Sunday, April 10, 2016


የደደቢት ወያኔዎች ትግሬ ቢሆኑም ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያቸው ድል ማግስት መቀሌ ተገኝተው በትግረኛ ባደረጉት የአደባባይ ንግግር እኛ ከሥልጣን ብንወርድ ነፍጠኞች አንድ ቀን አያሳድሩዋችሁም ማለታቸውን የአይን እማኝነታቸውን የሰጡ ሰዎች በወቅቱ አስነብበውናል፡፡
ይህ የአቶ መለስ ዘረኛ የጥላቻ ዘር  አብቦ እንዲያፈራ የሚያግዝ ተግባር ላለፉት ሀያ አመታት ቁጥራቸው ቀላል በማይባል  ወያኔን እንቃወማለን በሚሉ ሰዎች ሲፈጸም አይነላል እያየንም ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከጽሁፋቸውና ከንግግራቸው ይዘት ብሎም አጥብቀው ከሚጮሁበት ወቅት ምንነት አንጻር ድርጊቻው ሲመዘን አላማቸው ይሄው መሆኑን መገመት ይቻላል፡፡ ከምር ወያኔን የሚቃወሙትና በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ከልብ የሚሹት ሰዎች ግን ይህን ለማድረግ የበቁበትን ምክንያት መገመት ቢቻልም በወያኔ ቦይ እየፈሰሱ መሆናቸውን መገንዘብ ለተያያዙት ትግል እንደማያጠቅምም መረዳት አንደምን ተሳናቸው የሚያሰኝ ነው፡፡
ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ለተፈጸሙት ጥፋቶች ሁሉ ተጠያቂው  አቃጁ መሪው ፈጻሚና አስፈጻሚው  የደደቢቱ ወያኔ መሆኑ ያከራክረም፡፡ ይህ ማለት ግን እርሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሌሎች በማቀዱ ሆነ  በመሪነቱና በማስፈጸሙ ላይ ይህ ነው የሚባል ድርሻ ባይኖራቸውም በፈጻሚነት  ተሰልፈው እንደውም አንዳንዶች ከወያኔ በላይ ወያኔ ሆነው አጥፍተዋል እያጠፉም ነውና ድርሻው ይለያይ ካልሆነ በስተቀር ተጠያቂው ብዙ ነው፡፡መተባበርም፣ ጥፋትን ማስቀረት ሲቻል ዝም ማለትም ያስጠይቃል፡፡
ነገር ግን ውግዘቱ ተቃውሞውም ሆነ ትግሉ በእነዚህ ላይ ሲያተኩር አይታይም፡፡ የሥልጣንም ሆነ የቁስ ፍርፋሪ እየተጣለለት ውሻ በበላበት ይጮኻል እንዲሉ ሆኖ ወገኖቹን መውጫ መግቢያ የሚያሳጣውን የሚገድል የሚያስረውን የሚዘርፍ የሚያዘርፈውን የብሄራቸውን  አባል አረ! አንደውም ወንድማቸውን አለያም የአጎት የአክስት ልጅን ምንም ሲሉ የማያሙ   ትግረኛ ተናጋሪውን ወገን በጅምላ ለመወንጀል ለመውቀስ ብሎም ለመዝለፍ ያላቸው ድፍረት ይገርማል፡፡
የደደቢቱ ወያኔዎች በሙሉ ትግሬዎች መሆናቸው እንደማያከራክር ሁሉ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑ እንዲሁ ሊያከራክር ባልተገባ ነበር፡፡ ወያኔን በዘረኝነት እየከሰሱ ሀገሪቱን ለአደጋ ያጋለጠውና ለችግር የዳረገው የዘር ፖለቲካ በማራመዱ ነው እያሉ እየተቃወሙ እነርሱ  ትግረኛ ተናጋሪውን በሙሉ  ከደደቢት ወያኔዎች ጋር ደምረው ሲያወግዙና ሲያጥላሉ  ራሳቸው ዘረኝነትን እያራመዱና በወያኔ ቦይ አየፈሰሱ ስለመሆኑ መረዳት እንዴት አንደሚቸግራቸው ግራ የሚያገባ ነው፡፡
