Wednesday, April 13, 2016

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች – በት/ቤት አካባቢ የአልኮል መጠጥና ሱስ የሚያስይዙ ጎጅ ባህሎች እየተስፋፉ ነው ተባለ

ሚያዚያ 04 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 12, 2016 NEWS)
#በኢትንተርኔት አገልግሎት ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ አገሮች ተርታ ተመደበች፤ የነበሩትንም አገልግሎቶች ስሞኑን ወያኔ አፈነ
#በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤት አካባቢ የአልኮል መጠጥና ሱስ የሚያስይዙ ጎጅ ባህሎች እየተስፋፉ ነው ተባለ
#በወያኔ ጦር ውስጥ መኮንኖች ተይዘው ታሰሩ
#ቦኮሃራም በአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ህጻናት ቁጥር ጨመረ ተባለ
#በብሩንዲ ያልታወቁ ሰዎች በእሩምታ ተኩስ አምስት ሰዎችን ገድሉ ከሰባት በላይ አቆሰሉ
#የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ኃይሎች 16 የአማጽያን አባላትን ይዘው አሰሩ ተባለ
#የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሊቢያ ከአንድነት መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ተወያዩ

ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም.
Ø የእድገትና የልማት ከበሮ በሚደበድባት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጣራ ደርሷል እየተባለ የሚለፈፍላት ኢትዮጵያ በመረጃ ልማት ሰንጠረዥ የመጨረሻ ሶስተኛ ቦታ ላይ እንደምትገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ግልጽ አድርጓል። የኢንፎርሜሽን ዲቨሎፕመንት ኢንዴክክ ባለፈው ዓመት በ1967 የዓለም አገሮች ያደረገውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ጥናቱ በየአየገሮቹ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ስፋትና ጥራት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭትና ኔትወርክ የማግኘት አቅም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትን ለኢንተርኔት የደረሱ ዜጎች ቁጥርን ግምት   ውስጥ ያስገባ እንደነረ ሲታወቅ በውጤቱ በሰንስጠረዥ መጨርሻ 167 ኛ ያወጣቸው ቻድ ስትሆን 166ኛ የሻዕቢያዋ ኤርትራ 165 ኛ ደግሞ ወያኔ በዘረኛንት የሚገዛት ኢትዮጵያ ሆናለች በጥናቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጆ ለዜጎቻቸው በአስተማማኝ መንገድ ብቻ ሳይሆን በጥራት በማቅረብ ኮሪያ ቀዳም ስትሆን ዴንማርክና አይስላንድ አንደ ቅደም ተከተላችው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በጥፋቱ ሰንጠረዥ ትናንት ነጻነት አገኘሁ ያለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ በልጣና ተሽላ መገኘቷዘረኛዎቹ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሸርቡን ደባ ሸርና በግልጽ አሳይቷል

A telecommunications station in Addis Ababa, Ethiopiaበተያያዘ ዜና የወያኔ ቡድን ባለስልጣኖች በከፊል ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ በደቡብ አካባቢ  ለሚገኘው ተጠቃሚ የትዊተር የዋትስ አብፕ ና የሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ዘግቶ የነበረ መሆኑ ብሉመርግ የተባለ የዜና ወኪል አጋልጧል። የወያኔ አገልጋይ የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒከሽን መስሪያ ቤት የአገሪቷን የኢንተርኔት አገልግሎት በሞኖፖል የያዘ ሲሆን ተቀጣጥሎ ከተያያዘው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የኢንተርኔት አገግልጎትን በተለይም የሞባይል አገልግሎት ለመግዛት ማቀደቀዱ ቀደም ብሎ የተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣኖች የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆን ነው እንጅ ሆን ተብሎ የተወሰደ የመንግስት እርምጃ አይደለም ብለው በማለት መግለጫ ለመስጠት ቢሞክሩም አፈናው እንቅስቃሴውን ለማዳከም የተጠቀሙበት እርምጃ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑና ብሶት የገፋፋው የሕዝብ አመጽ በማናቸውም ዓይነት አፈና ሊዳከም እንደማይችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
Ø የወያኔ አገዛዝ ትውልድ ገዳይ የሆነ የትምህርት ፖሊስ ቀርጾ አንድ ዘርን ብቻ በዕውቀትና በሞራል ኮትኩቶ በማሳደግ ሌላውን ኢትዮጵያ ከንቱና ገልቱ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ ሱስና በጎጂ ባህል የታሰረ በማድረግ ተተኪ ትውልድ ለማሳጣት ጠንከሮ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በትግራይ ውስጥ በትምህርት ቤት አካባቢ መጠጥ መሸጥ ጫት መነገድ በት/ቤት ግቢ ስጋራ ማጤስ የከለከለው የወያኔ የትምህርት ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቱ ግቢ አጥር ተጠግቶ ወይም ተሸንቆ በተሰራ የንግድ ቤት አልኮል መጠጥና ሲጋራ እንዲሸጥ ማድረግ ይፈቅዳል። ለትምህርት ቤቱ ልዩ ገቢ ያስገኛል ተብለው የተከፈቱት የንግድ ሱቆች ከልዩ ልዩ ገቢ ጀምሮ የአልኮል መጠጦችን የሚሸጡ ሲሆን ተማሪዎችና መምህራን በእረፍት ጊዜያቸው ወደ ሱቆቹ ጎራ ማለታቸው እየተዘወተረና በትምህርት ሰዓትም መጠጥ የሚጠጡና ሲጋራ የሚያጨሱ መበርከታቸው ታውቋል። በአዲስ አባባ በደጃጅ ገነሜ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይህ ሁኔታ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ወላጆችችና ኅብረተሰብ አንድ ካላሉ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ገበታ መሆናቸው ቀርቶ የሱስ መሸመቻ ይሆናል በማለት የሚያስጠነቅቁ ዜጎች ብዙ ናቸው።

No comments:

Post a Comment