ ከፍተኛ አፈናና ጭፍጨፋ ከሚያካሄዱ የአለም አገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው በማለት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸው በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ቆይተዋል።



No comments:

Post a Comment