ከታምሩ ገዳ
የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስታቸው በጎረቤት አገር በኤርትራ ላይ የወረራ ዘመቻ ሊያደርግ መዘጋጀቱን እና የአውሮፓ ህብረት ለኤርትራ ያለውን ቀና አመለካከት ካልለወጠ /ሁኔታዎች ግፍተው ከመጡ ኢትዮጵያ የአወሮፓ ጎዳናዎችን በሰደተኞች እንደምታጨናንቃቸው አቶ ሃይለማሪያም ለአንድ የአውሮፓ ህብረት ከፈተኛ የፓርላማ አባል ሰሞኑን ማስጠንቀቃቸው ተገለጸ
ይህ “የማሰጠንቀቂያ” እና የማስፈራሪያ” ገለጻ የተደረገላቸው ሰሞኑን ከ አውሮፓ ህብረት መናገሻ ከተማ ቤልጂዩም/ ብራስለስ ወደ አዲስ አበባ ለሰራ ጉብኘት ያቀኑት በህብረቱ የሶሻሊስት እና የዲሞክራት ፓርቲ አባልት ጥምረት ፕሬዜዳንት የሆኑት ጅያኒ ፒቲላ ሲሆኑ የፓርላማው አባል እና የፓርቲው መሪ በአ/አ ቆይታቸው ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳልኝ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው የጠቀሰው ዘ ሁፊንግ ቶን ፖስት ድህረ ገጽ በእሮብ ሚያዚያ 6 / 2016 እኤአ እትሙ ሲያብራራው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካክል ባለፈው 1998 -2000 እኤአ ከተካሔደው ደም አፋስሽ የድንበር ይገባኛል ግጭት በሁዋላ የዘለቀው የውጥረት ደመና ዛሬም ማንጃበቡን የተናገሩት ሚስተር ጅያኒ “የተባበሩት መንግስትታት ያስተላለፈው ወሳኔን አሻፈረኝ ያለቸው አዲስ አበባ የመፍትሄ ሃሳቦች እንድታቀርብ ስትጠየቅ በአስመራ ያለው መንግስት አምባ ገነን በመሆኑ ለዚህም መፍትሄው የኤርትራ መንግስትን ማስወገድ እና ይህንንም ለማድረግ/ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል። በለውናል ሲሉ የአውሮፓው ህብረት የሕዝብ እንደራሴው ፣የሶሻሊስት እና የዲሞክራሲ ፓርቲ ሹሙ ለዜናው ዘገባው በሰልክ ገልጸውለታል።
ሚስተር ጅያኒ ለጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፍለ ጊዜ የብራስልሱ ወኪል ይህንኑ ሁኔታ በተመለከተ ሲናገሩ ” የአወሮፓ ህብረት ለ ኤርትራ የሚያደረገው እርዳታን አቁሟል ።እርዳታው ከቀጠለ ግን ኢትዮጵያ በኤርትራ መንግስት ላይ ወረራ ለማድረግ መዘጋጀቷን እና በግዛቷ (በኢትዮጵያ ) ውስጥ የሚገኙ በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኤርትራዊያን ሰደተኞችን ወደ ጣሊያን እና ወደ አውሮፓ አባል አገራት እንዲጎርፉ እንደምታደርጋቸው ዝተዋል። “ሲሉ ሚስተር ጅያኒ ለዘጋቢው ተናግረዋል ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ዛሬ ድርስ ያላቆመው “የገደብ የለሹ” ወታደራዊ ስልጠና የሚያደርገው “ኢትዮጵያ ልትወረን ሰለምትችል እራሳችንን በቅድሚያ ማዘጋጀት አለብን።” የሚል አቋም እንዳለው በሆፊንግተን ፖስት ላይ ተገልጿል። ከዚሁ ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ወደ ስልጠና ማእከል ሊወስዱ ከነበሩ ወጣት ኤርትራዊያኖች መካከል ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያለታወቀ ምልምሎች ከ መኪና ላይ በመወረድ ለመጥፋት ሲሞክሩ አደጋ እንደደረሰባቸው የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ መገናኛ ብዙሃናትን ዋቢ ያደረገው የእንግሊዙ (ቢቢሲ )በሚያዚያ 6/2016 እኤአ ዘግቦታል። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚ/ር አቶ የማነ ገ/መስቀል በበኩላቸው በወዳጆች መገናኛው ቲውተር አካውንታቸው”ለብሔራዊ አገልግሎት ወደ ስልጠና ማእከል በወታደራዊ ካሚዮን ሲጓዙ ከነበሩ መካከል ሁለት ምልምሎች አስመራ ከተማ ውስጥ ከመኪና ላይ ለመዝለል ሲሞክሩ ከደረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ሞተዋል።” በማለት የወጣቶቹ አሟሟት በራሳቸው ውስኔ እንደሆነ እና የሻቢያ መንግስት ታጣቂዎች ገደለዋች ዋል ተብሎ በአንዳንድ ሚዲያች የቀረበው ዘገባን አቶ የማነ ለማስተባበል ሞክረዋል።
የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ “ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል “ ዛቻ አንዳንድ ወገኖች በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት/ሕዝባዊ ቁጣን አቅጣጫን ለማስቀየር ፣አሊያም ከኤርትራ ጋር የዘለቀው “ጦርነት የለም፣ ሰላም የለም / No war , No peace “የሚለው አቀራረብን ለማጥበቅ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይገምታሉ። “የኤርትራ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንጎርፋለን ” የሚለው የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ ዛቻን በተመለከተ የቀደሞው የሊቢያው አምባገነን መሪ ኮ/ሌ መሃመድ ጋዳፊ በምእራባዊያን በተለይ ደግሞ አውሮፓዎች ባደረጉት ልግስና ሳቢያ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ሲዋጓቸው ጋዳፊ ”አርዳታችሁን ካላቆማችሁ በግዛቴ የሚገኙት በ10ሽዎች የሚቆጠሩ ህገ ዋጥ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲ ጎርፉ አደርጋለሁ።” በማለት መዛታቸው ይታወሳል። ጋዳፊም ተዋርደው ከስልጣን መውረዳቸው አይዘነጋም ፣የአውሮፓ ከተሞችም ዛሬ በመጠነ ሰፊ የስድተኞች ጎርፍ እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ። የኤርትራ መንግስት ከ ኢትዮጵያ በኩል ሰለ ቀረበበት ሰሞነኛው “የጦርነት ነጋሪት” ዙሪያ በተመለከተ አስከ አሁን ድረስ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች እና ኤርትራዊያኖች በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተገነባው “የጥላቻ ግንብን” ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመናድ እና በምትኩ ዘለቂታዊ ሰላም እና መረጋጋት ለመፍጠር ከተፈለገ ሁለቱ አምባገነኖች ( የ አ/አው ሕዋት/ኢሕ አዲግ እና የአስመራው አቻው ሻቢያን) ማስወገድ ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።
የአውሮፓ የፓርላማ አባላቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የኢሕ አዲግ መንግስት በዜጎቹ በተለይ በኦሮሚያ ወስጥ እየፈጸመ ያለውን የሰበዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ያሳደረደርባችው ስጋትን እና ሕብርቱም በቅርቡ በኢሕ አዲግ መንግስት ላይ ሰለ ወሰድው እርምጃ ሳይገልጹ አላለፉም።
No comments:
Post a Comment