Wednesday, April 20, 2016

የአማራ ምሁራን ፣ የወገናችሁን እርም ትበሉ ዘንድ እንዴት ተቻላችሁ?! – ልዩ ልዩ ካርታዎችን የያዘ መረጃ

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች | 

የአማራ ምሁራን ፣ የወገናችሁን እርም ትበሉ ዘንድ እንዴት ተቻላችሁ?!

በቅርቡ የግል የምርምር ጥናቴን ለማካሄድ ፈለጌ ይጠቅሙኛል ያልኳቸውን መረጃዎች ፍለጋ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን (CSA) ድረ-ገፅን ተመልከቼ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ ነበር ‘Atlas on Selected Welfare Indicators of Ethiopian Households’ የሚለው ሰነድ ላይ አይኔ ያረፈው፡፡ በCSA ና በአለም አቀፍ ባለሙያዎች ትብብር በ2004 GC የተሰበሰበን መረጃ አጠናቅሮ የያዘ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ክልልና ዞኖች ደረጃ  ስለ ህብረተሰቡ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ነባራዊ ሁኔታ መረጃ እንዲሰጥ እና በመንግስት ደረጃም ለፖሊሲ ዝግጅትና ትንተና እንዲያገለግል ተብሎ የተዘጋጀ ቁልፍ ሰነድ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሳይንሳዊ ማጣቀሻዎችን ከማካተት ውጭ፣ ሰነዱን እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ፡፡ እስኪ አንብቡና እናንተው ፍረዱ። 
  1. የጤና ባለሙያዎች እገዛና ክትትል አገልግሎት ተደርጎላቸው የሚወልዱ ነፍሰጡር እናቶች (Delivery Attendance in Modern Way
Amhara
ይህ ካርታ  በወሊድ ጊዜ በአዋላጅ ነርሶች ድጋፍ ያገኙ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ማህበረሰባዊና ክልላዊ ንፅፅር ያሳያል፡፡ በወሊድ ጊዜ  በባለሙያ መታገዝና ጥሩ እንክብካቤ ማግኜት ለእናትና ልጅ ጤንነት  አንዱ መሰረታዊና በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን አገልግሎቱ በሌሎች የማህበረሰብ ክልሎች በሚገባ እንዲተገበር ተደርጓል።
ከካርታዉ በግልፅ እንደሚታየዉ በአማራ ክልል በአዋላጅ ነርሶች ድጋፍ የሚፈፀም ወሊድ ከ6  በመቶ  በታች ነዉ፤ ይህም ከሀገሪቱ በጣም አስከፊ ደረጃ ላይ ያለ ነዉ፡፡ ይህ ፖሊሲያዊ አሰራር አዲስ ለሚወለዱ አዳጊህጻናት ሞት ያለዉን አስተዋጽኦ  ለመረዳት  ሰው ሆኖ ከመፈጠር ያለፈ ህሊና አይጠይቅም።  በአማራ ክልል ያለዉ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ሞት ከሀሪቱ በጣም ከፍተኛ መሆኑን በ 2013 GC አቶ/ ዶ/ር መኮንን እና ሌሎችአጋሮቹ  ይህን አስከፊ ሁኔታ በሳይንሳዊና በመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ላይ ተመርኩዘው በፃፉትና በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስምና ተቀባይነት ባለዉ BMC ጆርናል የታተመዉን የጥናት ጽሑፍ እንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል፡፡ ምናልባትም ይህ ጉዳይ ለአማራ ህዝብ ቁጥር መቀነስ (በ1999 ዓ.ም ህዝብ ቆጠራ መሰረት) አንዱ ምክንያት መሆኑ ብዙወችን ማስማማቱ አይቀርም።
  1. የልጆች ጤናማ ያልሆነ አሰተዳደግ መኖር (Prevalence of Stunting)
Amhara 2