ወያኔዎች በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ጉዳያቸውን የሚያስፈጽሙትና ዓላማቸውን የሚያሳኩት  ከኋላ ሆነው ከፊት በተቀመጡት የአካባቢው ሰዎች አማካኝነት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ግድያው፣ አስራቱ፣ ድብደባው፣ የመሬት ቅርምቱ፣ የሀብት ዘረፋው፣ ማፈናቀሉ ወዘተ ሁሉ የሚፈጸመው በየአካባቢው ሥልጣን ላይ ባሉ ሰዎች ቀዳሚ ተዋናይነት መሆኑ እንዲህ እየታወቀ በዚህ ድርጊት ትግረኛ ተናጋሪውን በሙሉ መወንጀል ከህሊና ዳኝነት ይልቅ ስሜታዊነት ያየለበት ተግባር ነውና ፍትሀዊ ሊሆን አይችልም፡፡
ከስሜታዊነት ወደ ህሊና ዳኝነት በመሸጋገር  ሁለት ነገሮችን ማድረግ ቢቻል ለዛሬው ትግል ውጤታማነት ለነገውም ኢትዮያዊ አንድነት
ይበጃል፡፡ የመጀመሪው ትግረኛ ተናጋሪውን በሙሉ ከደደቢቱ ወያኔ ጋር ደምሮ በጅምላ ማውገዙን መክሰሱንና መዝለፉን ማቆም፤ሁለተኛው የቃል ውንጀላና ውግዘታችንንም ሆነ የተግባር ትግላችንን ከጉያችን መጀመር፡፡ እየገደሉን የሚሾሙትን፤ እየዘረፉ የሚያዘርፉትን፤ ጃስ እየተባሉ የሚነክሱንን፤ ከጉያችን አስቀምጠን ወያኔ ወያኔ ማለቱ የትም አላደረሰንም ወደፊትም የትም አያደርሰንም፡ጠብደል ውሻ በግቢው ያለን ባላንጣ  ከቤቱ ገብቶ ለማነጋገርም ሆነ ርምጃ ለመውሰድ መጀመሪያ ውሻውን ማለፍ ግድ ነው፡፡ ውሻው የሚበላበት ስራው ነውና አላስገባ ብሎ ይከላከላል፤ ከቻለም ይነክሳል፤ባለቤቱንም ያነቃል፡፡ ስለሆነም ባለቤቱን ለማግኘት ሲታቀድ ውሻው ይህን ተግባሩን እንዳያከናውን ማድረግ የሚቻልበት ብልሀት ካልታሰበ የተፈለገው አለመሳካት ብቻ ሳይሆን መቀደምም ይከተላል፡፡
ፕ/ር ዓሥራት ወልደየስ   በህክምና ሙያቸው ዘር ቋንቋ ሀይማኖት ሳይለዩ የአያሌ የሰው ልጆችን ህይወት ከሞት ታግለው ያስጣሉ እውቅ ቀዳጅ ሀኪም ነበሩ፡፡ ህይወታቸው በወያኔ ባይቀጭ ኖሮም በርካታ የሰው ልጆችን ህይወት በታደጉ ነበር፡፡ በወቅቱ የፖለቲካ ስካር ለአደጋ የተዳረገውን አማራ ለመታደግ ሙያቸውን ቀይረው የመአህድ ፕሬዝዳንት በመሆን የፖለቲካ ትግሉን የጀመሩት ፕ/ር ኣሥራት ወልደየስ ከሁለት አመት ያለፈ በትግሉ አልቆዩም፡፡  ከጅምሩ ያገኙት የህዝብ ድጋፍና የፓርቲው  እንቅስቃሴ ያስፈራው ወያኔ እስከ ዛሬም ድረስ መታወቂያው የሆነውን የሀሰት ክስ መስርቶ ወህኒ አወረዳቸው፡፡ ፕ/ር የታሰሩት ዛሬ  ለአፍሪካ ህብረት ተሰጥቶ ቻይና ፎቅ በፎቅ ባደረገችው ቦታ ላይ በነበረው አዲስ አበባ ወህኒ ቤት ነበር፡፡ ርሳቸውን ለመጠየቅ ከምዝገባ እስከ ፍተሻ የነበረው ሂደት አናዳጅም እልህ አሲያዥም ሲሆን በተለይ ጫማ እስከማስወለቅ የሚደርሰው ፍተሻ ለሴቶች በጣም ፈታኝ ነበር፡፡ ፈተናው ሲገባ ብቻ አልነበረም፣ የሚወጣውም ተሰልፎ፣ ተፈትሾ፣ መታወቂያ ተቀብሎ ነውና በዚህ ግዜ አንተ/ቺ ከፕሮፌሰሩ ጋር ምንድን ነው ያወራኸው/ሽው በምልክት ተነጋግራችኋል ወዘተ በሚል መታገት ያጋጥማል፡፡
