Wednesday, April 13, 2016

በኢሕኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ የሕወሓት ተሰሚነት እያሽቆለቆለ ነው::ለጄኔራሎች እና ለደህንነት ሹሞች ተማጽኖ ቀርቧል::

የኢህኣዴግ ውጥረትና የኣቦይ ስብሓት ጭንቅ
።።።።።።።።።።።።።
ሰሞኑን ኢህኣዴግ በኣዲስ ኣበባ ስብሰባ ማካሄድ ጀምሮ ነበር።
ስብሰባው ከተጠበቀው በላይ ውጥረት የተሞላበትና የድርጅቶች ሞቧደን የታየበት ነበር። ቡዱኖቹ ህወሓትና ደህዴን በኣንድ በኩል፤ ብኣዴንና ኦህዴድ በሌላ መስመር ተሰልፈው ሲወቃቀሱ ነበር።
ሊቀ መንበሩ ሃይለማርያም ደሳለኝ የቡዱናዊ መንገድ ከተመለከቱ በኋላ የኢህኣዴግ ስብሰባ ኣቁመው የድርጅቶቹ በግላቸው ገምግመው እንዲመለሱ በማለት መላው ቀይረው ጉብኝት ለማድረግ ብለው ወደ ምዕራብ ኣፍሪካ ሄደዋል።
በኢህኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ለመሳተፍ የሞከሩት ኣቦይ ስብሓት ነጋና ኣቶ ኣባይ ፀሃየ “ስብሰባው ለኢህኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ብቻ የሚመለከት ስለሆነ ኣዳራሹ ለቃቹ ውጡልን” ተብለው በብኣዴን፣ ኦህዴድ ድርጅቶችና በነ ኣባይ ወልዱ የሚመራው ኣንጃ ተቃውሞ ስለ ደረሰባቸው በብስጭት ሳይወዱ በግድ ከስብሰባው ወጥተዋል።
ኣቦይ ስብሓት ነጋ በራሳቸው የደረሳቸው ጠንካራ ተቃውሞና ህወሓት በኢህኣዴግ የነበረው ተሰሚነት ማሽቆልቆሉ ኣስደንግጧቸዋል።
ለዚህ ጭንቀታቸው መፍትሄ ብለው የመረጡት መንገድ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ፕ/ጀነራል ሳሞራ ዮንስና የብሄራዊ ደህንነት ሃላፊ ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋ በሽምግልና እየያዙዋቸው ይገኛሉ።
የኣቦይ ስብሓት ተማፅኖ “መንግስታችን የቆመው በ60 ሺ መስዋእትነት ነው እያልን የመጣነው ለፕሮፖጋንዳ እንዲመቸን ነው(ህዝቡን ዋሽተነዋል) እንጂ በትጥቅ ትግል የተሰዋው ከ200 ሺ በላይ ውድ የሰው ሂወት ነው” ካሉ በኋላ “ይህ ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለበት ትግላችን እያየነው ወደ ጠላቶቻችን እጅ እየገባ ነው፣ ድርጅታችን ከዚ ውድቀት ለማውጣትና ስርዓታችን ከውድቀት ለማዳን ኣስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ኣለባቹ” የሚል ሓሳብና ተማፅኖ ኣቅርቦውላቸዋል።
በኣዲስ ኣበባ ለስብሰባ የተቀመጠው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ እየደረሰበት ያለው ተፅእኖ ለማብረድ በማሰብ “በትግራይ እየተካሄደ ያለው ልማት የሚቃወም ማንኛውም ሰው ከኣፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ…”የሚል መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።
የኣቦይ ስብሓት በትጥቅ ትግል ስለ ተከፈለው የሂወት መስዋእትነት ለ25 ዓመታት 60 ሺ ሲሉን ቆይተው ኣሁን ደርሰው 200 ሺ ነው የተከፈለው በማለት ስርዓቱ ለማቆየት ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው በመፈለግ ነው።
ስለ ኣጠቃላይ የድርጅቱ ንትርክ መረጃው ሲደርሰን እናካፍላቹሃለን።
Amdom Gebreslasie

No comments:

Post a Comment