Wednesday, April 13, 2016

የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በዛሬው ዕለት ከዕስር ተፈታ!



በነ አማን አሰፋ መዝገብ በ24ኛነት የተከሰሰው እና ላለፉት ከ3አመት በላይ በግፍ በማዕከላዊ፣ ቃሊቲ፣ ቂሊንጦ በጋዜጠኛነት ሞያው በመንቀሳቀሱ ብቻ ሲንገላታ የነበረው የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጀግናው ሰለሞን ከበደ በዛሬው ዕለት ከዕስር ተፈቱዋል።
የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው እና ሁሌም ለሞያው ታማኝ እና ትሁት በመሆኑ በመንግስት ጣት ተቀስሮበታል ለ3 አመታት በማንገላታት ከፍተኛ ቶርቸር ተፈፅሞበታል ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ከ3 አመታት በላይ መንገላታቱ እና በልፈፀመው ወንጀል በመንገላታቱ አለም አቀፍ የጋዜጠኛ መብት ተሟጋች ሲፒጄን ጀምሮ በርካታ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ወንጀል ሳይፈፅም እንደታሰረ እና በርካታ ግፎች እንደተፈፀሙበት ጠቅሰው መንግስት በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታው በተደጋጋሚ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።
መንግስት በማዕከላዊ እጅግ ዘግናኝ ቶርቸር ፈፅመውበት ካንገላቱት ቡሃላ ዛሬ እንዲለቀቅ አድርገውታል ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ እጅግ አስገራሚ ፀባይ ያለው ወጣት ሲሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያሉ ተከሳሾች ለጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ያላቸውን አድናቆት በተደጋጋሚ ሲገልፁ ቆይተዋል በነ አማን አፋ መዝገብ ተከሰው በቅርብ የተፈቱት ኡስታዝ ጀማል ሃሰን፣ኡስታዝ ኑረዲን፣ወንድማችን ኑሪ መዘይን፣ሳዳም አብዱረህማን እና የድሬዳዋው ጀግና ሰላሃዲን ሰኢድ ከዚ በፊት በቢኤን በቀረቡበት ወቅት ለጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ያላቸው አድናቆት እና ክብር መግለፃቸው ይታወቃል ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ከማዕከላዊ ወደ ቃሊቲ በተዘዋወረበት ከእህታችን ጋር የኒካህ ስነ ስርአቲን መፈፀሙ የሚታወቅ ነው!!
ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ እንኩዋን ከምትወደው ህዝበ ሙስሊም ጋር ቀላቀለክ ለማለት እንወዳለን!! ቢቢኤን ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደን ለማግኘት የምንሞክር ሲሆን ካገኘነው በምበሽት ፕሮግራም የምናቀርብ ይሆናል።አልሃምዱሊላህ!!! BBN

No comments:

Post a Comment