Friday, April 15, 2016

አማራነት እስከ ቀራኒዮ ወይስ እስከ ፌስ ቡክ ( ሄኖክ የሺጥላ )

1298

መጥምቁ ዩሃንስ በሉቃስ ፥ በማርቆስ እና በዩሃንስ ወንጌሎች ላይ « እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል» እያለ ይሰብክ ነበር።
ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከውሃ ጥምቀት የተለየ መሆኑን ማሳያ ብቻ ሳይሆን ፥ በውሃ የሚያጠምቀው በመንፈስ ቅዱስ ከሚያጠምቀው እጅግ ያነሰ እንደሆነ ሲገልጥልን እንጂ ። መእ ገብቶን እኛ እቴ!
አማራን ስለ ማዳን ስፅፍ ፥ ስናገር ፥ ስደሰኩር (discourse ) ፥ ከኢትዮጵያዊነት የወጣ ኣዲስ የሚመስል መስመር ይዤ ቆሜ ኣይመስለኝም ። ከሌሎች አማራን ለማዳን ከሚተጉት ጋር ለመፎካከር ወይም ለመገዳደርም ኣይደለም ። ለአማራ ተቆርቋሪ በመምሰል በኣማራ ስም ፀያፍ ቃላቶችን ከሚለዋወጡት ፥ በስድብ እና በዘለፋ ከወያኔ እኩያ መሆን ከፈለጉት ጋርም ዝምድና የመመስረት እቅድ ኖሮኝ ኣይደለም ። በሌላ ጎን እየተካሄደ ያለውን ትግል ለመሸንቆጥ እና ለመሸንቆር ኣማራን እንደ ወንጭፍ ተጠቅሜ የግል ስሜቴን እንደ ኣሎሎ በሰው ጭንቅላት ውስጥ ለመዶል ፈልጌም ኣይደለም ። ስለ ኣማራ ስፅፍ ወይም ስለ ኣማራ ስከትብ የኣማራ ጠላቶች ብዬ የማቸውን ኣካሎች ነቅሶ ለማውጣት ከመሻትም ኣይደለም ። እሱ ቢሆን ኖሮ የኣማራ ጠላት የኢትዮጵያም ጠላት ነው ስለዚህ ስለ ኢትዮጵያ በመናገር ስለ ኣማራ መናገር ይቻላል ብለው ከሚያምኑት ወጎኖች ጎን መቆም እውነትም ነው ፥ ቀላልም ነው ።
አማራ ብዬ ስል ፥ እኔን እስከገባኝ ፥ በጥናትም እና በ ልብ መረዳት ፥ ነባራዊ ሁኔታዎችን በማሰላሰልም እና የኣደጋዎችን ምንጭ በማጤን ፥ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ኣደጋ ውስጥ እንዳለ የተረዳሁትን ያህል ፥ አማራ ደሞ ከሌሎች በተለየ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ስለሆነ ለዚህ ጉዳይ ኣህፅኖት እሰጣለሁ ለማለት ነው። ምን ማለት ነው ? ሰዎች በፖለቲካ ኣመለካከታቸው ሊታሰሩ ፥ ሊገደሉ ይችላሉ ። ሰዎች የተፈጥሮ እምቅ ሃብታችንን ኣናስነካም በማለታቸው ኣሁንም ሊታሰሩም ሆነ ሊገደሉ ይችላሉ ። ትክክል ነው ? ኣይደለም ! ለነዚህ ሰዎች መቆም ኣለብን ወይ ? ኣዎ! ግን ደሞ ሰዎች ፥ በዘራቸው ምክንያት የሚታሰሩ እና የሚገደሉ ከሆነ ይህ የተለየ ጉዳይ ነው ለኔ ። ዛሬ በኢትዮጵያ የምናየውም ይህንኑ ነው ። አንድ ባ’ማራነቱ የሚታወቅ ተቃዋሚና አንድ በኢትዮጵያዊነቱ የሚታወቅ ተቃዋሚ በመንግስት ዘንድ የሚደርስባቸው ቅጣት እጅግ የተለያዩ ስለመሆናቸው ፥ አማራ ስለሆኑ ታስረው የተፈቱት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አድምጠናል፥ ኢትዮጵያዊ ነን ስላሉ ታስረው የተፈቱት የሰጡትንም ምስክርነት እንዲሁ አድምጠናል ። ለምሳሌ ለወያኔ የሚያሰጋው ኢትዮጵያዊ መሆን ሳይሆን አማራ መሆን ነው ። የአማራነትን ኣሻራ ይዘዋል ተብለው የሚታሰቡትን ነገሮች በሙሉ ማጥፋት ደሞ ዋና ስራቸው ስለመሆኑ ኣሁን በቅርቡ ኣባ ዱላ ገመዳ በመንበሩ ላይ ሆኖ በፀሎት ሲመሰጥ የሚያሳየው ፎቶግራፍ ኣንዱ ማሳያ ነው ። ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ጋ በማዛመድ ፥ ወይም በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያሉትን እና የማህበረሰቡ እሴቶች የምንላቸውን ለምሳሌ እምነትን ( ከኣማራነት ማዛመድ ) ፥ ኣንድነትን ( ከ ቀድሞ ስርዓት ናፋቂነት ጋር ማዛመድ ) ፥ ኣረንጓዴ ፥ ብጫ እና ቀይ ሰንደቅ ኣላማን ( ከኣማራ ሰንደቅ ኣላማነት ጋ በማያያዝ ) ፥ ኣድዋ ስንል ( ሲቻል በመንጠቅ ሳይቻል ደሞ በማንቋሸሽ ) ፥ ሃገር እንደ ሃገር ታሪክ እንዳይኖራት የሚደረግበት ዋናው ምክንያት ፥ በነዚህ በሚነገሩ ጉልህ ታሪኮች ውስጥ አማራ ያለው ድርሻ ብቻ ሳይሆን ኣቋም እና ኣቋቋም ከፊት እና ቀጥ ያለ በመሆኑ ፥ አማራን ለመምታት የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን መምታት የሚለው እንደ ዋና ሃሳብ ተወስዶ መተግበሩ ሳይበቃ ፥ ፍቀን እና ቀርፈን ሌጣውን እና መለመሉን ያስቀረነው ኢትዮጵያዊነት አማራ የሚባለው ህዝብ እና ኣማራኛ መንፈስ እስካለ ድረስ መነሳቱ እና ማንሰራራቱ ስለማይቀር ጎን ለጎን ኣማራንም ማጥፋት እንደ ኣንድ ኣብይ የስኬት ግብዓት ተወስዶ የዘር ማጥፋት እና የታሪክ ማፅዳቱ ስራ በተጧጧፈበት ሰዓት ስለ ኣማራ መቆም ከልክ በላይ ልክ ሆኖ በማግኘቴ ነው!!!
መልዕክቴም ሆነ ስሜቴ ፥ የማውቀውን ፥ የገበባኝን ፥ በስስ ነብሴ ውስጥ የሚጉላላውን ፥ የ ኣማራን ስቃይ ለማቆም ባልችል እንኳ መረዳቴን ለመጠቆም ከሚመነጭ ቅን ኣመለካከት ውስጥ የመጣ ስለመሆኑ ግንዛቤ ይኖራችሁ ዘንድ ኣበክራለሁ።
ስለ አማራነት ሳወራ ፥ አማራ የሚለው ቃል ኢትዮጵያ ከሚለው ቃል በምን ያህል ርቀት ላይ እንደተቀመጡ እንኳ መለየት እሰሚዳግተኝ ድረስ ኣጠገብ ላጠገብ የቆሙ ኣንድም ሁለትም መንፈሶች እንደሆኑ እና ያም እንደሚሰማኝ ኣንባቢ ኣሁንም ይወቅልኝ!
አማራ ስል ግን
« ጥንትም ቢሆን ሰው ወገኑን ካዋረደ ለግፍ ጥሎ
ባለቤት ያቀለለውን ባለ እዳ መች ተቀብሎ » ብለው ሃያላን ባለ ቅኔዎች እንደከተቡት ፥ እኔ ባለቤቱ ያላከበርኩትን ኣማራ ፥ ኣማራን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚሰራው እንዲያከብረው ነው ወይ የምጠብቀው ከሚል ግንዛቤ የመጣ ያንን ህዝብ የማዳን ጥሪ ነው ።

