የህብር ሬዲዮሚያዚያ 2 ቀን 2008 ፕሮግራም
<… በድርቁ ከሰቆጣ ተሰደው በደብረ ብርሃን የሚገኙትን በአምስት መኪና ጭነው ብዙዎቹን ወደመጡበትመልሰዋቸዋል። ድርቁ ጎድቷቸዋል ወገኖቻችንን ተጎሳቁለው አፈር መስለው ማየት ይረብሻል ይሄሳያንሳቸው አትለምኑብሎ በፖሊስ ማሳደድ ግን ምን አይነት… >
አቶ አበበ ውቤ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ በደብረ ብርሃን በድርቁ ሳቢያ ተሰደው ከሰቆጣየመጡትን ወደነበሩበት ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አይቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ለማህበር ተሰበሰቡ ሰዎችንም ሆነ ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥተው በኦሮሞ ሕዝብላይየሚፈጸመውን በደል የሚቃወሙትን ኦነግ አስታጥቋችሁ መንግስት ልትወጉ ነው ማለት የወያኔ ሸፍጥነው። ወጣቶቹየወገናቸው ብሶት ቆጭቷቸው ለመብታቸው የተነሱ ናቸው …የኦሮሞ ሕዝብ ለመብቱመቆምን የወያኔ ጥይት፣እስር ሆነ የፈጠራ ክስ አያቆመውም አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ቢል እንኳመስዋዕትነቱን ከፍሎ ለነጻነቱ የሚያደርገው ትግልይቀጥላል ተዳፍኖ የሚቀር አይደለም ። ትግሉንሌላውም ሊቀላቀለው ይገባል።የተቃዋሚ ድርጅቶችም …>>
አባ ጫላ ለታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በአገር ቤት ባለፈው ሀሙስ ፍርድ ቤት ቀርበውክስስለተመሰረተባቸው የኦሮሞ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ በመንግስት ላይ ጦርነት ልትከፍቱ ነበርስለተባለባቸው ክስ ከሰጡትምላሽ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የግንቦት 7ቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የመን ላይ አፍኖ ለወሰደው የኢሃ አዲግ መንግስት የደህነነትሰራተኞችንለማጠናከር ከሎንዶን መንግስት የሚጎርፈው የገንዘብ እርዳታ በተመለከተ የእንግሊዝመንግስት፣የሰበዊ መብት ተሟጋቾች እና የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት የሰጡት አስተያየትን ያካተተው ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ (ዘ ስንድየ ሚይል ) ያወጣው ወቅታዊ ዘገባ ሲዳሰስ (ልዩ ሬፖርታዥ)
ከአፍሪካ አገሮች እስከ ምዕራባውያን አገሮች የተዘረጋው ዓለም አቀፍ የጉቦ የማቀባበል ቅሌትና ግንባርቀደም ተጠያቂውዩኒ ኦይል ኩባንያ ገበና ሲፈተሽ (ልዩ ጥንቅር)
<…ከሰቆጣ የመጣነው ረሃቡ አሰድዶን ነው። አሁን ወደ ሰቆጣ ካልሄዳችሁ ያሉት ለሁለት ወር ለአንድቤተሰብ አስራሁለት ጣሳ እህል ዕርዳታ እንሰጣለን ከዚያ ውጭ የለም ብለዋል…እምቢ ብለን ያልሄድነውአሁን በደብረ ብርሃንሚስቶቻችን ወጥተው እንዳይለምኑ ፖሊስ እያሳደደድ ነው። ትታሰራላችሁ ብለውያባርሩናል ችግር ላይ ነው ያለነው…>አቶ ይትባረክ ጻድቁ ከድርቁ ተፈናቃዮች አንዱ ለህብር ሬዲዮከሰጡት ቃለ ምልልስ በከፊል(ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ለከፋ አደጋ መጣሉ አለማቀፋዊ ሰጋትፈጥሯል
በአዲስ አበባ ለማህበር ጽዋ የተሰባሰቡ የኦሮሞ ወጣቶች ኦነግ ልኳችሁ መንግስትን ልትወጉ ነበር ተብለውክስቀረበባቸው
የኦነግ ጉዳዩ የወያኔ የፈጠራ ክስ ነው የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ በዚህማዳፈን አይቻልም ብሏል
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በስልጣን ኮርቻ ላይ መቆየት ከፈለጉ የባህሪይ ለውጥ እንዲያሳዩ አንድ የአውሮፓህብረትየሕዝብ አንደራሲዎች መሪ ሰሞኑን ተግሳጻዊ ምክር ሰጧቸው
ከኤርትራ የከዳው ሞላ አስግዶም መቀሌ ሙስና ሰፈር ላይ ሕወሓት ኢንቨስተር አድርጎ ቦታ መስጠቱተገለጸ
የኬኒያ አየር መንገድ ፓይለቶቹን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በተውሶ አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ የናይሮቢ ነዋሪዎችንአነጋገረ
ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ኬኒያዎችን አባረው መሬት መቆጣጠራቸው ተዘገበ
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ የሚል አዲስ የታሪክ መጽሐፍ ጻፉ
የዙምባብዊው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ “ይሞታል ብላቸሁ በመመኘታቸሁ አፈርኩባችሁ” በማለትተተኪዎቻቸውን በነገርሸነቆጧቸው
No comments:
Post a Comment