ከእድሜ ጋር የተመጣተነ የልጆች እድገት (በተለይም ቁመት) ከጤናማ አመጋገብ ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህ ካርታ በኢትዮጵያ ያለዉን ጤናማ ያልሆነ እድገት ያላቸዉን ልጆች ስርጭት ያሳያል፡፡ በዚህም  በአማራ ክልል ያለዉ የሕጻናት መጎሳቆል ከሀገሪቱ የማህበረሰብ ክልሎች በጣም የከፋ ደረጃ ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡
ለረጅም ጊዜ  የተመጣጠነ ምግብ አለማገኘትና በችግር ማቅ እንዲወድቁ መደረጉ የማመዛዘን ችሎታ እና እዉቀት የመሻት ብቃትን እንደሚጎዳ በሳይንስ የተረጋገጠ እውነታ ነው (ለምሳሌ Kar et al. 2008) ፡፡ ምንም እንኳ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድምታው/ተጽኖው ትንሽ ሊመስል ቢችልም በረጅም የጊዜ ሂደት ሲደመር ግን ውጤቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው፤ በተለይ የወደፊቱ ትውልደ አማራ የሆኑ ሃገር ተረካቢ  ሕጻናት የህልውና ሁኔታ ሲታሰብ፡፡
  1. የልጆች መቀጨጭ (Prevalence of underweight)
Amhara 3

የልጆች ከእድሜያቸዉ ጋር የተመጣጠነ ክብደት መኖር  የጤናማ አመጋገብን መኖር አመላካች ነዉ፡፡ ይህ ካርታ በክልሎች ያለዉን የልጆች ጤናማ ያልሆነና ከተፈለገዉ ክብደት በታች የመሆን ንፅፅራዊ ምጣኔን ያሳያል፡፡ በዚህም በአማራ ክልል ያለዉ የልጆች መቀጨጭ በጣም ከፍተኛና ከሀገሪቱ በጣም በአስከፊ ደረጃ ላይ ያለ ነዉ፡፡ ይህም ከላይ የተጠቀሰውን ችግር ጥልቀት የሚያጠናክር ነው፡፡
  1. የቤተሰብ ኑሮ ደረጃ (The proportion of households preferring current living standard)
Amhara 4

ይህ ካርታ በክልሎች መካከል ያለዉን የኑሮ ደረጃ ያሳያል፡፡ ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር በአማራ ክልል ያለዉ በጣም የተበደለና ባሊህ ባይ ተቆርቋሪ ወገን ያጣ መሆኑን የሚያሳይ አሳዛኝ ሁኔታ ነዉ፡፡
  1. መረጃ ተደራሽነትና ሀገራዊ ውሳኔ ሰጭነት – Information access: particularly Radio Ownership
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ካሉት የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች መካከል ሬዲዮ በጣም ጠቃሚዉና ዝቅተኛው ነዉ፡፡ ይህ ካርታ በክልሎች መካከል በአባወራ ደረጃ ያለዉን የሬዲዮ ሰርጭት ያሳያል፡፡በአማራ ክልል ከአስር አባወራዎች መካከል በአንዱ እንኳን ሬዲዮ ያለዉ ማግኘት አይቻልም፤ ይህም ከሌሎች ክልሎች አንፃር ሲታይ በጣም ወደኋላ እንዲቀርና ለሀገራዊ ጉዳዮች እንዳይሰጥ የተደረገ መሆኑን ያሳያል፡፡
በዚህ የመረጃ ዘመን እንደ ሬዲዮ ያሉ በጣም በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ የመረጃ  ምንጮችን ማግኝት እንዳይችል  መደረጉ በብዙ መልኩ ተፅእኖ አድርሶበት ይገኛል ፡፡  ለምሳሌ፣ የአማራ ክልል በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ተተብትቦ እያለ (ከላይ ከሌሎቹ ክልሎች በባሰ ሁኔታ ኑሮው እንደመረረው ቢገልፅም) ምናልባትም የመረጃ እጥረት በክልሉ ለሚታየው   ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መልስ አለመስጠት ራሱ የሆነ ተፅዕኖ ማድረሱ  አልቀርም፡፡
ከሌሎች ጋር ሲወዳደር በክልሉ የ HIV/AIDS መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች ግንዛቤ አለመኖር (በተመሳሳይ ሪፖርት የተገለፀ) ፤ እንዲሁም ከላይ እንደተገለፀዉ የነፍሰ ጡሮች የጤና ባለሙያ አገልግሎት ያለማግኘት ችግር ጋር ተዳምሮ የቫይረሱን ከእናት ወደልጅ የመተላለፍ እድል ከፍተኛ መሆኑን ይገፃል፡፡ ይህም ጉዳይ ለአማራ ህዝብ ቁጥር መቀነስ (የ1999 ዓ.ም ህዝብ ቆጠራ ይመልከቱ) አንዱ መሆኑን ብዙወች ከመስማማት አልፈው በየመድረኩ  በመረጃ አስደግፈው ማቅረባቸው የ፡amhara 5

No comments:

Post a Comment