ለዚህ ህዝብ ዘወትር ከመጮህ እና ከማልቀስ በተለየ ፋይዳ ያለው ነገር ለማድረግ ኣይደለም በጎሳ በቀበሌም ታስቦም ቢሆን ይህንን የዘር ማጥፋት መድሎ እየደረሰት ያለን ኣካል መታደግ ከተቻለ ፥ ጥያቄው ሰው የማዳን ነውና ነውሩ ምን ይሆን ? ዘረኝነት ? በሃገር ደረጃም ይሁን በዘር ደረጃ እኔን እስከሚገባኝ ኣንድ ሰው ዘረኝነትን ተቃውሞ ሲነሳ እራሱ በመጀመሪያ የዘረኝነት ዘረኛ መሆኑ የግድ ነው ። ዘረኝነትን የሚቃወም ዘረኛ ከሆነ ግን ሌላ ነገር ነው ። ኣማራው በትግሬ ይገደላል ማለት የትግሬን ዘረኝነት ማሳያ ነው ። ኣማራ በትግሬ ስለሚገደል ኣማራ ሁሉ ይነሳና ትግሬ የተባለን ይግደል ማለት ግን ሌላ ዘረኝነት ነው ። ኣማራውን የሚበዘብዘውም ሆነ የማምከኛ መድሃኒት የሚወጋው ትግሬ ከሆነ ትግሬ ነው ብሎ ማለት ከእውነትነት ባሻገር ለትግሬዎች ዘረኝነት ሊሆን ይችላል ። ትግሬዎች ኣንድን ሰው በዘሩ ምክንያት ብልቱ ላይ የውሃ ኮዳ ኣንተልጥለው ሲገርፉት ዘረኞች መባል የለባቸውም ፥ ኣንተ ግን ያንን እውነት በማንነታቸው ጠቅሰህ ስትናገር ዘረኛ ነህ የሚለውን ኣስተሳሰብ ስለምፀየፍ አማራው ተሟጋች ያስፈልገዋል ኣልኩ ። ለዚህም ስለ ኣማራ መፃፍ ፥ መናገር ፥ መቆርቆር እና ሲቻል መሞት የህይወት ጥሪዬ ኣድርጌ ተቀበልኩ ።
ታላቁ መፅሃፍ እንዲህ ይላል «የኀዘን የልቅሶና የጩኸት ድምጽ በራማ ተሰማ ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች ፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድምጽሽን ከለቅሶ ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክየይ ፤ ለሥራሽ ፤ ዋጋ ይሆናልና ፥ ይላል፡፡ እግዚአብሔር ፤ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ። ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ ልጆችሽም ወደ ሀገራቸዎ ይመለሳሉ። » ኤር ፴፮ ፥፲፭ ፡፡
ነቢያት የሚናገሩት ስለ ዘመናቸው ብቻም ኣይደለም ፤ ከዘመን ባሻገር ስላለው ዘመንም እንጂ ። ያለፈውን ብቻ ሳይሆን መፃኢውን በጥበብ እና በምልክት ያስቀምጣሉ ። ከለቅሶ እና ከሃዘን ባሻገር ፥ እንባ ይታበስ ዘንድ ፥ ቁስልም ይጠግ ዘንድ ፥ በጠላት እጅ የወደቁት ኣርነት ይወጡ ዘንድ ፥ ድምፃቸው በኛ ተቆርቋሪነት ይሰማ ፥ ሞታቸው በኛ ለነሱ መቆም ኣፈር የማይሸፍነው ፥ ጡብ የማይከድነው ይሁን ! ኢትዮጵያዊ ሁሉ መከራ ውስጥ ነው ፥ ኣማራ ግን በዘሩ የከፋ መከራ ውስጥ ነው እያልኩ ነው !
የምለው ያልገባው ምን ኣገባው እያልኩ ግን ኣይደለም ! ከተራ ጭቅጭቅ ፥ ሙቀት እና ንቀት ወጥተን ጉዳዩን እስኪ እንመርምረው ። በፌስ ቡክ ተጀምሮ በ ፈስ የሚያልቅ ትግል እንዳይሆን ከልብ ልብ ለልብ መነጋገር እንጀምር ። እንደዛሬ ውሃ ብርቅ ባልነበረበት ዘመን ኣባቶቻችን እና እናቶቻችን « ጋን በጠጠር ይደገፋል » ይሉ ነበር !
በቸር እንሰንብት ( ሄኖክ የሺጥላ 

No comments:

Post a Comment