Wednesday, April 13, 2016

ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ረሀብ በኢትዮጵያ፡ ለመሆኑ ጋይሌ ኢ. ስሚዝ ምን እያለች ነው?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
Gayle Smith pixየጸሐፊው ማስታወሻ፡  ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ጽሁፍ የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለሆነችው ለጋይሌ ኢ. ስሚዝ እ.ኤ.አ መጋቢት 16/2016 በቀጥታ የጻፍኩላት ደብዳቤ ትክክለኛ ቅጅ እና ለዚህም ደብዳቤ ምላሽ በዩኤስኤአይዲ/USAID ረዳት አስተዳዳሪ በቲ.ሲ ኩፐር፣ ከሕግ እና የመንግስት ጉዳዮች ቢሮ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 7/2016 የተሰጠውን ምላሽ ያካተተ ነው፡፡
የላኩት ደብዳቤ ሚስስ ስሚዝ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ በማስመልከት የሰጠችው መግለጫ እውነተኛ ስለመሆኑ እና የፖሊሲ ማብራሪያዎችን ይጠይቃል፡፡
የሚስተር ኩፐር ደብዳቤ በአስተዳዳሪዋ ላይ ስላቀረብኩት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሳይሰጥ እና በተጨባጭ ያቀረብኳቸውን እውነታዎች እና የፖሊሲ ጉዳዮች ገሸሽ በማድረግ አልፎፏቸዋል፡፡
ቀደም ሲል ሚስስ ስሚዝ የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ እንድትሆን ቀርቦ የነበረው ሹመት እንዳይጸድቅ በጥብቅ ተቃውሜ እንደነበር በሰፊው የታወቀ ነገር ነው፡፡ ሆኖም የአሜሪካን ሴናት ሚስ  ስሚዝን ሽመት ስላፀደቀ እና እንደ አጥባቂ  የሕገ መንግስት ባለሞያ ሴናቱ የሰጠዉን ዉሳኔ ተቀብያለሁ  ተፈጻሚነቱንም አከብራለሁ፡፡
የእኔ የጥያቄ ደብዳቤ እንደ አሜሪካዊ ዜግነቴ እና እንደ ግብር ከፋይነቴ በግልጽ በሚያሳስበኝ ጉዳይ ቀጥታ የሚመራ እንጅ እንዲሁ ከሹመት ማጽደቁ ሂደት ጋር በተያያዘ መልኩ በባዶ ግላዊ መከፋት ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡
የሚስስ ስሚዝን ሹመት በመቃወም ሳቀርባቸው ከነበሩት ትችቶቼ መካከል በመጀመርያውትጽሁፌ እንዲህ የሚል ቃል ገብቼ ነበር፣ “የስሚዝን ይፋ ድርጊት እና ውሳኔዎች የአሜሪካ ሕግ በሚፈቅደው እና ባለው በማንኛውም የሕግ አማራጭ ተጠያቂ አናረጋታለን…“
የእኔ የጥያቄ ደብዳቤ ዋናው ዓላማ “እርዳታን ለመጨቆኛ መሳሪያ“ እና ከፍተኛ ጉዳትን እያስከተለ ያለ የሙስና ታሪክ ካለው መንግስት ጋር በተያያዘ መልኩ የአሜሪካ ሕዝብ የግብር ዶላር አጠቃቀም ላይ ዩኤስኤአይዲ/USAIDን ተጠያቂ ለማድረግ ነው፡፡
ጥያቂያችን ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
===========  ==============  =============  ============
እ.ኤ.አ መጋቢት 16/2016
ሚስስ ጋይሌ ኢ. ስሚዝ
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ
አስተዳዳሪ
1300 ፔንሲልቫኒያ አቬኑ፣ ኤንደብልዩ
ዋሽንግተን፣ ዲሲ 20523
በዩ.ኤስ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የተረጋገጠ 
ውድ ሚስስ ስሚዝ፡
እ.ኤ.አ መጋቢት 3/2016 ከጀምስ ኪርቢ ጋር አድርገሽው በነበረው ቃለመጠይቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ስላለው ድርቅ “አዲስ እርምጃዎች“ ለመውሰድ ዓላማ አድርገን እንሰራለን ስላልሽው ሁኔታ ጉዳዩ ከምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለመከታተል ነው ይህንን ደብዳቤ የጻፍኩልሽ፡፡ በደብዳቤየ የቅሬታ ስሞታ ከማቅረቤ በፊት እንዲሁም ጉዳዩ ግልጽ እንዲሆን ገና ከመጀመሪያው የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ሆነሽ እንዳትሾሚ እና ሹመትሽም እንዳይጸድቅ ጠንካራ ተቃውሞ ሳቀርብ የነበርኩ መሆኔን እንድተገነዘቢልኝ እወዳለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 12/2015 የአንቺ ሹመት እንዳይጸድቅ ለዩኤስ ኮንግረስ በመጻፍ ተቃውሞየን አሰምቼ ነበር፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች በርካታ የውትወታ መልኮች እና መድረኮች እንዲሁም በእራሴ ድረ ገጽ ጭምር በመጠቀም ተቃውሞየን ስገልጽ ቆይቻለሁ፡፡
የአንቺ ዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪነት ሹመት እንዳይጽድቅ ስቃወም የቆየሁባቸው ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ፡፡ እነርሱም፣
1ኛ) በአፍሪካ የዴሞክራሲ፣ ነጻነት እና የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መስፋፋት እና መደገፍን አስመልክቶ ያለሽ ታሪክ ደካማ እንደሆነ አምናለሁ፡፡
2ኛ) ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ለአፍሪካ አምባገነኖች ስታደርጊ የቆየሽው የማያወላውል ድጋፍ የአፍሪካን ሕዝቦች ደህንነት ሲጎዳ የቆዬ መሆኑን አምናለሁ፡፡
3ኛ) አፍሪካውያን ለዘላለም ከአሜሪካ ጠንካራ ግብር ከፋይ ሕዝብ ኪስ ጋር ተቆራኝተው የሰብአዊ እርዳታ ተቀባዮች ሆነው እንዲኖሩ ለማድረግ በምታራምጅው የአሜሪካ የአፍሪካ የውጭ ፖሊሲ አቀራረብሽ ላይ ተቃውሞ አለኝ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ይህንን ጉዳይ ግልጽ እያደርግሁ ያለሁት ባለፈው ጊዜ ሳቀርብ የነበረውን ተቃውሞ ለመድገም አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ይህ አስቸኳይ የጥያቄ ደብዳቤ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ በማሰብ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ድርቅ ለመቋቋም ዩኤስኤአይዲ/USAID እያደረገ ያለውን ጥረት በማስመልከት እ.ኤ.አ መጋቢት 3/2016 ለጆን ኪርቢ በሰጠሽው ቃለመጠይቅ እኔን ያስደነቁኝ፣ ግራ ያጋቡኝ እና እንቆቅልሽ የሆኑብኝ በርካታ ነገሮችን ተናግረሻል ፡፡

No comments:

Post a Comment