ፕ/ር አስራት በመደበኛ የመጠየቂያ ቦታቸው ሆነው የሚመጣውን ሁሉ በየተራ የሚያነጋግሩት ሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ ታጥቆ ጠብ-መንጃ በወደረ ታጋይ  እየተጠበቁ ሲሆን ሲቪል ለባሾች ደግሞ ከጠያቂው ጋር ተመሳስለው የሚነገረውን ብቻ አይደለም የሰውነት እንቅስቃሴን ሁሉ ይከታተላሉ፡፡ ይህን የተላመዱት ፕ/ር ብዙ ግዜ የሚፈልጉትን ነገር የሚነግሩን በምሳሌ  ነበር፡፡ ታዲያ ከዛ ስንወጣ እንዲህ ያሉት ይህን ለማለት ነው በሚል እንከራከራለን፤የማንተማመንበትም ግዜ ነበር፡፡
በዚህ መልኩ ካጫወቱንና ከማረሳቸው አንዱ ከላይ የገለጽኩትን ጉዳይ የሚያጠናክር ስለመሰለኝ ልጠቅሰው  ፈለጌ ነው  ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖብኝ ስለ ወህኒ ቤቱ  ያነሳሁት፡፡ በተለይ የፕ/ር ዓሥራትን ስም እየጠሩ ፈለጋቸውን ተከታይ ነንም እያሉ ለአማራ እንደሚታገሉም እየተናገሩ ትግረኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ በመሉ በደደቢቱ ወያኔ ቅርጫት ውስጥ ከትተው ለሚያወግዙ ሲያልፍም ለሚዘልፉ ሲብስም ጠላት ለሚሉ  ጠቃሚ ምክር ይመስለኛል፡፡
ወቅቱ ልክ አንደ አሁኑ ከወያኔ አልፎ ትግርኛ ተናጋሪውን በሙሉ በወያኔነት ፈርጆ መወንጀል ማውገዙ የበረታበት ነበር፡፡ እናም ከፕ/ር ጋር በወህኒ ቤት ስናወራ ጉዳዩ ተነስቶ በምሳሌ  ከነገሩን በአጭሩ ልግለጽ፡፡ ጣሊያን ተሸንፎ ከሀገር በወጣ ግዜ በርካታ ጣሊያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርተው ነበር፡፡ ከእነዚህ አንዱ በሚኖርበት ሰፈር ሲወጣ ሲገባ ዘመዶችህ ወገኖቻችን በመርዝ ጋዝ ጨርሰው፣ በአካፋና ዶማ ጨፍጭፈው  እያለ ሰው ይነዘንዘው ነበር፤ ታዲያ አንድ ቀን ምርር ብሎት ምን እኔ ላይ ጣታችሁን ትቀስራላችሁ፤እኔን መውጫ መግቢያ ታሳጡኛላችሁ፤ከእኛ ወታደሮች እየቀደሙ ሲተኩሱ ሲገሉ ቤት ሲያቃጥሉ የነበሩት፤ የአርበኞችን ምሽግ እየጠቆሙ ሲያሲዙ የነበሩት የእናንተው ወገኖች አልነበሩም ወይ? አላቸው በማለት አስረዱን።
አዎ ዛሬም ከየቤታችን አንስቶ እስከ ቤተ መንግሥቱ ድረስ የወያኔ መሳረያ ሆነው ዜጎችን የሚበድሉ ሀገሪቱንም እየገደሉ ያሉ ከሁሉም ብሄር ያሉ ናቸው፡፡ታዲያ በየጉያችን ያሉ አጥፊዎች ላይ ተቃውሞ ማሰማትም ሆነ ጣት መቀሰር ሳንችል   በደም ይገናኛሉ በቋንቋ ይግባባሉ በሚል ትግረኛ ተናጋሪውን ሁሉ ወያኔ ብሎ መፈረጅ ከዛም አልፎ በአጥፊነት መወንጀል ለወያኔ ፍላጎት መሳካት መርዳት ካልሆነ በስተቀር ተገቢና ትክክል የሚሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡
የአንዳንዶች መከራከሪያ ወያኔ ነግሶ ትግሬዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፤ሌላው ቢቀር ሲቃወሙ አይሰሙም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ማስተዋል ከተቻለ በወያኔ ንግስና ተጠቃሚ የሆነው ትግረኛ ተናጋሪው ብቻ አይደለም፤ ከሁሉም  የሀገሪቱ ክፍል ለወያኔ ያደረ፣ አብልቶ መብላቱን የተካነ፣ የአባትህ ቤት ሲበዘበዝ አብረህ በዝብዝ የሚለውን ብሂል የተከተለ ተጠቃሚ ሆኗል፤ ወደ ፊትም እስከጠቀመ ድረስ ይጠቀማል፡፡ ታዲያ የትግረኛ ተናጋሪዎቹ ተለይቶ ጎልቶ ለውግዘት የሚያበቃው ለምንድን ነው? ወያኔዎች ትግራይን የክፉ ቀን ምሽጋቸው ለማድረግ ካላቸው ዓላማ አንጻር ትግረኛ ተናጋሪው ወገን በሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዲጠላና ሞቴን ከወያኔ ጋር ያድርገው የሚል ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሰርተዋል እየሰሩም ነው፡፡ ለዚህ ዓላማቸው መሳካት ከፈጸሙዋቸው እኩይ ተግባራት አንዱና ዋናው  ትግራይን በተለየ ሁኔታ ማልማትና ትግሬዎችን በተለያየ መንገድ እያሰባሰቡ በአንድ ጀንበር ከበርቴ እንዲሆኑ በማስቻል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከጥላቻም አልፎ የጠላትነት ስሜት አንዲያድርበት ማድረግ ነው፡፡ ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው የሚሉ ሰዎች እንግዲህ ይህን የወያኔን ዓላማ ነው እያሳኩ ያሉት፡፡ከመነሻው የተገለጸው የአቶ መለስ ዘረኛ ስብከት በትግረኛ ተናጋሪው አንዲታመን ነው የሚያግዙት።
ትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በወያኔነት የሚፈረጁበትና የሚኮነኑበት ድርጊት ሁሉ በሌሎች ኢትዮጵያውያን የተፈጸሙና የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ ታዲያ ኦሮሞ በሙሉ ኦህዴድ፣ አማራ በሙሉ ብአዴን ደቡብ በሙሉ ደኢህዴግ ወዘተ ሳይባሉ ትግሬዎችን ብቻ ጠቅልሎ ወያኔ ማለትና ማውገዝ ሲከፋም መጥላት ከወያኔ ያልተናነሰ ዘረኛ መሆንና አውቆ በድፍረት ሳያውቁ በስሜት የወያኔን ዓላማ ማሳካት ነው፡፡
ብዙ ግዜ የሚጠቀሰው የዛፎች ምሳሌም በዚህ ጽሁፍ ለተነሳው ሀሳብ በቂ ገላጭ ይመስለኛል፡፡  ምሳሌው በአጭሩ ዛፎች መጥረቢያ ጨረሰን ብለው መከሩ፣ ሊከሱትም ተወካይ መርጠው ወደ ችሎት ላኩ፤ ተወካዮቹ በመንገድ ላይ ሳሉ አንዱ ምስጢሩ ተገለጠለት፤ለመጥረቢያ ዛቢያ ሆነው የሚያገለገግሉት ከመካከላችን የሚበቅሉ ጠማማ እንጨቶች ናቸው፤ አነርሱ ባይኖሩ መጥረቢያ ዛፍ ለመቁረጥ አቅም አይኖረውም፤ ስለሆነም መጥረቢያን ከመክሰስ የራሳችንን ጠማሞች ከመካከላችን እናስወገድ አለ፤ ሁሉም ነገሩን አመኑበት፤ተስማሙ፤ ክሱን ሰረዘው ጣማማዎችን የማስወገድ ስራ ላይ ተሰማሩ፡፡
እህ እኛስ ምስጢሩ የሚገለጥልን መቼ ይ

No comments:

Post a Comment